በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 ልጆቻችሁን አስተምሩ

ከአንድ ወንጀለኛ የምናገኘው ትምህርት

ከአንድ ወንጀለኛ የምናገኘው ትምህርት

ይህ ወንጀለኛ በሥዕሉ ላይ ኢየሱስ ሲያነጋግረው የሚታየው ነው። ይህ ሰው በሠራቸው ወንጀሎች ተጸጽቷል። በመሆኑም ኢየሱስን “ወደ መንግሥትህ ስትመጣ አስበኝ” በማለት ጠየቀው። በሥዕሉ ላይ እንደምትመለከተው ኢየሱስ ይህን ወንጀለኛ እያነጋገረው ነው። ኢየሱስ ምን እያለው እንደሆነ ታውቃለህ? * “እውነት እልሃለሁ ዛሬ፣ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” በማለት ቃል እየገባለት ነው።

ገነት ምን ዓይነት ቦታ ይመስልሃል?— የዚህን ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ለማግኘት እስቲ አምላክ ለመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት ማለትም ለአዳምና ለሔዋን አዘጋጅቶላቸው ስለነበረው ገነት እንመልከት። ይህ ገነት የሚገኘው የት ነበር? ሰማይ ወይስ ምድር?

ምድር ካልክ ትክክል ነህ። ስለዚህ ወንጀለኛው “በገነት” ውስጥ ይኖራል ሲባል ወደፊት ገነት በምትሆነው በዚህች ምድር ላይ ይኖራል ማለት ነው። ታዲያ ይህ ገነት ምን ይመስላል?— እስቲ እንመልከት።

ይሖዋ አምላክ የመጀመሪያዎቹን ባልና ሚስት ማለትም አዳምንና ሔዋንን ከፈጠረ በኋላ እዚሁ ምድር ላይ በገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህ ቦታ ‘የኤደን የአትክልት ስፍራ’ ይባላል። ‘የኤደን የአትክልት ስፍራ’ ምን ያህል የሚያምር ይመስልሃል?— በዛሬው ጊዜ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ካየው ከየትኛውም ስፍራ ይበልጥ የሚያምር እንደሆነ የታወቀ ነው!

ኢየሱስ፣ ወንጀለኛ ከነበረው ሰው ጋር እዚህ ምድር ላይ አብሮ ይኖራል ማለት ነው?— እንደዚያ ማለት አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ኢየሱስ በሰማይ ንጉሥ ሆኖ ገነት የምትሆነውን ምድር ይገዛል። በመሆኑም ኢየሱስ ከዚህ ወንጀለኛ ጋር ይሆናል ሲባል እሱን ከሞት በማስነሳት ገነት በምትሆነው ምድር ላይ በደስታ እንዲኖር ያደርገዋል ማለት ነው። ግን ኢየሱስ ወንጀለኛ የነበረን ሰው በገነት ውስጥ እንዲኖር የሚያደርገው ለምንድን ነው?— እስቲ ይህን ደግሞ እንመልከት።

 ይህ ወንጀለኛ በጣም መጥፎ ነገሮችን እንዳደረገ የታወቀ ነው። በምድር ላይ የሚኖሩ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎችም እንዲሁ አድርገዋል። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ሰዎች መጥፎ ነገር የሠሩት ስለ ይሖዋም ሆነ ከእነሱ ስለሚጠብቀው ነገር ስላልተማሩ ነው።

በመሆኑም ኢየሱስ በእንጨት ላይ በተሰቀለበት ወቅት ያነጋገረውን ወንጀለኛ ጨምሮ ስለ ይሖዋ የመማር አጋጣሚ ያላገኙ ሰዎች ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ከሞት ይነሳሉ። እነዚህ ሰዎች የአምላክ ፈቃድ ምን እንደሆነ ይማራሉ። ከዚያም ለይሖዋ ፍቅር ካላቸው ይህን በተግባር ያሳያሉ።

ይህን የሚያደርጉት እንዴት እንደሆነ ታውቃለህ?— አምላክ የሚጠብቅባቸውን ነገር በመፈጸም ነው። በገነት ውስጥ ይሖዋንም ሆነ ሌሎች ሰዎችን ከሚወዱ ሰዎች ጋር መኖር በጣም የሚያስደስት ይሆናል!

ከመጽሐፍ ቅዱስህ ላይ

^ አን.3 ይህን ርዕስ የምታነበው ከትንሽ ልጅ ጋር ከሆነ፣ ይህ ሰረዝ ቆም ብለህ ልጁ ሐሳቡን እንዲገልጽ እንድታበረታታው ለማስታወስ ተብሎ የተደረገ ነው።