በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይመከራ የበዛው ለምንድን ነው? የሚያበቃውስ መቼ ነው?

በርካታ ንጹሐን ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል!

በርካታ ንጹሐን ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል!

ሕፃኗ ኖኤል፣ ሥዕል መሣል የምትወድ አፍቃሪ ልጅ ነበረች። አንድ የበጋ ምሽት ላይ በቤታቸው ጓሮ ስትጫወት ተደናቅፋ መዋኛ ገንዳ ውስጥ በመውደቋ ሰጥማ ሞተች። ኖኤል፣ ከሁለት ሳምንት በኋላ አራት ዓመት ይሞላት ነበር።

ሻርሎት፣ ዳንዬል፣ ኦሊቪያ፣ ጆዜፊን . . . እነዚህ ልጆች፣ በከኔቲከት፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ታኅሣሥ 14 ቀን 2012 በጥይት ከተገደሉት 26 ሰለባዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፤ በዚህ ወቅት፣ ከስድስት እስከ ሰባት ዓመት ባለው ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ 20 ሕፃናት ተገድለዋል። በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ኦባማ፣ የሟቾቹን ሕፃናት ስም ከጠሩ በኋላ “እነዚህ አሳዛኝ ክስተቶች መቆም አለባቸው” በማለት ለተሰበሰቡት ሐዘንተኞች ተናገሩ።

የ18 ዓመቷ ባኖ እና ቤተሰቧ በ1998 ከኢራቅ ወደ ኖርዌይ በመሄድ በዚያ መኖር ጀመሩ። የባኖ ጓደኞች፣ “የፀሐይ ጮራ” በሚል የቁልምጫ ስም ይጠሯት ነበር። የሚያሳዝነው ግን ባኖ፣ ሐምሌ 22 ቀን 2011 አንድ ጽንፈኛ የሆነ ሰው የ77 ሰዎችን ሕይወት በማጥፋት የፈጸመው የዓመፅ ድርጊት ሰለባ ሆነች፤ ይህ ሰው “ይቅርታ መጠየቅ የምፈልገው ተጨማሪ ሰዎች መግደል ባለመቻሌ ነው” በማለት በጉራ ተናግሯል።

እንደ እነዚህ ዓይነት ልብ የሚሰብሩ ታሪኮች፣ በመላው ዓለም በተደጋጋሚ በዜና ዘገባ ላይ መቅረባቸው የተለመደ እየሆነ መጥቷል። አደጋዎች፣ ወንጀል፣ ጦርነት፣ ሽብርተኝነት፣ የተፈጥሮ አደጋዎችና ሌሎችም የሚያሳዝኑ ክስተቶች የሚያስከትሉትን ሐዘንና ሥቃይ ለማሰብ ሞክር። ብዙ ንጹሐን ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ እንዲሁም በሰዎች ላይ ይህ ነው የማይባል መከራ ይደርሳል፤ አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ ዓይነት ነገሮች የሚደርሱበት ምክንያት አይታወቅም።

አንዳንድ ሰዎች አምላክን የሚወቅሱ ሲሆን ፈጣሪያችን ስለ ሰው ዘር ደንታ እንደሌለው ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ፣ አምላክ የሚደርስብንን መከራ ቢመለከትም ጣልቃ መግባት እንደማይፈልግ ያስባሉ። አንዳንዶች፣ የሰው ልጆች እንዲህ ዓይነቶቹ አሳዛኝ ክስተቶች የሚያጋጥሟቸው ዕድላቸው ስለሆነ ነው የሚል አመለካከት አላቸው። ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። ታዲያ አስተማማኝና አጥጋቢ መልስ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው? የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ፣ የመከራ መንስኤ ምን እንደሆነና የሚያበቃው እንዴት እንደሆነ ለሚነሱት ጥያቄዎች ምን መልስ እንደሚሰጥ በሚቀጥሉት ርዕሶች ላይ እንመረምራለን።