በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ይህን ዓለም እየገዛ ያለው ማን ነው?

ይህን ዓለም እየገዛ ያለው አምላክ ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ መከራ ይኖር ነበር?

ብዙ ሰዎች የዚህ ዓለም ገዢ እውነተኛው አምላክ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ይሁን እንጂ ይህ እውነት ቢሆን ኖሮ ምድር ይህን ያህል በመከራ ትሞላ ነበር? (ዘዳግም 32:4, 5) መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ከሆነ ዓለም ክፉ በሆነ ኃይል ቁጥጥር ሥር ነው።—1 ዮሐንስ 5:19ን አንብብ።

ለመሆኑ አንድ ክፉ ኃይል የሰውን ዘር የመቆጣጠር ሥልጣን እንዴት ሊኖረው ቻለ? በሰው ልጆች ታሪክ መጀመሪያ ላይ አንድ መልአክ በአምላክ ላይ ያመፀ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስትም ከእሱ ጋር እንዲያብሩ ገፋፋቸው። (ዘፍጥረት 3:1-6) እነሱም ሰይጣን የተባለውን ዓመፀኛ መልአክ ለመታዘዝ በመምረጥ ገዢያቸው አደረጉት። የሰው ልጆችን ለመግዛት ሕጋዊ መብት ያለው ብቸኛው አካል ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ቢሆንም ሰዎች በፍቅር ተገፋፍተው እንዲገዙለት ይፈልጋል። (ዘዳግም 6:6፤ 30:16, 19) የሚያሳዝነው ግን አብዛኛው የሰው ዘር በሰይጣን ማታለያ በመሸነፍ ልክ እንደ መጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት መጥፎ ምርጫ አድርጓል።—ራእይ 12:9ን አንብብ።

የሰው ልጆችን ችግር መፍታት የሚችለው ማን ነው?

ክፉ የሆነው የሰይጣን አገዛዝ እንዲቀጥል አምላክ ይፈቅዳል? በፍጹም! አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት ሰይጣን የፈጸማቸውን ክፉ ነገሮች ሁሉ ያስወግዳል።—1 ዮሐንስ 3:8ን አንብብ።

ኢየሱስ ከአምላክ ባገኘው ሥልጣን ተጠቅሞ ሰይጣንን ይደመስሰዋል። (ሮም 16:20) ከዚያም አምላክ የሰውን ዘር መግዛት ይጀምራል፤ እንዲሁም መጀመሪያ አስቦት የነበረውን ደስታና ሰላም የሰፈነበት ሕይወት ለሰው ልጆች ይሰጣቸዋል።—ራእይ 21:3-5ን አንብብ።