በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በእርግጥ ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን አስነስቷል?

ኢየሱስ ለአራት ቀናት ሞቶ የቆየውን አልዓዛርን ከሞት አስነስቶታል

ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን እንዳስነሳ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል። ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን እንዳስነሳ የሚገልጹት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ተረት አይደሉም፤ የተፈጸሙበት ጊዜም ሆነ ቦታ በትክክል ተጠቅሷል። ለምሳሌ ያህል፣ በ31 ዓ.ም. የበጋ ወቅት ላይ ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን አስከትሎ ከቅፍርናሆም ወደ ናይን እየተጓዘ ነበር። ወደ ከተማዋ ሲደርሱ ብዙ ሕዝብ ከከተማዋ ሲወጣ አገኙ። በዚህ ወቅት ትንሣኤ እንደተፈጸመ በሚናገረው ታሪክ ላይ እምነት መጣል ትችላለህ፤ ምክንያቱም ይህ ታሪክ የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፤ በተጨማሪም ሁኔታው ሲፈጸም የተመለከቱ በርካታ የዓይን ምሥክሮች ነበሩ።—ሉቃስ 7:11-15ን አንብብ።

በተጨማሪም ኢየሱስ ለአራት ቀናት ሞቶ የቆየውን ወዳጁን አልዓዛርን ከሞት አስነስቷል። ኢየሱስ ይህንንም ተአምር የፈጸመው ብዙ የዓይን ምሥክሮች ባሉበት በመሆኑ ትንሣኤው ስለ መፈጸሙ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ።—ዮሐንስ 11:39-45ን አንብብ።

ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ያስነሳው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ያስነሳው ርኅሩኅ ስለነበረ ነው። በተጨማሪም ይህን ያደረገው የሕይወት ምንጭ የሆነው አባቱ በሞት ላይ ሥልጣን እንደሰጠው ለማሳየት ነው።—ዮሐንስ 5:21, 28, 29ን አንብብ።

ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ማስነሳቱ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሰጠው ተስፋ እንደሚፈጸም እንድንተማመን ያደርገናል። ኢየሱስ ስለ እውነተኛው አምላክ ምንም የማያውቁ ዓመፀኛ ሰዎችን ጨምሮ ሌሎች እጅግ ብዙ ሰዎችን ከሞት ያስነሳል። እነዚህ ሰዎች ስለ ይሖዋ አምላክ የመማርና እሱን እንደሚወድዱ ማሳየት የሚችሉበት አጋጣሚ ያገኛሉ።—የሐዋርያት ሥራ 24:15ን አንብብ።