በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ክፋት ከየት መጣ?

ኢየሱስን መጥፎ ነገር እንዲሠራ ሊያባብለው የሞከረው ማን ነው?—ማቴዎስ 4:8-10

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሰላማዊ፣ ሐቀኛና ደግ መሆን ይፈልጋሉ። ታዲያ ዓመፅ፣ ግፍና ጭካኔ የበዛው ለምንድን ነው? ዘግናኝ የዜና ዘገባዎች የተለመዱ ነገሮች እየሆኑ መጥተዋል። ሰዎች መጥፎ ነገር እንዲያደርጉ የሚገፋፋቸው አካል ይኖር ይሆን?—1 ዮሐንስ 5:19ን አንብብ።

አምላክ ሰዎችን የፈጠራቸው መጥፎ ነገር የመሥራት ዝንባሌ እንዲኖራቸው አድርጎ ነው? በፍጹም፤ ይሖዋ አምላክ ሰዎችን የፈጠራቸው በራሱ መልክ ይኸውም የእሱን ፍቅር የማንጸባረቅ ዝንባሌ እንዲኖራቸው አድርጎ ነው። (ዘፍጥረት 1:27፤ ኢዮብ 34:10) ይሁን እንጂ አምላክ ለሰዎች የመምረጥ ነፃነት በመስጠትም አክብሯቸዋል። የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን መጥፎ ነገር ለማድረግ በመረጡ ጊዜ የአምላክን ምሳሌነት ለመከተል እምቢተኛ በመሆናቸው ፍጽምና የጎደላቸው ሆኑ። እኛም ከእነሱ ኃጢአት የመሥራት ዝንባሌን ወርሰናል።—ዘዳግም 32:4, 5ን አንብብ።

ክፋት ምንጊዜም በውስጣችን ይኖራል?

አምላክ መጥፎ ዝንባሌዎቻችንን እንድንቆጣጠር ይፈልግብናል። (ምሳሌ 27:11) በመሆኑም ስህተት የሆነውን ነገር ከመፈጸም መቆጠብና እውነተኛ ደስታ ማግኘት የምንችልበትን መንገድ ያስተምረናል። ይሁንና በአሁኑ ጊዜ የአምላክን ፍቅር ፍጹም በሆነ መንገድ መኮረጅ አንችልም።—መዝሙር 32:8ን አንብብ።

በአሁኑ ጊዜ ክፋት ተንሰራፍቶ የሚገኝ ቢሆንም አምላክ ሁሉም ሰው የክፋትን አሳዛኝ መዘዞች ማየት እንዲችል ክፋት እንዲኖር የፈቀደው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው። (2 ጴጥሮስ 3:7-9) በቅርቡ ግን ምድር አምላክን በሚታዘዙ ደስተኛ ሰዎች ትሞላለች።—መዝሙር 37:9-11ን አንብብ።