በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

ሃይማኖትን የፈጠሩት ሰዎች ናቸው?

አንዳንዶች ምን ይላሉ? አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖትን የፈጠሩት የሰው ልጆች እንደሆኑ ይሰማቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ አምላክ፣ ሰዎች ወደ እሱ እንዲቀርቡ ለመርዳት በሃይማኖት እንደሚጠቀም ያምናሉ። አንተ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“በአምላካችንና በአባታችን ዓይን ንጹሕና ያልረከሰ ሃይማኖት” አለ። (ያዕቆብ 1:27 የግርጌ ማስታወሻ) የንጹሑ ወይም የእውነተኛው ሃይማኖት ምንጭ አምላክ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አንድ ሃይማኖት አምላክን የሚያስደስት እንዲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ መመሥረት አለበት።—ዮሐንስ 4:23, 24

  • በሰው አስተሳሰብ ላይ የተመሠረቱ ሃይማኖቶች ከንቱ ናቸው።—ማርቆስ 7:7, 8

የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን አስፈላጊ ነው?

ምን ትላለህ?

  • አዎ

  • አይደለም

  • እንደ ሁኔታው

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤ . . . መሰብሰባችንን ቸል አንበል።” (ዕብራውያን 10:24, 25) አምላክ፣ ሕዝቦቹ በተደራጀ መልኩ እንዲሰበሰቡ ይፈልጋል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አምላክን በኅብረት የሚያመልኩ ሰዎች በሚያምኑት ነገር ረገድ አንድነት ሊኖራቸው ይገባል።—1 ቆሮንቶስ 1:10, 11

  • በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሃይማኖት አባላት ዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር አላቸው።—1 ጴጥሮስ 2:17