በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

ሰዎች ምን ብለው ያምናሉ? አምላክ በሰው ልብ ውስጥ እንደሚገዛ የሚያመለክት ነገር ነው የሚሉ አሉ፤ ሌሎች ደግሞ ሰዎች ዓለም አቀፍ ሰላምና ወንድማማችነት ለማምጣት በሚያደርጉት ጥረት የሚገኝ ነገር እንደሆነ ያስባሉ። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን አመለካከት አለዎት?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት ያቋቁማል። ይህም መንግሥት . . . እነዚህን [ሰብዓዊ] መንግሥታት ሁሉ ያደቅቃል፤ ፈጽሞም ያጠፋቸዋል።” (ዳንኤል 2:44) የአምላክ መንግሥት እውን መስተዳድር ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • የአምላክ መንግሥት የሚገዛው በሰማይ ሆኖ ነው።—ማቴዎስ 10:7፤ ሉቃስ 10:9

  • አምላክ በዚህ መንግሥት አማካኝነት በሰማይም ሆነ በምድር ላይ ፈቃዱ እንዲፈጸም ያደርጋል። —ማቴዎስ 6:10

የአምላክ መንግሥት የሚመጣው መቼ ነው?

ምን ትላለህ?

  • ማንም አያውቅም

  • በቅርቡ ይመጣል

  • ፈጽሞ አይመጣም

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24:14) ምሥራቹ በተሟላ መልኩ ከተሰበከ በኋላ የአምላክ መንግሥት አሁን ያለውን ክፉ ሥርዓት ያጠፋል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • በምድር ላይ ያለ ማንም ሰው የአምላክ መንግሥት የሚመጣበትን ጊዜ በትክክል አያውቅም።—ማቴዎስ 24:36

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች መንግሥቱ በቅርቡ እንደሚመጣ ይጠቁማሉ።—ማቴዎስ 24:3, 7, 12