በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

አንድ ያልተጋቡ ወንድና ሴት አጠያያቂ በሆነ ሁኔታ አብረው ቢያድሩ ጉዳዩ በፍርድ ኮሚቴ መታየት ይኖርበታል?

አዎ፣ አብረው እንዲያድሩ የሚያስገድድ ሁኔታ ሳይኖር አብረው ማደራቸው የፆታ ብልግና ተፈጽሞ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም ጠንካራ ማስረጃ ነው፤ በመሆኑም ሌላ አጥጋቢ ምክንያት እስከሌለ ድረስ የፍርድ ኮሚቴ መቋቋም ይኖርበታል።—1 ቆሮ. 6:18

የሽማግሌዎች አካል የፍርድ ኮሚቴ መቋቋም ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም የሚለውን ለመወሰን እያንዳንዱን ሁኔታ በጥንቃቄ መመርመር ይኖርበታል። ለምሳሌ ያህል፦ አንዳቸው ለሌላው የፍቅር ስሜት እንደነበራቸው የሚያሳይ ማስረጃ አለ? እርስ በርስ በነበራቸው ግንኙነት ረገድ ከዚህ ቀደም ምክር ተሰጥቷቸው ያውቃል? አንድ ላይ እንዲያድሩ ያደረጋቸው ሁኔታ ምንድን ነው? እንዲህ ያደረጉት አቅደውበት ነው? አብረው ላለማደር አማራጭ ነበራቸው? ወይስ አብረው ከማደር ውጭ ምንም አማራጭ እንዳልነበራቸው የሚያሳምን ያልታሰበ ወይም ድንገተኛ ነገር አጋጥሟቸው ነበር? (መክ. 9:11) ያደሩት በምን ዓይነት ሁኔታ ነው? እያንዳንዱ ሁኔታ ስለሚለያይ ሽማግሌዎች ግምት ውስጥ ሊያስገቧቸው የሚገቡ ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ነገሮችም ሊኖሩ ይችላሉ።

የሽማግሌዎች አካል ሁኔታውን በሚገባ ካጣራ በኋላ ግለሰቦቹ የፈጸሙት ድርጊት በፍርድ ኮሚቴ መታየት ይኖርበት እንደሆነና እንዳልሆነ ይወስናል።