በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ደቀ መዝሙሩ እስጢፋኖስ ከባድ ተቃውሞ ባጋጠመው ወቅት አስደናቂ መረጋጋት ሊኖረው የቻለው እንዴት ነው?

እስጢፋኖስ በጥላቻ ከተሞሉ ሰዎች ጋር ፊት ለፊት ተፋጧል። እነዚህ 71 ዳኞች የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማለትም የሳንሄድሪን ሸንጎ አባላት እንደመሆናቸው መጠን በብሔሩ ውስጥ ትልቅ ሥልጣን አላቸው። ዳኞቹን የሰበሰባቸው ከጥቂት ወራት በፊት ኢየሱስ ሞት በተፈረደበት ወቅት ፍርድ ቤቱን በሊቀ መንበርነት የመራው ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ነው። (ማቴ. 26:57, 59፤ ሥራ 6:8-12) ዳኞቹ የሐሰት ምሥክሮችን እያከታተሉ በሚያቀርቡበት ጊዜ በእስጢፋኖስ ላይ አንድ የሚያስደንቅ ነገር ተመለከቱ፤ “ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ታያቸው።”—ሥራ 6:13-15

እስጢፋኖስ እንዲህ ባለ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ይህን ያህል ሊረጋጋ የቻለው እንዴት ነው? እስጢፋኖስ ወደ ሳንሄድሪን ከመወሰዱ በፊት፣ ኃያል በሆነው የአምላክ መንፈስ እየተመራ የተሰጠውን ሥራ በትጋት ያከናውን ነበር። (ሥራ 6:3-7) ለፍርድ በቀረበበት ጊዜም ቢሆን ይኸው መንፈስ አጽናኝና አስታዋሽ በመሆን በእሱ ላይ እየሠራ ነበር። (ዮሐ. 14:16 ግርጌ) እስጢፋኖስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 7 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን የመከላከያ ሐሳቡን በድፍረት ሲያቀርብ መንፈስ ቅዱስ በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ያሉ 20 ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ጥቅሶችን ማስታወስ እንዲችል ረድቶታል። (ዮሐ. 14:26) ይሁን እንጂ የእስጢፋኖስን እምነት ይበልጥ ያጠናከረው ኢየሱስን በአምላክ ቀኝ ቆሞ በራእይ መመልከቱ ነው።—ሥራ 7:54-56, 59, 60

እኛም አንድ ቀን ዛቻ ወይም ስደት ይደርስብን ይሆናል። (ዮሐ. 15:20) የአምላክን ቃል አዘውትረን መመገባችንና በአገልግሎት ንቁ ተሳትፎ ማድረጋችን የይሖዋ መንፈስ በእኛ ላይ እንዲሠራ ያደርጋል። በተጨማሪም ውስጣዊ ሰላማችንን ይዘን እንድንቀጥልና ተቃውሞን ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት እንድናገኝ ይረዳናል።—1 ጴጥ. 4:12-14