በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 20–21

“ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል”

“ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል”

20:28

ኩሩ የነበሩት ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በገበያ ቦታ ሰዎች ትኩረት እንዲሰጧቸውና እጅ እንዲነሷቸው ይፈልጉ ነበር

ኩሩ የነበሩት ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ሌሎችን ማስደመምና የክብር ቦታ ማግኘት ይፈልጉ ነበር። (ማቴ 23:5-7) ኢየሱስ ግን ከእነሱ ፈጽሞ የተለየ ነበር። ‘የሰው ልጅ የመጣው ለማገልገል እንጂ እንዲገለገል አይደለም።’ (ማቴ 20:28) እኛስ የሰዎችን ትኩረት በሚስቡና በሌሎች ዘንድ አድናቆት እንድናተርፍ በሚያደርጉ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የማተኮር ዝንባሌ አለን? እንደ ክርስቶስ ታላቅ መሆን የሚቻለው ሌሎችን በማገልገል ነው። እንዲህ ያለው ሥራ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ የሚከናወነው ከሰዎች እይታ ውጭ ነው፤ በመሆኑም የምናደርገውን ነገር ከይሖዋ በቀር ማንም ላያየው ይችላል። (ማቴ 6:1-4) ትሑት የሆነ አገልጋይ . . .

  • የስብሰባ አዳራሹን በማጽዳቱና በመጠገኑ ሥራ ይካፈላል

  • ቅድሚያውን ወስዶ አረጋውያንንና ሌሎችን ይረዳል

  • ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለመደገፍ የገንዘብ መዋጮ ያደርጋል