በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከመጋቢት 12-18

ማቴዎስ 22–23

ከመጋቢት 12-18
  • መዝሙር 30 እና ጸሎት

  • የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

  • ሁለቱን ታላላቅ ትእዛዛት ጠብቁ”፦ (10 ደቂቃ)

    • ማቴ 22:36-38—እነዚህ ጥቅሶች ከሕጉ ውስጥ ከሁሉ የሚበልጠውንና የመጀመሪያውን ትእዛዝ መጠበቅ ምን ነገሮችን እንደሚጨምር የሚያብራሩት እንዴት ነው? (“ልብ፣” “ነፍስ፣” “አእምሮ” ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች​—⁠ማቴ 22:37፣ nwtsty)

    • ማቴ 22:39—ከሕጉ ውስጥ ሁለተኛው ታላቅ ትእዛዝ የትኛው ነው? (“ሁለተኛው፣” “ባልንጀራ” ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች​—⁠ማቴ 22:39፣ nwtsty)

    • ማቴ 22:40—የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት በሙሉ በፍቅር ላይ የተመሠረቱ ናቸው (“ሕግም ሆነ የነቢያት ቃል፣” “የተመሠረቱ” ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች​—⁠ማቴ 22:40፣ nwtsty)

  • መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)

    • ማቴ 22:21—‘የቄሳር የሆኑት’ ነገሮች ምንድን ናቸው? ‘የአምላክ የሆኑት’ ነገሮችስ ምንድን ናቸው? (“የቄሳር የሆነውን ለቄሳር፣” “የአምላክ የሆነውን . . . ለአምላክ” ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች​—⁠ማቴ 22:21፣ nwtsty)

    • ማቴ 23:24—ኢየሱስ ይህን ሐሳብ የተናገረው ምን ለማለት ፈልጎ ነው? (“ትንኝን አጥልላችሁ ታወጣላችሁ፤ ግመልን ግን ትውጣላችሁ”​—⁠ማቴ 23:24፣ nwtsty)

    • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

    • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ማቴ 22:1-22

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

  • መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም።

  • የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውትና ተወያዩበት።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) bhs ገጽ 199 አን. 8-9—የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ፣ የሚያውቃቸውን ሰዎች መታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ እንዲጋብዝ አበረታታ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት