በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የጉልበተኞችን ጥቃት ለመቋቋም በይሖዋ ታመኑ

የጉልበተኞችን ጥቃት ለመቋቋም በይሖዋ ታመኑ

ጉልበተኞች አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ሥቃይ ሊያስከትሉብን ይችላሉ። አምልኳችንን ሲቃወሙ ከተሸበርን ደግሞ መንፈሳዊ ጉዳትም ሊያደርሱብን ይችላሉ። ታዲያ ራሳችሁን ከጉልበተኞች ጥቃት መጠበቅ የምትችሉት እንዴት ነው?

በርካታ የይሖዋ አገልጋዮች በእሱ በመታመን የጉልበተኞችን ጥቃት መቋቋም ችለዋል። (መዝ 18:17) ለምሳሌ አስቴር፣ ጉልበተኛ የነበረው ክፉው ሃማ የሸረበውን ሴራ በድፍረት አጋልጣለች። (አስ 7:1-6) እንዲህ ከማድረጓ በፊት ግን በመጾም በይሖዋ እንደምትታመን አሳይታለች። (አስ 4:14-16) ይሖዋ እሷንም ሆነ ሕዝቦቹን በመታደግ ጥረቷን ባርኮላታል።

ወጣቶች፣ እናንተም ጉልበተኞች ካስቸገሯችሁ ይሖዋ እንዲረዳችሁ ጠይቁት፤ እንዲሁም ስላጋጠማችሁ ችግር ለወላጆቻችሁ ወይም ለሌላ ትልቅ ሰው ተናገሩ። ይሖዋ አስቴርን እንደረዳት ሁሉ እናንተንም እንደሚረዳችሁ መተማመን ትችላላችሁ። የጉልበተኞችን ጥቃት ለመቋቋም ሌላስ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

የወጣትነት ሕይወቴ—የጉልበተኞችን ጥቃት መቋቋም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ወጣቶች ከቻርሊና ከፈሪን ተሞክሮ ምን ትምህርት ያገኛሉ?

  • ወላጆች ልጆቻቸው የጉልበተኞችን ጥቃት እንዲቋቋሙ መርዳት የሚችሉበትን መንገድ በተመለከተ ቻርሊና ፈሪን ከሰጡት ሐሳብ ምን ትምህርት ያገኛሉ?