በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለይሖዋ ሕዝቦች ጥቅም የቆሙ እረኞች

ለይሖዋ ሕዝቦች ጥቅም የቆሙ እረኞች

ብዙዎች ሥልጣን ላይ ላሉ ሰዎች አሉታዊ አመለካከት አላቸው። ደግሞም አይፈረድባቸውም። የሰው ልጆች ለበርካታ ዘመናት ሥልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም የራሳቸውን ጥቅም ሲያራምዱ ኖረዋል። (ሚክ 7:3) በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሽማግሌዎች ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ለይሖዋ ሕዝቦች ጥቅም እንዲቆሙ ሥልጠና በማግኘታቸው ምንኛ አመስጋኞች ነን!—አስ 10:3፤ ማቴ 20:25, 26

በዓለም ውስጥ ሥልጣን ላይ ካሉ ሰዎች በተቃራኒ ሽማግሌዎች የበላይ ተመልካች ለመሆን የሚጣጣሩት ለይሖዋና ለሕዝቡ ፍቅር ስላላቸው ነው። (ዮሐ 21:16፤ 1ጴጥ 5:1-3) በኢየሱስ አመራር ሥር ያሉት እነዚህ እረኞች እያንዳንዱ አስፋፊ በይሖዋ ቤተሰብ ውስጥ ቦታ እንዳለው እንዲሰማውና ወደ እሱ እንዲቀርብ ለመርዳት ጥረት ያደርጋሉ። ለይሖዋ በጎች መንፈሳዊ እርዳታ ለመስጠት እንዲሁም ድንገተኛ የጤና እክል ወይም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥማቸው እገዛ ለማድረግ ፈጣኖች ናቸው። እርዳታ የሚያስፈልግህ ከሆነ፣ ቅድሚያውን ወስደህ በጉባኤህ ውስጥ ያለን አንድ ሽማግሌ ለምን አታነጋግርም?—ያዕ 5:14

መንጋውን የሚንከባከቡ እረኞች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ማሪያና ሽማግሌዎች ከሰጧት እርዳታ የተጠቀመችው እንዴት ነው?

  • ኤልያስ ሽማግሌዎች ከሰጡት እርዳታ የተጠቀመው እንዴት ነው?

  • ቪዲዮውን ከተመለከትክ በኋላ ሽማግሌዎች ስለሚያከናውኑት ሥራ ምን ተሰማህ?