በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የJW.ORGን መነሻ ገጽ በአገልግሎት ላይ ተጠቀሙበት

የJW.ORGን መነሻ ገጽ በአገልግሎት ላይ ተጠቀሙበት

የድረ ገጻችን መነሻ ገጽ ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች ሊማርኩ የሚችሉ ርዕሶችንና ቪዲዮዎችን ያስተዋውቃል። (ሥራ 13:48) ብዙውን ጊዜ፣ በዜና ላይ የቀረቡ እንዲሁም ሰዎች የሚያስቧቸውንና የሚነጋገሩባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ይዳስሳል።

የ​jw.org​ን መነሻ ገጽ በአገልግሎት ላይ መጠቀም የምትችሉት እንዴት ነው?

  • ድረ ገጹን አዘውትራችሁ ተመልከቱ። ያስተዋወቅነው ርዕሰ ጉዳይ ምን እንደሆነ ካያችሁ በኋላ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ለመርዳት ልትጠቀሙበት የምትችሉት እንዴት እንደሆነ አስቡ። (በቅርቡ መነሻ ገጹ ላይ አስተዋውቀናቸው የነበሩ ሌሎች ርዕሶችን ለማግኘት “ተጨማሪ ለመመልከት” የሚለውን ጠቅ አድርጉ።) ድረ ገጹን በየጊዜው መመልከታችሁ መግቢያችሁን ወቅታዊ ለማድረግ ይረዳችኋል።

  • በመነሻ ገጹ ላይ ያስተዋወቅናቸውን ርዕሶችና ቪዲዮዎች ተጠቅማችሁ ውይይት ጀምሩ። በዚህ ገጽ ላይ የቀረቡት ርዕሶች በክልላችን ውስጥ ያሉት ሰዎች የሚያሳስቧቸውን ጉዳዮች ለማወቅ ይረዱናል።

  • ለሰዎች መነሻ ገጹን አሳዩ። አንድን ርዕሰ ጉዳይ ካነሳችሁ በኋላ ግለሰቡ ከድረ ገጹ መረጃ ማግኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳዩት።

  • ሊንክ ላኩ። አንዳንድ ሰዎች እኛን በአካል ማነጋገር ባይፈልጉም ድረ ገጻችንን ለመጎብኘት ፈቃደኛ ናቸው። በመሆኑም ፍላጎት ላላቸው ሰዎች የመነሻ ገጹን ወይም በዚያ ላይ የቀረበን አንድ ርዕስ ወይም ቪዲዮ ሊንክ ከመላክ ወደኋላ አትበሉ።