በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ፈጣሪያቸውን እንዲያውቁ እርዷቸው

ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ፈጣሪያቸውን እንዲያውቁ እርዷቸው

ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ጥሩ ምላሽ እንደማይሰጡ በማሰብ ለእነሱ ከመስበክ ወደኋላ ብላችሁ ታውቃላችሁ? ከሆነ፣ አምላክ የለሾችን ጨምሮ ሃይማኖት የሌላቸው ብዙ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች መሆን እንደቻሉ አስታውሱ። ብዙዎቹን ለዚህ ያበቃቸው አምላክ መኖሩን የሚያሳየውን ማስረጃ እንዲመረምሩ የተሰጣቸው ጥቂት ማበረታቻ ነው።—ሮም 1:20፤ 10:14

እምነት የለሽ ሰዎች እምነት ሊያዳብሩ እንደሚችሉ አስታውሱ!—ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦

የቶማዞ ተሞክሮ ሃይማኖት ለሌላቸው ሰዎች ስለመስበክ አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ የሚረዳህ እንዴት ነው?