በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ወላጆች—ልጆቻችሁ አምላካዊ ጥበብን እንዲያገኙ እርዷቸው

ወላጆች—ልጆቻችሁ አምላካዊ ጥበብን እንዲያገኙ እርዷቸው

ወላጆች ልጆቻቸው አምላካዊ ጥበብን እንዲያገኙ መርዳት ከሚችሉባቸው ግሩም መንገዶች አንዱ ከክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ጥቅም እንዲያገኙ መርዳት ነው። ልጆች በስብሰባ ላይ የሚያዩት፣ የሚሰሙትና ሐሳብ ሲሰጡ የሚናገሩት ነገር ስለ ይሖዋ እንዲማሩና የቅርብ ወዳጆቹ እንዲሆኑ ሊረዳቸው ይችላል። (ዘዳ 31:12, 13) ወላጅ ከሆናችሁ፣ ልጆቻችሁ ከስብሰባዎች የተሟላ ጥቅም እንዲያገኙ ልትረዷቸው የምትችሉት እንዴት ነው?

  • በስብሰባዎች ላይ በአካል ለመገኘት ልባዊ ጥረት አድርጉ።—መዝ 22:22

  • ከስብሰባ በፊት ወይም በኋላ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ ከወንድሞች ጋር ለመጨዋወት ጊዜ መድቡ።—ዕብ 10:25

  • ሁሉም የቤተሰባችሁ አባል በስብሰባ ላይ የሚጠናው ጽሑፍ እንዲኖረው አድርጉ፤ ዲጂታል ወይም በወረቀት የታተመው ሊሆን ይችላል

  • ልጆቻችሁ በራሳቸው አባባል መልስ እንዲመልሱ አዘጋጇቸው።—ማቴ 21:15, 16

  • ስለ ስብሰባዎችና በዚያ ስለምታገኙት ትምህርት አዎንታዊ ነገር ተናገሩ

  • ልጆቻችሁ የስብሰባ አዳራሹን እንደማጽዳት እንዲሁም በጉባኤው ውስጥ ካሉ አረጋውያን ጋር እንደመጨዋወት ባሉ እንቅስቃሴዎች እንዲካፈሉ እርዷቸው

ልጆቻችሁ ወደ ይሖዋ እንዲቀርቡ መርዳት ከባድ ሥራ ነው፤ አንዳንድ ጊዜም ከአቅማችሁ በላይ እንደሆነባችሁ ሊሰማችሁ ይችላል። ያም ቢሆን ይሖዋ እንደሚረዳችሁ እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ።—ኢሳ 40:29

ወላጆች፣ በይሖዋና እሱ በሚሰጣችሁ ብርታት ታመኑ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ድካም በዛክና በሊያ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሮባቸዋል?

  • ወላጆች ብርታት ለማግኘት ወደ ይሖዋ ዘወር ማለት ያለባቸው ለምንድን ነው?

  • ዛክና ሊያ በይሖዋ እርዳታ እንደሚታመኑ ያሳዩት በየትኞቹ መንገዶች ነው?