በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ድረ ገጻችንን ለመጠቀም የሚረዱ ሐሳቦች

ድረ ገጻችንን ለመጠቀም የሚረዱ ሐሳቦች

ያስተዋወቅናቸውን ርዕሶች ማግኘት

ብዙ ወንድሞችና እህቶች በ​jw.org መነሻ ገጽ ላይ የሚተዋወቁትን ርዕሶች ለአገልግሎት ይጠቀሙባቸዋል። በኤሌክትሮኒክ መሣሪያችን አማካኝነት በቀላሉ ለሌሎች ልናጋራ የምንችላቸው እነዚህ ርዕሶች በአብዛኛው የሚያብራሩት በዓለማችን ላይ እየተከናወኑ ያሉት ነገሮች የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት እንዲፈጸም የሚያደርጉት እንዴት እንደሆነ ነው። አንድ ወንድም እንደጻፈው መነሻ ገጽ ላይ የሚወጡት ርዕሶች “አሁን አገልግሎታችንን እያከናወንን ላለንበት መንገድ በጣም ተስማሚ ናቸው።”

ሆኖም መነሻው ገጽ ላይ የሚተዋወቁት ርዕሶች በየጊዜው ይቀየራሉ፤ ታዲያ መነሻው ገጽ ላይ የማይታዩ ርዕሶችን ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?

  • jw.org መነሻ ገጽ ላይ ከላይ አካባቢ ያለውን “ተጨማሪ ለመመልከት” የሚለውን ጠቅ አድርጉ። ይህ ሊንክ “መነሻ ገጽ ላይ በቅርቡ ያስተዋወቅናቸው” ወደሚለው ገጽ ይወስዳችኋል፤ በቅርቡ ያስተዋወቅናቸውን ተጨማሪ ርዕሶች እዚህ ገጽ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

  • jw.org ወይም JW Library® ላይ “ላይብረሪ” የሚለውን ምረጡ፤ በዚያ ሥር “ተከታታይ ርዕሶች” ከዚያም “ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች” የሚለውን ምረጡ። በመነሻ ገጹ ላይ ካስተዋወቅናቸው ርዕሶች መካከል አብዛኞቹን በዚህ ክፍል ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።