የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን የግድ አስፈላጊ ነው? አጫውት የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን የግድ አስፈላጊ ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? አዎ፣ ምክንያቱም ሰዎች ለአምልኮ አንድ ላይ እንዲሰባሰቡ አምላክ ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤ . . . መሰብሰባችንን ቸል አንበል።”—ዕብራውያን 10:24, 25 ኢየሱስ “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ሰዎች ሁሉ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ” በማለት የተናገረው ሐሳብ ደቀ መዛሙርቱ አንድ የተደራጀ ቡድን እንደሚመሠርቱ ይጠቁማል። (ዮሐንስ 13:35) የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ይህን ዓይነቱን ፍቅር ማሳየት ከሚችሉባቸው ዋነኛ መንገዶች አንዱ ከእምነት አጋሮቻቸው ጋር መሰብሰብ ነው። ዘወትር አንድ ላይ ተሰብስበው አምልኳቸውን ለመፈጸም ጉባኤዎችን ማቋቋም አለባቸው። (1 ቆሮንቶስ 16:19) እነዚህ ጉባኤዎች ደግሞ አንድ ላይ ዓለም አቀፋዊ አንድነት ያለው የወንድማማች ማኅበር ይመሠርታሉ።—1 ጴጥሮስ 2:17 የአንድ ሃይማኖት አባል ከመሆን የበለጠ ነገር ያስፈልጋል መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች አምላክን ለማምለክ አንድ ላይ መሰብሰብ እንዳለባቸው ሲናገር አንድ ሰው የአንድ ሃይማኖት አባል መሆኑ ብቻውን አምላክን ያስደስተዋል ማለቱ አይደለም። ግለሰቡ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፈለገ ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት የዕለት ተዕለት ሕይወቱን መምራት አለበት። ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “በአምላካችንና በአባታችን ዓይን ንጹሕና ያልረከሰ ሃይማኖት ‘ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና መበለቶችን በመከራቸው መርዳት እንዲሁም ከዓለም እድፍ ራስን መጠበቅ’ ነው።”—ያዕቆብ 1:27 የግርጌ ማስታወሻ ተዛማጅ ርዕሶች እምነት እና አምልኮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው እነዚህንስ አይተሃቸዋል? መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች አምላክ ሁሉንም ሃይማኖቶች ይቀበላል? ብዙ ሰዎች የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ብትሆን ለውጥ እንደሌለው ይናገራሉ። በአገልግሎት የምንጠቀምባቸው መግቢያዎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ማወቅ ትፈልጋለህ? ብዙ ሰዎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ማንነት ማወቅ ይፈልጋሉ። ስለ ማንነታችን ከእኛ ከራሳችን እንድትሰማ እንጋብዝሃለን። ስብሰባዎች በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? አንተው ራስህ እንድትመለከት እንጋብዝሃለን። ስለ እኛ በስብሰባዎቻችን ላይ እንድትገኝ ጋብዘንሃል ስለ ስብሰባዎቻችን ማወቅ ትፈልጋለህ? ለአንተ ቅርብ የሆነው የመሰብሰቢያ ቦታ የት እንደሆነ እዚህ ገጽ ላይ መፈለግ ትችላለህ። አትም አጋራ አጋራ የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን የግድ አስፈላጊ ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን የግድ አስፈላጊ ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን የግድ አስፈላጊ ነው? https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/502015170/univ/art/502015170_univ_sqr_xl.jpg ijwbq 90