በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 5, 2019
ፊሊፒንስ

ፊሊፒንስ በምድር መናወጦች ተመታች

ፊሊፒንስ በምድር መናወጦች ተመታች

ሐምሌ 27, 2019 ፊሊፒንስ ውስጥ ከማኒላ ከተማ 690 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ኢትባያት የተባለች አነስተኛ ደሴት በሁለት የምድር መናወጦች ተመታች። የምድር መናወጦቹ በመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ 5.4 እና 6.4 ተመዝግበዋል። በአደጋው 9 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ 64 ሰዎች ቆስለዋል፤ 266 ቤቶች ደግሞ ፈራርሰዋል። ባለሥልጣናቱ እንደገለጹት በምድር መናወጦቹ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር 2,968 ነው።

በምድር መናወጦቹ ምክንያት የሞተ አንድም የይሖዋ ምሥክር የለም። ሆኖም አንዲት እህት መጠነኛ የአካል ጉዳት ደርሶባታል። ከዚህም ሌላ ሁለት የወንድሞቻችን ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ቅርንጫፍ ቢሮው የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ያዋቀረ ሲሆን እንደ ምግብና ውኃ ያሉ መሠረታዊ ነገሮችን የመግዛቱንና የማሰራጨቱን ሥራ እያደራጀ ነው። የቅርንጫፍ ቢሮው ተወካዮች በአደጋው የተጠቁ ወንድሞችንና እህቶችን በመጎብኘት መንፈሳዊ ማበረታቻና ተግባራዊ እርዳታ ለመስጠት ተዘጋጅተዋል።

በምድር መናወጦቹ ለተጠቁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንጸልያለን። “የመጽናናት ሁሉ አምላክ” የሆነው ይሖዋ ወንድሞቻችን የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንደሚያሟላላቸው እንተማመናለን።—2 ቆሮንቶስ 1:3