በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በናቶኒን፣ ማውንቴን ግዛት የደረሰው የመሬት መንሸራተት ያስከተለው ጉዳት

ነሐሴ 14, 2019
ፊሊፒንስ

በፊሊፒንስ የጣለው ኃይለኛ ዝናብ ጉዳት አስከተለ

በፊሊፒንስ የጣለው ኃይለኛ ዝናብ ጉዳት አስከተለ

ነሐሴ 2019 መጀመሪያ ላይ የፊሊፒንስ ዝናባማ ወቅት የጀመረ ሲሆን በጣለው ከባድ ዝናብና በኃይለኛ ነፋሱ ምክንያት የጎርፍ መጥለቅለቅና የመሬት መንሸራተት አጋጥሟል። የሚያሳዝነው፣ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆኖ የሚያገለግል አንድ ወንድም በናቶኒን፣ ማውንቴን ግዛት በደረሰው የመሬት መንሸራተት ምክንያት ሕይወቱን አጥቷል። ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆኖ የሚያገለግል ሌላ ወንድምም በዚያው የመሬት መንሸራተት የተነሳ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል። በሌላ ቦታ ደግሞ አንድ የአሥር ዓመት ልጅ በፍርስራሹ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም አስፈላጊው የሕክምና እርዳታ ተደርጎለታል።

ከወንድሞቻችን ቤቶች መካከል ከባድ ጉዳት የደረሰበት የለም። ሆኖም በኔግሮስ ኦክሲደንታል የሚገኝ አንድ የስብሰባ አዳራሽ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል፤ በኃይለኛው ነፋስ የተነሳ የጣሪያው የተወሰነ ክፍል ወድቋል።

የፊሊፒንስ ቅርንጫፍ ቢሮ እና በአካባቢው የሚያገለግለው የወረዳ የበላይ ተመልካች በአደጋው ለተጎዱ ወንድሞችና ለቤተሰቦቻቸው መንፈሳዊና ስሜታዊ ድጋፍ እየሰጡ ነው።

ወንድማችንን በማጣታችን በጣም አዝነናል፤ እንዲሁም ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ እንዲጽናኑ እንጸልያለን። እንዲህ ያሉ አሳዛኝ ነገሮች ጨርሶ ‘የማይታወሱበትን’ ጊዜ እንናፍቃለን።—ኢሳይያስ 65:17 የግርጌ ማስታወሻ