በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 14, 2020
ሊባኖስ

በቤይሩት፣ ሊባኖስ የደረሰው ከባድ ፍንዳታ

በቤይሩት፣ ሊባኖስ የደረሰው ከባድ ፍንዳታ

ነሐሴ 4, 2020 የሊባኖስ ዋና ከተማ በሆነችው በቤይሩት የደረሰው ከባድ ፍንዳታ በአንድ ወደብ ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል። ይህ አውዳሚ ፍንዳታ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ካስከተለው ጉዳት በተጨማሪ ይህ ነው የማይባል ጥፋት አድርሷል። የበርካታ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ቤቶች በፍንዳታው ተጎድተዋል። የሚያሳዝነው ጥቂት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ሆኖም ከወንድሞቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም።

ለጋሱ አምላካችን ለአገልጋዮቹ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ መስጠቱን እንደሚቀጥል እንተማመናለን።—2 ሳሙኤል 22:3