በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ኒኮላዬቭ እና ባለቤቱ ዬቭጌኒያ

ታኅሣሥ 30, 2021
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ይግባኙ ውድቅ ተደረገ | ወንድም ኒኮላዬቭ በይሖዋ ላይ ያለው እምነት ውስጣዊ ሰላሙን ጠብቆ እንዲቀጥል ረድቶታል

ወቅታዊ መረጃ—ይግባኙ ውድቅ ተደረገ | ወንድም ኒኮላዬቭ በይሖዋ ላይ ያለው እምነት ውስጣዊ ሰላሙን ጠብቆ እንዲቀጥል ረድቶታል

ጥቅምት 20, 2022 የክራስኖዳር ግዛት ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሳንደር ኒኮላዬቭ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል። አሌክሳንደር እስር ቤት ይቆያል።

የክሱ ሂደት

  1. ታኅሣሥ 23, 2021

    በክራስኖዳር ክልል የሚገኘው የአብንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት አሌክሳንደር ጥፋተኛ ነው በማለት በሁለት ዓመት ተኩል እስራት እንዲቀጣ ወሰነ

  2. መስከረም 30, 2021

    ማረፊያ ቤት ገባ

  3. ነሐሴ 4, 2021

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  4. ግንቦት 26, 2021

    ከቤተሰቡና ከወዳጆቹ ጋር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ተወያይቷል በሚል ወንጀል ተከሰሰ፤ መርማሪዎቹ ይህን ድርጊት “በሕገ መንግሥታዊው ሥርዓትና በአገሪቱ ደህንነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል” እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩታል

  5. ሚያዝያ 7, 2021

    ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ የደህንነት አባላትና ፖሊሶች ወንድም ኒኮላዬቭና ቤተሰቡ የሚኖሩበትን ቤት ፈተሹ። ወንድም ኒኮላዬቭ ለምርመራ የተወሰደ ሲሆን በኋላ ላይ ተለቀቀ

  6. መጋቢት 31, 2021

    በኒኮላዬቭ ላይ ክስ ተመሠረተበት

አጭር መግለጫ

ወንድም ኒኮላዬቭን ጨምሮ በሩሲያና በክራይሚያ ያሉ ታማኝ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በይሖዋ በመታመናቸው እንደሚባረኩ እርግጠኞች ነን።—ኤርምያስ 17:7