በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ቭላዲሚር ቡኪን፣ ወንድም ሚክሃይል ቡርኮቭ፣ ወንድም ቫሊሪ ስላሽችዮቭ እና ወንድም ሰርጌ ዩፌሮቭ

ጥር 26, 2022 | የታደሰው፦ ሰኔ 27, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | በቲንዳ የሚኖሩ ወንድሞች ሌሎችን መርዳታቸውና በይሖዋ መታመናቸው እንዲጸኑ ረድቷቸዋል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | በቲንዳ የሚኖሩ ወንድሞች ሌሎችን መርዳታቸውና በይሖዋ መታመናቸው እንዲጸኑ ረድቷቸዋል

ሰኔ 23, 2023 በአሙር ክልል የሚገኘው የቲንዲንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ቭላዲሚር ቡኪን፣ ሚክሃይል ቡርኮቭ፣ ቫሊሪ ስላሽችዮቭ እና ሰርጌ ዩፌሮቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሚክሃይል የስድስት ዓመት ከሁለት ወር እስራት ተፈርዶበታል። ቭላዲሚር፣ ቫሊሪ እና ሰርጌ ደግሞ የስድስት ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈርዶባቸዋል። አራቱም ወንድሞች ወዲያውኑ ወህኒ ወርደዋል።

ታኅሣሥ 27, 2022 የአሙር ክልላዊ ፍርድ ቤት በወንድም ቭላዲሚር ቡኪን፣ ሚክሃይል ቡርኮቭ፣ ቫሊሪ ስላሽችዮቭ እና ሰርጌ ዩፌሮቭ ላይ የተላለፈውን ብይን በመሻር ክሳቸው ዳግመኛ እንዲታይ ወስኗል። ወንድሞች ከእስር የተለቀቁ ሲሆን ክሳቸው ዳግመኛ የሚታይበትን ጊዜ እየተጠባበቁ ነው። ሆኖም ክልሉን ለቅቀው እንዳይወጡ ክልከላ ተጥሎባቸዋል።

ጥቅምት 25, 2022 በአሙር ክልል የሚገኘው የቲንዲንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በቭላዲሚር፣ በሚክሃይል፣ በቫሊሪ እና በሰርጌ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ቭላዲሚር፣ ቫሊሪ እና ሰርጌ እያንዳንዳቸው የስድስት ዓመት ተኩል እስራት ተፈርዶባቸዋል። ሚክሃይል የስድስት ዓመት ከሁለት ወር እስራት ተፈርዶበታል። አራቱም ከፍርድ ቤት ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል።

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 17, 2019

    ሕግ አስከባሪ አካላት የአራቱን ወንድሞች ቤት ጨምሮ በአካባቢው የሚኖሩ ስምንት የይሖዋ ምሥክር ቤተሰቦችን ቤቶች በረበሩ

  2. ኅዳር 18, 2019

    መርማሪዎች አራቱንም ወንድሞች በጽንፈኝነት ወንጀል ከሰሷቸው። ወንድሞች አካባቢውን ለቀው እንዳይሄዱ ተከለከሉ

  3. ሐምሌ 26, 2021

    ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለውድ ወንድሞቻችንና ለታማኝ አገልጋዮቹ በሙሉ “ታማኝ ፍቅር” ማሳየቱን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—ዘፍጥረት 39:21