በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከላይ፦ ወንድም ዬቭጌኒ ቦችኮ፣ ቭላድሚር ኮሌስኒኮቭ እና አሌክሴ ሹብኒኮቭ

ከታች፦ ወንድም ቪታሊ ኡሻኮቭ እና ቫለሪ ቬችካዬቭ

የካቲት 13, 2024
ሩሲያ

ይሖዋን ማገልገል በሚያስገኘው ክብር ላይ አተኩረዋል

ይሖዋን ማገልገል በሚያስገኘው ክብር ላይ አተኩረዋል

በክራስኖዳር ግዛት የሚገኘው የቭይሴልኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ዬቭጌኒ ቦችኮ፣ ቭላድሚር ኮሌስኒኮቭ፣ አሌክሴ ሹብኒኮቭ፣ ቪታሊ ኡሻኮቭ እና ቫለሪ ቬችካዬቭ ክስ ላይ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለእነዚህ ወንድሞችም ሆነ የእሱን ድጋፍ ለሚሹት ሁሉ ደስታና ብርታት መስጠቱን እንደሚቀጥል አንጠራጠርም።​—መዝሙር 141:8

የክሱ ሂደት

  1. የካቲት 11, 2022

    ዬቭጌኒ፣ አሌክሴ፣ ቪታሊ እና ቫለሪ የክስ ፋይል ተከፈተባቸው

  2. የካቲት 13, 2022

    ቤቶቻቸው ተፈተሹ። ዬቭጌኒ፣ አሌክሴ እና ቪታሊ ምርመራ ተደረገባቸው። ቪታሊ ጣቢያ እንዲቆይ ተደረገ

  3. የካቲት 15, 2022

    ቪታሊ ማረፊያ ቤት ገባ

  4. የካቲት 16, 2022

    ዬቭጌኒ እና አሌክሴ የጉዞ ገደብ ተጣለባቸው

  5. የካቲት 18, 2022

    ቫለሪ የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  6. የካቲት 21, 2022

    ቭላድሚር የክስ ፋይል ተከፈተበት

  7. መጋቢት 15, 2022

    ቭላድሚር የጉዞ ገደብ ተጣለበት። ክሳቸው በአንድ መዝገብ ተጠቃለለ

  8. መስከረም 8, 2022

    ቪታሊ ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ፤ ከዚያም የቁም እስረኛ ተደረገ

  9. ጥቅምት 10, 2022

    ቪታሊ ከቁም እስር ተፈታ፤ ከዚያም የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  10. ግንቦት 31, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ