መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ኅዳር 2012

ይህ እትም የይሖዋን ስም፣ ዓላማና ሕግ ከፍ አድርገን መመልከት የሚኖርብን ለምን እንደሆነ ያብራራል። በተጨማሪም እውነተኛ ክርስቲያኖች ትሑትና ይቅር ባይ መሆናቸው አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ይገልጻል።

“ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ”

የዳዊትን ምሳሌ በመከተል የይሖዋን አመለካከት ግምት ውስጥ ማስገባት የምንችለው እንዴት ነው?

የእነሱ ትርፍ የሌሎችን ጉድለት ሸፈነ

የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች የተቸገሩትን ለመርዳት በየወሩ የተወሰነ መጠን ያለው ገንዘብ ‘ያስቀምጡ’ ነበር። እኛም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ኢየሱስ በትሕትና ረገድ አርዓያ ትቷል

ኢየሱስ ክርስቶስ ትሑት በመሆን ረገድ ከተወው ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?

ራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ የመመልከት መንፈስ አዳብሩ

ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ትሕትና ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ኢየሱስ የነጠላነት ስጦታን አስመልክቶ የተናገረው ሐሳብ ምን ትርጉም አለው?

የይሖዋ ይቅር ባይነት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

ይሖዋ በጥንት ዘመን ኃጢአት የሠሩ ሰዎችን የያዘበት መንገድ ይቅር ለማለት ዝግጁ መሆኑን ያስተምረናል።

እርስ በርስ በነፃ ይቅር ተባባሉ

ይሖዋ ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆነ አምላክ ነው። በዚህ ረገድ የይሖዋን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

‘እስከ ዛሬ ተሰምቶ የማያውቅ ግሩም መልእክት’

በ1926 የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች (በወቅቱ የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠሩበት ስም ነው) በአራት የካናዳ ከተሞች ውስጥ የራሳቸው የሬዲዮ ጣቢያዎች ነበሯቸው።