ንቁ! የካቲት 2015 | መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ ይጠቅማል?

ጥንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም ጠቃሚ የሆኑ አራት የመጽሐፍ ቅዱስ እሴቶችን ተመልከት።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ ይጠቅማል?

ሂልተን የወላጆቹን ቤት ለቅቆ ሲወጣ፣ ወላጆቹ ፈጽሞ ሊሻሻል እንደማይችል አስበው ነበር። ከ12 ዓመታት በኋላ ወደ ቤቱ ሲመለስ ግን በጣም ተሻሽሎ ስለነበር ወላጆቹ እሱ መሆኑን ማመን ከበዳቸው። ሂልተንን የለወጠው ምንድን ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ሐቀኝነት

ራኬል ጉቦ ብትቀበል ኖሮ የገንዘብ ጥቅም ማግኘት ትችል ነበር፤ ሆኖም እንዲህ ያለውን ነገር ባለመቀበሏ ከገንዘብ የበለጠ ነገር እንዳገኘች ይሰማታል።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ራስን መግዛት

ካስያስ የተባለ ግልፍተኛ የነበረ ሰው ቁጣውን መቆጣጠር እንዲችል የረዳው ምንድን ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ታማኝነት

አንዲት ሴት፣ ለባለቤቷ ታማኝ መሆኗ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የተማረችው ብዙ ችግር ከደረሰባት በኋላ ነበር። ታዲያ ትዳሯን ልትታደገው ትችል ይሆን?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ፍቅር

ፍቅር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል፤ ቃሉ ብዙውን ጊዜ የተሠራበት ግን ተቃራኒ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚኖረውን የፍቅር ዓይነት ለማመልከት አይደለም።

ከዓለም አካባቢ

የዜናው ትኩረት—ጤና

መጽሐፍ ቅዱስ ከጤና ጋር በተያያዘም ትክክለኛ መረጃ የያዘ መጽሐፍ እንደሆነ በቅርብ የወጡ የዜና ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

ጥበብ ጥበቃ ያስገኛል

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘው “የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ ድኻው ግን ሥጋት የለበትም” የሚለው አባባል ምን ትርጉም አለው?

ለቤተሰብ

ልጅህ ስለ ሞት ሲጠይቅህ

ልጆች ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚያነሱትን ጥያቄ እንዴት መመለስ እንደምትችል እንዲሁም የቅርብ ሰው ሲሞትባችሁ ልጆች ሐዘኑን እንዲቋቋሙ መርዳት የምትችለው እንዴት እንደሆነ የሚገልጹ አራት ነጥቦችን አንብብ።

ቃለ ምልልስ

አንድ ቄስ ይከተለው የነበረውን ሃይማኖት የተወው ለምንድን ነው?

አንቶንዮ ዴላ ጋታ አምላክን ለመፈለግ ስላደረገው ጥረት እንዲሁም በመጨረሻ ከአምላክ ጋር መቀራረብ የቻለው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መሲሑ

መሲሑ ዓላማውን ሙሉ በሙሉ አከናውኖ ሳይጨርስ እንደሚሞት መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ ተናግሯል፤ ይህን ታውቅ ነበር?

ንድፍ አውጪ አለው?

ወደ ላይ የሚቀለበስ ክንፍ ያላቸው ወፎች

የአውሮፕላን መሐንዲሶች የእነዚህን ወፎች ክንፍ ንድፍ በመኮረጅ የሠሩት ነገር በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 7,600 ሚሊዮን ሊትር የሚሆን ነዳጅ እንዳይባክን አስተዋጽኦ አድርጓል።

በተጨማሪም . . .

ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን

በኢንተርኔት አማካኝነት ከጓደኞችህ ጋር ስትገናኝ አስተዋይ ሁን።

መስጠት ያስደስትሃል

ለሌሎች መስጠት የምትችልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። ምሳሌ መጥቀስ ትችላለህ?