መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መጋቢት 2015

ይህ እትም ከግንቦት 4 እስከ 31, 2015 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

የሕይወት ታሪክ

ይበልጥ የሚያረካ ሙያ አገኘን

ዴቪድ እና ግዌን ካርትራይት በአንድ ወቅት ባሌ ዳንስ አብረው ይደንሱ ነበር፤ አሁን ግን እግሮቻቸውን የሚጠቀሙት ለዳንስ ሳይሆን ለሌላ የተሻለ ነገር ነው።

‘ይህ የአንተ ፈቃድ ነው’

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጽሑፎቻችን የመጽሐፍ ቅዱስን ዘገባዎችን ይበልጥ ግልጽና ቀላል በሆነ መንገድ ማብራራት የጀመሩት ለምንድን ነው?

‘ነቅታችሁ ትጠብቃላችሁ?’

ኢየሱስ ስለ አሥሩ ደናግል ከተናገረው ምሳሌ ጋር በተያያዘ ያገኘነውን የተሻሻለ ግንዛቤ አንብብ፤ ማብራሪያው ከምሳሌው በምናገኘው ቀላልና ወቅታዊ ትምህርት ላይ ያተኮረ ነው።

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ቀደም ሲል ጽሑፎቻችን ጥላ ስለሚሆኑ ነገሮችና ስለ እውነተኛዎቹ ነገሮች ብዙ ጊዜ ይጠቅሱ ነበር፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን እንዲህ ዓይነቱ ማብራሪያ እየቀረ መጥቷል። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?

ከታላንቱ ምሳሌ ትምህርት ማግኘት

ይህ ርዕስ ኢየሱስ ስለ ታላንቱ ከተናገረው ምሳሌ ጋር በተያያዘ ያገኘነውን የተሻሻለ ግንዛቤ የያዘ ነው።

የክርስቶስን ወንድሞች በታማኝነት መደገፍ

ክርስቶስ በግ እንደሆኑ የሚፈርድላቸው ሰዎች ወንድሞቹን የሚደግፉት እንዴት ነው?

“በጌታ ብቻ” ማግባት—በዘመናችንም ይቻላል?

የአምላክን ምክር በሥራ ላይ ለማዋል ቁርጥ ውሳኔ ያደረጉ ሰዎች እሱን የሚያስደስቱ ከመሆኑም ሌላ መንፈሳዊ በረከት ያገኛሉ።