መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ኅዳር 2015

ይህ እትም ከታኅሣሥ 28, 2015 እስከ ጥር 31, 2016 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

ልጃችሁ ይሖዋን እንዲያገለግል አሠልጥኑት—ክፍል 1

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምር ያሳያቸው ሦስት ባሕርያት ወላጆች እናንተም ልጆቻችሁን በማሠልጠን ረገድ ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆኑ ይረዷችኋል።

ልጃችሁ ይሖዋን እንዲያገለግል አሠልጥኑት—ክፍል 2

በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ልጃችሁን በጉርምስና ወቅት በመንፈሳዊ እድገት እንዲያደርግ ልትረዱት የምትችሉት እንዴት ነው?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የጥንቷ ኢያሪኮ ድል የተደረገችው ለረጅም ጊዜ ሳትከበብ ለመሆኑ ምን ማስረጃ አለ?

ለይሖዋ ለጋስነት አድናቆት አሳዩ

መጽሐፍ ቅዱስ ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንንና ጥሪታችንን ለመስጠት ሊያነሳሳን ስለሚገባው ተገቢ የሆነ አመለካከትና ተገቢ ስላልሆነ አመለካከት ይገልጻል።

ይሖዋ የፍቅር አምላክ ነው

ይሖዋ ለሰው ዘር ፍቅሩን ያሳየው እንዴት ነው?

‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ትወዳለህ?’

ኢየሱስ የሰጠውን ትእዛዝ በትዳርህ ውስጥ፣ በጉባኤና በስብከት ሥራህ ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ።

በመንግሥቱ አገዛዝ ሥር ያሳለፍነው መቶ ዓመት!

ስለ አምላክ መንግሥት ለመስበክ በየትኞቹ ሦስት መስኮች ታጥቀናል?

ከታሪክ ማኅደራችን

“ከፀሐይ በታች ምንም ነገር ሊያግዳችሁ አይገባም!”

በ1930ዎቹ በፈረንሳይ የነበሩ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የቅንዓትና የጽናት ምሳሌ ናቸው።