መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 5 2016 | ማጽናኛ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?

ሁላችንም በተለይ ችግር በሚያጋጥመን ወቅት አምላክ የሚሰጠው ማጽናኛ ያስፈልገናል። ይህ ተከታታይ ርዕስ ችግሮችና ተፈታታኝ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ አምላክ የሚያጽናናን እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ሁላችንም መጽናኛ ያስፈልገናል

የምትወደውን ሰው በሞት ስታጣ ወይም ከጤና፣ ከትዳር ወይም ከሥራ ጋር የተያያዘ ከባድ ችግር ሲያጋጥምህ እርዳታ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

አምላክ የሚያጽናናን እንዴት ነው?

አምላክ መከራ የደረሰባቸውን ሰዎች ለማጽናናት የሚጠቀምባቸው አራት መንገዶች

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ችግር ሲያጋጥመን ማጽናኛ ማግኘት

አንዳንድ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ወቅት ያገኙት እንዴት ነው?

በእምነታቸው ምሰሏቸው

“ውጊያው የይሖዋ ነው”

ዳዊት ጎልያድን እንዲያሸንፍ የረዳው ምንድን ነው?

ዳዊትና ጎልያድ—ታሪኩ እውነት ነው?

አንዳንዶች የዘገባውን እውነተኝነት ይጠራጠራሉ። ለዚህ የሚያበቃ ማስረጃ አላቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል

ሕይወት የመረረውና ዓመፀኛ ሰው ነበርኩ

በሜክሲኮ የሚኖረው ተደባዳቢ በሕይወቱ ላይ ለውጥ እንዲያደርግ የረዳው ምንድን ነው?

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

ከምታስበው የተለየ መልስ ታገኝ ይሆናል።

በተጨማሪም . . .

መጸለይ ለምን አስፈለገ? አምላክ ጸሎቴን ይመልስልኛል?

አምላክ ጸሎትህን ሰምቶ መልስ መስጠቱ በአብዛኛው የተመካው በአንተ ላይ ነው።