መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም የካቲት 2018

ይህ እትም ከሚያዝያ 2 እስከ 29, 2018 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ የተዉትን የእምነትና የታዛዥነት ምሳሌ ተከተሉ

እነዚህ ታማኝ ወንዶች ከእኛ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ፈተናዎች አጋጥመዋቸዋል። ንጹሕ አቋማቸውን ጠብቀው ለመኖር የረዳቸው ምንድን ነው?

የኖኅን፣ የዳንኤልንና የኢዮብን ያህል ይሖዋን ታውቀዋለህ?

እነዚህ ሰዎች ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ማወቅ የቻሉት እንዴት ነው? ይህ እውቀት የጠቀማቸው እንዴት ነው? እኛስ እንደ እነሱ ዓይነት እምነት ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?

የሕይወት ታሪክ

በይሖዋ ዘንድ ሁሉ ነገር ይቻላል

በኪርጊስታን የምትኖር አንዲት ሴት አውቶቡስ ውስጥ የተናገረችው አስገራሚ ሐሳብ የአንድን ባልና ሚስት ሕይወት ለውጧል።

መንፈሳዊ ሰው መሆን—ምን ማለት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ “መንፈሳዊ ሰው” ተለይቶ የሚታወቅባቸውን ምልክቶች እንዲሁም ‘ከዓለማዊ ሰው’ ጋር ምን ልዩነት እንዳለው ይገልጻል።

መንፈሳዊ ሰው በመሆን እድገት ማድረጋችሁን ቀጥሉ!

መንፈሳዊ ሰው ለመሆን የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ብቻ በቂ አይደለም። ሌላ ምን ያስፈልጋል?

ደስታ—ከአምላክ የምናገኘው ግሩም ባሕርይ

በዕለት ተዕለት ሕይወት የሚያጋጥሙ ችግሮች ደስታ እያሳጡህ እንደሆነ ከተሰማህ እንደገና ደስተኛ ለመሆን ምን ማድረግ ትችላለህ?

ከታሪክ ማኅደራችን

የሕዝብ ንግግሮች አየርላንድ ውስጥ ምሥራቹን አስፋፉ

ቻርልስ ቴዝ ራስል በአየርላንድ “ለመሰብሰብ የደረሰ አዝመራ” እንዳለ የተሰማው ለምንድን ነው?