መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ጥር 2019

ይህ እትም ከመጋቢት 4 እስከ ሚያዝያ 7, 2019 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

“እኔ አምላክህ ነኝና አትጨነቅ”

ተፈታታኝ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ እንኳ ተረጋግተን ለመኖር የሚያስችሉንን ሦስት ምክንያቶች ተመልከት።

በጉባኤ መካከል ይሖዋን አወድሱ

በስብሰባዎች ላይ ሐሳብ መስጠት ይከብድሃል? ይህ ርዕስ የምትፈራበትን ምክንያት ለማወቅና ፍርሃትህን ለማሸነፍ ይረዳሃል።

ልብህን መጠበቅ የምትችለው እንዴት ነው?

ሰይጣን ልባችንን ለማጥቃት የሚሞክረው እንዴት ነው? ልባችንን መጠበቅ የምንችለውስ እንዴት ነው?

የጌታ ራት—በሰማይ ስላለው ንጉሣችን የሚያስተምር ቀለል ያለ ዝግጅት

የመታሰቢያው በዓል ኢየሱስ ስላሳየው ትሕትና፣ ድፍረትና ፍቅር ምን ያስተምረናል?

በስብሰባዎች ላይ መገኘታችን ስለ እኛ ምን ይጠቁማል?

ፍቅር፣ ትሕትናና ድፍረት በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት የሚረዱን እንዴት ነው?

አዲስ የበላይ አካል አባል

ስለ ወንድም ኬኔዝ ኩክ የሚገልጽ አጭር መረጃ