መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መጋቢት 2019

ይህ እትም ከግንቦት 6 እስከ ሰኔ 2, 2019 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?

ይሖዋ አምላክን የሚያውቁ አንዳንድ ሰዎች ከመጠመቅ ወደኋላ ይላሉ። እነዚህ ሰዎች ይህን ውሳኔ ማድረግ ከባድ እንዲሆንባቸው የሚያደርጉ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን መወጣት የሚችሉት እንዴት ነው?

የይሖዋን ድምፅ ስሙ

ይሖዋ በዛሬው ጊዜ የሚያናግረን በምን መንገድ ነው? አምላክን መስማታችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?

የሌሎችን ስሜት የምትረዱ ሁኑ

ይሖዋና ኢየሱስ የሌሎችን ስሜት እንደሚረዱ ያሳዩት በየትኞቹ መንገዶች ነው? እኛስ እነሱ የተዉትን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

በአገልግሎት ላይ የምታገኟቸውን ሰዎች ስሜት የምትረዱ ሁኑ

በአገልግሎት ላይ የምናገኛቸውን ሰዎች ስሜት እንደምንረዳ ማሳየት የምንችልባቸው አራት መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ጥሩነት—እንዴት ልታዳብረው ትችላለህ?

ጥሩነት ምንድን ነው? ይህን ባሕርይ ለማዳበር ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?

ይሖዋ “አሜን” ለሚለው ቃል ትልቅ ቦታ ይሰጣል

ብዙዎች በጸሎት መጨረሻ ላይ ‘አሜን’ የማለት ልማድ አላቸው። ለመሆኑ ይህ ቃል ምን ትርጉም አለው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሠራበትስ እንዴት ነው?