መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መጋቢት 2020

ይህ እትም ከግንቦት 4-31, 2020 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

ለይሖዋ ያለህ ፍቅርና አድናቆት ለመጠመቅ ያነሳሳሃል

ለይሖዋ ያለህ ፍቅር ለመጠመቅ ሊያነሳሳህ ይችላል። ይሁንና ወደኋላ እንድትል ሊያደርግህ የሚችለው ምንድን ነው?

ለመጠመቅ ዝግጁ ነህ?

በዚህ ርዕስ ውስጥ የሚገኙት ጥያቄዎች መልስ ውሳኔ ለማድረግ ይረዳሃል።

የሕይወት ታሪክ

“እነሆኝ! እኛን ላኩን!”

ጃክ እና ማሪሊን የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለመጀመር ያነሳሳቸውና ከአዳዲስ ምድቦች ጋር ለመላመድ የረዳቸው ምን እንደሆነ ይናገራሉ።

ለመናገር ትክክለኛው ጊዜ መቼ ነው?

መቼ መናገር፣ መቼ ደግሞ ዝም ማለት እንዳለብን ለማወቅ የሚረዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎችን እንመልከት።

እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ

ኢየሱስ ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ እንደሆነ ተናግሯል። ፍቅር ሰላም ፈጣሪ፣ ከአድልዎ ነፃ እና እንግዳ ተቀባይ እንድንሆን የሚረዳን እንዴት ነው?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

እስራኤላውያን በግብፅ ባሪያ እንደነበሩ የሚያሳይ ማስረጃ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ይገኛል?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአይሁድ የቤተ መቅደስ ፖሊሶች እነማን ነበሩ? ሥራቸውስ ምን ነበር?