በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 21, 2022
ሩሲያ

ቤታቸው የተበረበረባቸውና በጭካኔ የተደበደቡት የኢርኩትስክ የይሖዋ ምሥክሮች ታማኝነታቸውን ጠብቀዋል

ቤታቸው የተበረበረባቸውና በጭካኔ የተደበደቡት የኢርኩትስክ የይሖዋ ምሥክሮች ታማኝነታቸውን ጠብቀዋል

ጥቅምት 4, 2021 በኢርኩትስክ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች ቤታቸው ተበርብሮ ነበር። ሕግ አስከባሪ አካላት በይሖዋ ምሥክሮቹ ላይ የወንጀል ምርመራ በሚያደርጉበት ወቅት የኃይል ጥቃት ፈጽመውባቸዋል። ስድስት የይሖዋ ምሥክሮች በሰላማዊ መንገድ ክርስቲያናዊ እምነታቸውን በማራመዳቸው ምክንያት ብቻ ወደ ማረፊያ ቤት ተልከዋል።