በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?

የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሲሆን የተለያየ ዘር፣ ባሕልና አስተዳደግ ያላቸው ሰዎች ናቸው። እነዚህን ሰዎች አንድ ያደረጋቸው ምንድን ነው?

የአምላክ ፈቃድ ምንድን ነው?

አምላክ የእሱ ፈቃድ በመላው ምድር ላይ እንዲታወቅ ይፈልጋል። የእሱ ፈቃድ ምንድን ነው? በዛሬው ጊዜ ፈቃዱን ለሰዎች እያስተማሩ ያሉትስ እነማን ናቸው?

ትምህርት 1

የይሖዋ ምሥክሮች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው?

ስንት የይሖዋ ምሥክሮችን ታውቃለህ? ስለ እኛ በእርግጠኝነት የምታውቀው ምንድን ነው?

ትምህርት 2

የይሖዋ ምሥክሮች ተብለን የምንጠራው ለምንድን ነው?

በዚህ ስም ለመጠራት የመረጥነው ለምንድን ነው? ሦስት ምክንያቶችን አንብብ።

ትምህርት 3

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ዳግመኛ የተገለጠው እንዴት ነው?

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ትክክለኛ ግንዛቤ እንዳለን እርግጠኞች የሆንነው ለምንድን ነው?

ትምህርት 4

አዲስ ዓለም ትርጉም የተባለውን መጽሐፍ ቅዱስ ያዘጋጀነው ለምንድን ነው?

ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

ትምህርት 5

ከክርስቲያናዊ ስብሰባዎቻችን ምን ጥቅም ታገኛለህ?

መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናትና እርስ በርስ ለመበረታታት እንሰበሰባለን። አንተም በስብሰባዎቻችን ላይ እንድትገኝ ጋብዘንሃል!

ትምህርት 6

ከክርስቲያን ባልንጀሮቻችን ጋር መቀራረባችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?

የአምላክ ቃል፣ ክርስቲያኖች እንዲቀራረቡ ያበረታታል። እንዲህ ያለው መቀራረብ ምን ጥቅም አለው?

ትምህርት 7

ስብሰባዎቻችን ምን ይመስላሉ?

ስብሰባዎቻችን ምን እንደሚመስሉ ማወቅ ትፈልጋለህ? በዚያ በሚሰጠው ግሩም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንደምትደሰት እርግጠኞች ነን።

ትምህርት 8

ስብሰባ ስንሄድ ለአለባበሳችን ልዩ ትኩረት የምንሰጠው ለምንድን ነው?

የምንለብሰው ልብስ ዓይነት አምላክን ያሳስበዋል? ከአለባበስና ከአጋጌጥ ጋር በተያያዘ የምንከተላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች የትኞቹ እንደሆኑ ተመልከት።

ትምህርት 9

ለስብሰባዎች ጥሩ አድርገን መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

ከስብሰባዎች በሚገባ መጠቀም ከፈለግህ አስቀድመህ ዝግጅት አድርግ።

ትምህርት 10

የቤተሰብ አምልኮ ምንድን ነው?

ይህ ዝግጅት ወደ አምላክ ለመቅረብና ከቤተሰብህ ጋር ያለህን ዝምድና ለማጠናከር የሚረዳህ እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ትምህርት 11

በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ የምንገኘው ለምንድን ነው?

በዓመት ሦስት ጊዜ አንድ ላይ የምንሰበሰብበት ለየት ያለ ፕሮግራም አለን። እነዚህ ስብሰባዎች የሚጠቅሙህ እንዴት ነው?

ትምህርት 12

የመንግሥቱን ምሥራች የምንሰብከው እንዴት ነው?

ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት የተወውን ምሳሌ እንከተላለን። ኢየሱስ ለመስበክ ከተጠቀመባቸው ዘዴዎች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው?

ትምህርት 13

አቅኚነት ምንድን ነው?

አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮች በወር ውስጥ 30፣ 50 ወይም ከዚያ የበለጠ ሰዓት በስብከቱ ሥራ ላይ ያሳልፋሉ። እንዲህ እንዲያደርጉ የሚያነሳሳቸው ምንድን ነው?

ትምህርት 14

አቅኚዎች ምን ዓይነት የትምህርት አጋጣሚዎች ተከፍተውላቸዋል?

ሙሉ ጊዜያቸውን የመንግሥቱን መልእክት በመስበክ ለሚያሳልፉ አቅኚዎች ምን ዓይነት ሥልጠናዎች ተዘጋጅተዋል?

ትምህርት 15

ሽማግሌዎች ጉባኤውን የሚያገለግሉት እንዴት ነው?

ሽማግሌዎች ጉባኤውን የሚመሩ በመንፈሳዊ የጎለመሱ ወንዶች ናቸው። ሽማግሌዎች ሌሎችን የሚረዱት በምን መንገድ ነው?

ትምህርት 16

የጉባኤ አገልጋዮች ምን ሚና ይጫወታሉ?

የጉባኤ አገልጋዮች በጉባኤ ውስጥ ያሉት ሥራዎች በአግባቡ እንዲከናወኑ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። የሚያከናውኑት ሥራ ተሰብሳቢዎችን የሚጠቅመው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

ትምህርት 17

የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚጠቅሙን እንዴት ነው?

የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ጉባኤዎችን የሚጎበኙት ለምንድን ነው? ከዚህ ጉብኝት ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ትምህርት 18

አስቸጋሪ ሁኔታ ያጋጠማቸውን ወንድሞቻችንን የምንረዳው እንዴት ነው?

አደጋ ሲከሰት በአደጋው ለተጎዱ ሰዎች ሰብዓዊና መንፈሳዊ እርዳታ ለመስጠት ፈጣን እርምጃ እንወስዳለን። ይህን የምናደርገው እንዴት ነው?

ትምህርት 19

ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?

ኢየሱስ በተገቢው ጊዜ መንፈሳዊ ምግብ የሚያቀርብ ባሪያ እንደሚሾም ቃል ገብቷል። ይህ ባሪያ ይህን እያደረገ ያለው እንዴት ነው?

ትምህርት 20

በዛሬው ጊዜ የበላይ አካሉ ሥራውን የሚያከናውነው እንዴት ነው?

በመጀመሪያው መቶ ዘመን የተወሰኑ ሽማግሌዎችና ሐዋርያት የክርስቲያን ጉባኤ የበላይ አካል ሆነው አገልግለዋል። በዛሬው ጊዜስ?

ትምህርት 21

ቤቴል ምንድን ነው?

ቤቴል በጣም አስፈላጊ የሆነ ሥራ የሚከናወንበት ልዩ ቦታ ነው። በዚያ የሚሠሩት እነማን እንደሆኑ ማወቅ ትፈልጋለህ?

ትምህርት 22

በቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ምን ዓይነት ሥራ ይከናወናል?

እንግዶች ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንን መጎብኘት ይችላሉ። አንተም ተጋብዘሃል!

ትምህርት 23

ጽሑፎቻችን የሚዘጋጁትና የሚተረጎሙት እንዴት ነው?

ጽሑፎቻችን ከ750 በሚበልጡ ቋንቋዎች ይገኛሉ። እንዲህ ያለ ጥረት የምናደርገው ለምንድን ነው?

ትምህርት 24

በዓለም ዙሪያ ለምናከናውነው ሥራ የሚያስፈልገውን ገንዘብ የምናገኘው እንዴት ነው?

ከመዋጮ ጋር በተያያዘ ድርጅታችንን ከሌሎች ሃይማኖቶች ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

ትምህርት 25

የስብሰባ አዳራሾችን የምንሠራው ለምንድን ነው? የሚገነቡትስ እንዴት ነው?

ለአምልኮ የምንሰበሰብበትን ቦታ የስብሰባ አዳራሽ ብለን የምንጠራው ለምንድን ነው? ቀለል ባለ መንገድ የተሠሩት እነዚህ አዳራሾች ጉባኤዎቻችንን የሚጠቅሙት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

ትምህርት 26

የስብሰባ አዳራሻችንን በመንከባከብ ረገድ አስተዋጽኦ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ንጹሕና በሥርዓት የተያዘ የስብሰባ አዳራሽ ለአምላክ ክብር ያመጣል። የስብሰባ አዳራሹን ንጽሕና ለመጠበቅ ምን ዝግጅት ተደርጓል?

ትምህርት 27

ከስብሰባ አዳራሹ ቤተ መጻሕፍት ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለህን እውቀት ለማሳደግ ምርምር ማድረግ ትፈልጋለህ? በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ ያለውን ቤተ መጻሕፍት ተጠቀም!

ትምህርት 28

በድረ ገጻችን ላይ ምን መረጃ ማግኘት ይቻላል?

ስለ እኛ ይበልጥ ማወቅና ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችህ መልስ ማግኘት ትችላለህ።

አንተስ የይሖዋን ፈቃድ ታደርጋለህ?

ይሖዋ አምላክ ይወድሃል። አንተስ በዕለት ተዕለት ሕይወትህ የእሱን ፈቃድ ማድረግ እንደምትፈልግ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?