ወደ ይሖዋ ቅረብ

አምላክ ወደ እሱ እንድትቀርብ ጋብዞሃል። ይህ መጽሐፍ፣ ይህን ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ ያሳይሃል።

መቅድም

ከይሖዋ አምላክ ጋር ፈጽሞ የማይበጠስ ወዳጅነት መመሥረት ትችላለህ።

ምዕራፍ 1

“እነሆ፣ አምላካችን ይህ ነው!”

ሙሴ የአምላክን ስም እያወቀ ስሙን የጠየቀው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 2

በእርግጥ ‘ወደ አምላክ መቅረብ’ ትችላለህ?

የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ አምላክ ጋብዞናል፤ ደግሞም ተስፋ ሰጥቶናል።

ምዕራፍ 3

“ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው”

መጽሐፍ ቅዱስ ቅድስናን ከውበት ጋር የሚያያይዘው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 4

‘ይሖዋ ኃይሉ ታላቅ ነው’

አምላክ ያለው ኃይል እንድንፈራው ሊያደርገን ይገባል? ትክክለኛው መልስ ይገባልም፣ አይገባምም የሚል ነው።

ምዕራፍ 5

‘የሰማይና የምድር ፈጣሪ’—ለመፍጠር የሚጠቀምበት ኃይል

ግዙፍ ከሆነችው ፀሐይ አንስቶ ኢምንት እስከሆነችው ሃሚንግበርድ የተባለችው ወፍ፣ የአምላክ ፍጥረታት ስለ አምላክ አስፈላጊ ትምህርት ያስተምሩናል።

ምዕራፍ 6

‘ኃያል ተዋጊ የሆነው ይሖዋ’—ለማጥፋት የሚጠቀምበት ኃይል

“የሰላም አምላክ” መለኮታዊ ጦርነት የሚያካሂደው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 7

‘መጠጊያችን የሆነው አምላክ’—ለመጠበቅ የሚጠቀምበት ኃይል

አምላክ ሕዝቡን የሚጠብቀው በሁለት መንገዶች ነው፤ አንደኛው ግን ከሁሉ በላይ አስፈላጊ ነው።

ምዕራፍ 8

‘ሁሉንም ነገር አዲስ የሚያደርገው’ ይሖዋ—ለማደስ የሚጠቀምበት ኃይል

ይሖዋ በአሁኑ ጊዜ ንጹሑን አምልኮ መልሶ አቋቁሟል። ወደፊትስ ምን ነገር ያድሳል?

ምዕራፍ 9

‘ክርስቶስ የአምላክ ኃይል ነው’

ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸማቸው ተአምራት እንዲሁም ያስተማራቸው ትምህርቶች ስለ ይሖዋ ምን ይነግሩናል?

ምዕራፍ 10

በኃይል አጠቃቀም ረገድ “አምላክን የምትመስሉ ሁኑ”

አለኝ ብለህ ከምታስበው በላይ ኃይል ወይም ሥልጣን ይኖርህ ይሆናል፤ ይሁንና ይህን ኃይልህን በአግባቡ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 11

“መንገዶቹ ሁሉ ፍትሕ ናቸው”

የአምላክ ፍትሕ ተወዳጅ ባሕርይ የሆነው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 12

“አምላክ ፍትሕ ያዛባል?”

ይሖዋ የፍትሕ መጓደልን የሚጠላ ከሆነ ዓለም በግፍ የተሞላው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 13

“የይሖዋ ሕግ ፍጹም ነው”

ፍቅር የሚንጸባረቅበት የሕግ ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 14

ይሖዋ “በብዙ ሰዎች ምትክ . . . ቤዛ” አዘጋጀ

ቀላል ሊመስል ቢችልም ከምናስበው በላይ አስገራሚ የሆነው ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወደ አምላክ እንድትቀርብ ይረዳሃል።

ምዕራፍ 15

ኢየሱስ ‘ፍትሕን በምድር ላይ ያሰፍናል’

ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ፍትሕ ያሰፈነው እንዴት ነው? ዛሬስ ፍትሕ እያሰፈነ ያለው እንዴት ነው? ወደፊትስ የሚያሰፍነው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 16

‘ፍትሕን በማድረግ’ ከአምላክ ጋር መሄድ

ፍትሕ፣ ትክክል እና ስህተት ስለሆነው ነገር ያለንን አመለካክት እንዲሁም ሌሎችን የምንይዝበትን መንገድ ያካትታል።

ምዕራፍ 17

‘የአምላክ ጥበብ እንዴት ጥልቅ ነው!’

የአምላክ ጥበብ ከእውቀቱና ከማስተዋሉ ጭምር የላቀ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 18

‘በአምላክ ቃል’ ላይ የተንጸባረቀ ጥበብ

አምላክ መልእክቱን በጽሑፍ ለማስፈር በሰዎች የተጠቀመው ለምንድን ነው? በመጽሐፉ ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ሳያካትት የቀረውስ ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 19

“በቅዱስ ሚስጥር የተገለጠው . . . የአምላክ ጥበብ”

አምላክ ደረጃ በደረጃ የገለጠው ቅዱስ ሚስጥር ምንድን ነው?

ምዕራፍ 20

“ጥበበኛ ልብ አለው”—ግን ትሑት ነው

የአጽናፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ጌታ ትሑት የሆነው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 21

ኢየሱስ ‘ከአምላክ የመጣውን ጥበብ’ ገልጧል

ኢየሱስ ያስተማረበት መንገድ በጣም አስደናቂ ከመሆኑ የተነሳ በአንድ ወቅት እሱን ይዘው እንዲመጡ የታዘዙ ወታደሮች ባዶ እጃቸውን ተመልሰዋል!

ምዕራፍ 22

‘ከሰማይ የሆነውን ጥበብ’ በአኗኗርህ እያንጸባረቅህ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ አምላካዊ ጥበብ ለማዳበር የሚረዱህን አራት ነጥቦች ያብራራል።

ምዕራፍ 23

‘እሱ አስቀድሞ ወዶናል’

“አምላክ ፍቅር ነው” የሚለው መግለጫ ትርጉሙ ምንድን ነው?

ምዕራፍ 24

“ከአምላክ ፍቅር ሊለየን” የሚችል ነገር የለም

በአምላክ ፊት ዋጋ የላችሁም የሚለውን ውሸት አትመኑ።

ምዕራፍ 25

‘ከአንጀት የሚራራልን አምላካችን’

አምላክ ለአንተ ያለው ስሜት አንዲት እናት ለልጇ ካላት ስሜት ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 26

‘ይቅር ለማለት ዝግጁ’ የሆነ አምላክ

አምላክ ሁሉንም ነገር የሚያስታውስ ከሆነ ይቅር ካለን በኋላ በደላችንን የሚረሳው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 27

“ጥሩነቱ ምንኛ ታላቅ ነው!”

የአምላክ ጥሩነት ምን ያካትታል?

ምዕራፍ 28

“አንተ ብቻ ታማኝ ነህ”

ይሖዋ እምነት የሚጣልበት አምላክ ነው፤ ታማኝነቱ ግን ከዚህም የላቀ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 29

‘የክርስቶስን ፍቅር ማወቅ’

ኢየሱስ የይሖዋን ፍቅር ያንጸባረቀባቸው ሦስት መንገዶች።

ምዕራፍ 30

“በፍቅር መመላለሳችሁን ቀጥሉ”

አንደኛ ቆሮንቶስ ፍቅር ልናሳይ የምንችልባቸውን የተለያዩ መንገዶች ይነግረናል።

ምዕራፍ 31

“ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል”

ራስህን መጠየቅ ያለብህ አስፈላጊ ጥያቄ የትኛው ነው? ለጥያቄውስ ምን መልስ ትሰጥ ይሆን?