ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ

ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው ለሰዎች የማንበብ እንዲሁም የንግግርና የማስተማር ችሎታህን ለማሻሻል እንዲረዳህ ታስቦ ነው።

የበላይ አካሉ መልእክት

ለሰው ልጆች ከተሰጡት መልእክቶች ሁሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን መልእክት የማስተላለፍ መብት አለን።

ጥናት 1

ጥሩ መግቢያ

አንድ ጥሩ መግቢያ ሦስት ዓላማዎችን ያሳካል።

ጥናት 2

በጭውውት መልክ መናገር

በጭውውት መልክ መናገር፣ አድማጮችህ ዘና ብለው እንዲያዳምጡና መልእክትህን እንዲቀበሉ ይረዳቸዋል።

ጥናት 3

ጥያቄዎችን መጠቀም

አድማጮችህ ለመልእክቱ ጉጉት እንዲያድርባቸውና ዋና ዋና ነጥቦችን ለማጉላት ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ተጠቀም።

ጥናት 4

ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ

አንድን ጥቅስ ከማንበብህ በፊት አድማጮችህ ለጥቅሱ ጉጉት እንዲያድርባቸው ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነ አስብ።

ጥናት 5

ጥርት ያለ ንባብ

ጥርት ያለ ንባብ ስለ ይሖዋ የሚገልጸውን እውነት ለሌሎች ለማስተላለፍ በጣም አስፈላጊ ነው።

ጥናት 6

የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ማድረግ

አድማጮችህ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ባሉት ቃላትና በምታብራራው ዋና ነጥብ መካከል ያለውን ዝምድና ማስተዋል እንዲችሉ እርዳቸው።

ጥናት 7

ትክክለኛ እና አሳማኝ መረጃ

ትክክለኛ እና አሳማኝ መረጃ ማቅረብህ አድማጮችህ ትክክለኛ መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ ለመርዳት ወሳኝ ነው።

ጥናት 8

ትምህርት አዘል ምሳሌዎች

የአድማጮችህን ትኩረት የሚስቡና ዋናውን ነጥብ ለማጉላት የሚረዱ ቀለል ያሉ ምሳሌዎችን በመጠቀም ንግግርህ ማራኪ እንዲሆን ማድረግ ትችላለህ።

ጥናት 9

በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ማስተማር

አድማጮችህ ትምህርቱን በሚገባ ማስታወስ እንዲችሉ በሚታዩ ነገሮች ተጠቅመህ አስተምር።

ጥናት 10

ድምፅን መለዋወጥ

የድምፅህን መጠን፣ ውፍረትና ቅጥነት እንዲሁም የምትናገርበትን ፍጥነት በመለዋወጥ የአድማጮችህን ስሜት ለመቀስቀስና እነሱን ለተግባር ለማነሳሳት ጥረት አድርግ።

ጥናት 11

በጋለ ስሜት መናገር

በጋለ ስሜት መናገርህ ጉዳዩን ከልብ እንደምታምንበት ያሳያል፤ አድማጮችህ በትኩረት እንዲከታተሉህም ይረዳል።

ጥናት 12

ወዳጃዊ ስሜትና አሳቢነት ማሳየት

ከልብ በመነጨ ስሜት የምትናገር ከሆነ አድማጮችህ እንደምታስብላቸው ይሰማቸዋል።

ጥናት 13

የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ

አድማጮችህ፣ ትምህርቱ ከሕይወታቸው ጋር እንዴት እንደሚያያዝ እንዲሁም የተማሩትን ነገር እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ እንዲያስተውሉ እርዳቸው።

ጥናት 14

ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ

አድማጮችህ ንግግርህን በትኩረት እንዲከታተሉ እርዳቸው፤ በተጨማሪም እያንዳንዱ ዋና ነጥብ ከንግግርህ ዓላማና ጭብጥ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ግልጽ አድርግላቸው።

ጥናት 15

በእርግጠኝነት መናገር

በእርግጠኝነት እና የምትናገረው ነገር በጣም አስፈላጊ መሆኑን ከልብህ እንደምታምን በሚያሳይ መንገድ ተናገር።

ጥናት 16

አዎንታዊና የሚያበረታታ

ነቃፊ ከመሆን ይልቅ የሚያበረታታ ንግግር ለማቅረብ ጥረት አድርግ። አድማጮችህ በአምላክ ቃል ውስጥ በሚገኘው መንፈስን የሚያድስ እውነት ላይ እንዲያተኩሩ አድርግ።

ጥናት 17

በቀላሉ የሚገባ

አድማጮችህ መልእክቱን በደንብ መረዳት እንዲችሉ እርዳቸው። ቁልፍ የሆኑ ነጥቦችን በደንብ አብራራ።

ጥናት 18

ግንዛቤ የሚያሰፋ

አድማጮችህ ርዕሰ ጉዳዩን እንዲያስቡበት ብሎም ጠቃሚ ትምህርት እንዲያገኙ አድርግ።

ጥናት 19

የአድማጮችን ልብ ለመንካት መጣር

አድማጮች ለአምላክ እንዲሁም ለቃሉ ለመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር እንዲያዳብሩ እርዳቸው።

ጥናት 20

ግቡን የሚመታ መደምደሚያ

ግቡን የሚመታ መደምደሚያ፣ አድማጮችህ ትምህርቱን አምነው እንዲቀበሉና እርምጃ እንዲወስዱ ያነሳሳቸዋል።

የምታደርገውን መሻሻል ገምግም

የማንበብና የማስተማር ችሎታህን ለማሻሻል በምትጥርበት ጊዜ የምታደርገውን መሻሻል ገምግም።

እነዚህንስ አይተሃቸዋል?

ተከታታይ ቪዲዮዎች

ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ—ቪዲዮዎች

የማስተማር እንዲሁም ለሰዎች የማንበብ ችሎታህን ለማሻሻል የሚያስፈልጉህን ክህሎቶች ለማዳበር እነዚህን ቪዲዮዎች ተጠቀም።