በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

የእልባት አጠቃቀም—አንድሮይድ

የእልባት አጠቃቀም—አንድሮይድ

JW Library ላይ እልባት ለማድረግ የሚያስችለው ገጽታ በታተመው ጽሑፍ ላይ ንባብህን ያቆምክበትን ቦታ ለማስታወስ ከምታደርገው እልባት ጋር ተመሳሳይ ነው። በJW Library ላይ የሚገኘው እያንዳንዱ ጽሑፍ 10 ዓይነት እልባቶች አሉት።

እልባት ለመጠቀም እነዚህን መመሪያዎች ተከተል፦

 አዲስ እልባት ማድረግ

በአንድ ርዕስ፣ ምዕራፍ፣ አንቀጽ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ እልባት ማድረግ ትችላለህ።

በአንድ ርዕስ ወይም ምዕራፍ ላይ እልባት ለማድረግ እልባት የሚለውን ቁልፍ ተጫን። ስትጫን ለከፈትከው ጽሑፍ የሚሆኑ እልባቶች ዝርዝር ይወጣሉ። ያለህበት ርዕስ ወይም ምዕራፍ ላይ እልባት ለማድረግ ነፃ የሆነውን የእልባት ምልክት ተጫን።

አንድ አንቀጽ ወይም ጥቅስ ላይ እልባት ለማድረግ መጀመሪያ አንቀጹን ወይም ጥቅሱን ተጫን፤ ከዚያም ስትጫን በሚወጣው ማውጫ ላይ ያለውን የእልባት ምልክት ተጫን።

 እልባቱን መክፈት

እልባት ያደርግክበትን ቦታ ለማግኘት እልባቱ የሚገኝበትን ጽሑፍ ከፍተህ የእልባት ምልክቱን ተጫን። ከዚያም የምትፈልገውን እልባት ምረጥ።

 የተለያየ የእልባት አጠቃቀም

እልባት ካደረግክ በኋላ ልታጠፋው ወይም በሌላ ልትተካው ትችላለህ።

እልባቱን ለማጥፋት እልባት የሚለውን ቁልፍ ተጫን፤ ከዚያም ማጥፋት ከምትፈልገው እልባት አጠገብ ያለውን ሌሎች የሚል ምልክት ተጫን። አጥፋ የሚለውን ተጫን።

እልባቱን በሌላ ለመተካት እልባት የሚለውን ቁልፍ ተጫን፤ ከዚያም መተካት ከምትፈልገው እልባት አጠገብ ያለውን ሌሎች የሚል ምልክት ተጫን። ተካ የሚለውን ተጫን። እልባቱ አሁን በመረጥከው ቦታ ላይ ይሆናል። ይህም የምታነብበውን ጽሑፍ ያቆምክበትን ቦታ ለማወቅ ያስችልሃል። ለምሳሌ በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብብ ያቆምክበትን ቦታ ለማወቅ ይረዳሃል።

እነዚህ ገጽታዎች የወጡት ግንቦት 2014 JW Library 1.2 ሲወጣ ነው፤ አንድሮይድ 2.3 ወይም ከዚያ በላይ ለሚጠቀሙ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Libraryን መጠቀም ጀምር—አንድሮይድ” የሚለውን ከፍተህ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ርዕስ ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።