በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

ጽሑፍ ማቅለም—አንድሮይድ

ጽሑፍ ማቅለም—አንድሮይድ

JW Library ላይ ጽሑፎችን ስታነብብ አንድን ቃል ወይም ሐረግ ማቅለም ትችላለህ።

ጽሑፎችን ለማቅለም እነዚህን መመሪያዎች ተከተል፦

 ጽሑፉን ማቅለም

አንድን ጽሑፍ በሁለት መንገዶች ማቅለም ይቻላል።

አንድን ቃል ተጭነህ በመቆየት ምረጥ። ጫፍ ላይ ያሉትን ምልክቶች በማንቀሳቀስ የምታቀልመውን መጠን መምረጥ ትችላለህ። ቃሉን ስትጫን ከሚመጣው ማውጫ ውስጥ የማቅለሚያ ምልክቱን ተጫን፤ ከዚያም የምትፈልገውን ቀለም ምረጥ።

አንድን ቃል ወይም ሐረግ በአንዴ ለማቅለም ተጭነህ ያዘው፤ ከዚያም ጎትተው። ስትጎትት ጽሑፉን እያቀለምክ ትሄዳለህ። ስትጨርስ ለአጭር ጊዜ ማውጫው ይታያል። ይህን ማውጫ በመጠቀም ቀለም መቀየር ወይም ማጥፋት ትችላለህ።

 ቀለሙን መለወጥ

ቀለም ለመለወጥ ያቀለምከውን ጽሑፍ ተጫን፤ ከዚያም ሌላ ቀለም ምረጥ። ቀለሙን ለማጥፋት ያቀለምከውን ጽሑፍ ተጫን፤ ከዚያም አጥፋ የሚለውን ቁልፍ ተጫን።

እነዚህ ገጽታዎች የወጡት ኅዳር 2015 JW Library 1.6 ሲወጣ ነው፤ አንድሮይድ 4.0 ወይም ከዚያ በላይ ለሚጠቀሙ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Libraryን መጠቀም ጀምር—አንድሮይድ” የሚለውን ከፍተህ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ርዕስ ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።