JW LIBRARY
ቃላትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከጽሑፎች ላይ መፈለግ—አንድሮይድ
በJW Library ላይ ያለው የመፈለጊያ ገጽታ አንድን ቃል ወይም ሐረግ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከጽሑፎች ላይ ለማግኘት ያስችልሃል።
ለመፈለግ እነዚህን መመሪያዎች ተከተል፦
ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መፈለግ
እያነበብከው ካለው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድን ቃል ወይም ሐረግ መፈለግ ትችላለህ።
በምታነብበት ወቅት ፈልግ የሚለውን ቁልፍ ተጫን፤ ከዚያም የምትፈልገውን ቃል ጻፍ። መጻፍ ስትጀምር ተዛማጅ ቃላት ይወጣሉ። ከወጡት ቃላት መካከል የምትፈልገውን በመምረጥ ወይም ጽፈህ ስትጨርስ ቀጥል የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤቱን ማየት ትችላለህ።
ብዙ ጊዜ የተጠቀሱ ጥቅሶች የሚለው፣ ቃሉ የሚገኝባቸውን ብዙ ጊዜ የተጠቀምክባቸውን ጥቅሶች ያወጣል። ሁሉም ጥቅሶች የሚለው ደግሞ ቃሉ የሚገኝባቸውን ጥቅሶች በሙሉ በመጻሕፍቱ ቅደም ተከተል ያወጣል። ርዕሶች የሚለው ደግሞ የምትፈልገው ሐረግ ከአምላክ ቃል ጋር ተዋወቅ በሚለው ወይም በተጨማሪ መረጃዎቹ ላይ የሚገኝበትን ቦታ ያወጣል።
የጻፍከው ከአንድ ቃል በላይ ከሆነ ልክ እንደተጻፈው አውጣ የሚለውን ስትመርጥ ከጻፍከው ሐረግ ጋር አንድ ዓይነት የሆኑትን ውጤቶች ብቻ ያሳይሃል።
ከጽሑፎች ላይ መፈለግ
እያነበብክ ካለኸው ጽሑፍ ላይ አንድን ቃል ወይም ሐረግ መፈለግ ትችላለህ።
እያነበብክ ያለኸው ጽሑፍ ላይ ሆነህ ፈልግ የሚለውን ቁልፍ ተጫን፤ ከዚያም ማግኘት የምትፈልገውን ቃል ጻፍ። መጻፍ ስትጀምር ተዛማጅ የሆኑ ቃላት ይወጣሉ። ውጤቱን ለማየት ከወጡት ቃላት አንዱን ተጫን ወይም [ጽፈህ ስትጨርስ] ቀጥል የሚለውን ቁልፍ ተጫን።
የጻፍከው ከአንድ ቃል በላይ ከሆነ ልክ እንደተጻፈው አውጣ የሚለውን ስትመርጥ ከጻፍከው ሐረግ ጋር አንድ ዓይነት የሆኑትን ውጤቶች ብቻ ያሳይሃል።
ከርዕሶች ላይ መፈለግ
ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል የሚለውን መጽሐፍ ካወረድክ በዚህ መጽሐፍ ላይ የሚገኝን ርዕሰ ጉዳይ መፈለግም ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ ጽሑፎችን ስታነብብ ይህን ገጽታ መጠቀም ትችላለህ።
ፈልግ የሚለውን ቁልፍ ተጫን፤ ከዚያም የምትፈልገውን ቃል ጻፍ። መጻፍ ስትጀምር ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ላይ ያሉ ተዛማጅ ርዕሶችም ይወጡልሃል። ለመክፈት የምትፈልገውን ርዕስ ተጫን።
እነዚህ ገጽታዎች የወጡት ጥቅምት 2014 JW Library 1.3.4 ሲወጣ ነው፤ አንድሮይድ 2.3 ወይም ከዚያ በላይ ለሚጠቀሙ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Libraryን መጠቀም ጀምር—አንድሮይድ” የሚለውን ከፍተህ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ርዕስ ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።