በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

ቃላትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከጽሑፎች ላይ መፈለግ—iOS

ቃላትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከጽሑፎች ላይ መፈለግ—iOS

በJW Library ላይ ያለው የመፈለጊያ ገጽታ አንድን ቃል ወይም ሐረግ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከጽሑፎች ላይ ለማግኘት ያስችልሃል።

ቃላትን ለመፈለግ ከታች ያሉትን መመሪያዎች ተከተል፦

 ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መፈለግ

እያነበብክ ካለኸው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድን ቃል ወይም ሐረግ መፈለግ ትችላለህ።

በምታነብበት ወቅት ፈልግ የሚለውን ቁልፍ ተጫን፤ ከዚያም የምትፈልገውን ቃል ጻፍ። መጻፍ ስትጀምር ተዛማጅ ቃላት ይወጣሉ። ከወጡት ቃላት መካከል የምትፈልገውን በመምረጥ ወይም ፈልግ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤቱን ማየት ትችላለህ።

ብዙ ጊዜ የተጠቀሱ ጥቅሶች የሚለው፣ ቃሉ የሚገኝባቸውን በጽሑፎቻችን ላይ በተደጋጋሚ የወጡ ጥቅሶች ያወጣል። ሁሉም ጥቅሶች የሚለው፣ ቃሉ የሚገኝባቸውን ጥቅሶች በሙሉ በመጻሕፍቱ ቅደም ተከተል ያወጣል። ርዕሶች የሚለው ደግሞ የምትፈልገው ሐረግ ከአምላክ ቃል ጋር ተዋወቅ በሚለው ላይ ወይም በተጨማሪ መረጃዎቹ ላይ የሚገኝበትን ቦታ ያወጣል።

የጻፍከው ከአንድ ቃል በላይ ከሆነ ልክ እንደተጻፈው አውጣ የሚለውን ስትመርጥ ከጻፍከው ሐረግ ጋር አንድ ዓይነት የሆኑትን ውጤቶች ብቻ ያሳይሃል።

 ከጽሑፎች ላይ መፈለግ

እያነበብክ ካለኸው ጽሑፍ ላይ አንድን ቃል ወይም ሐረግ መፈለግም ትችላለህ።

እያነበብክ ያለኸው ጽሑፍ ላይ ሆነህ ፈልግ የሚለውን ቁልፍ ተጫን፤ ከዚያም ማግኘት የምትፈልገውን ቃል ጻፍ። መጻፍ ስትጀምር ተዛማጅ የሆኑ ቃላት ይወጣሉ። ውጤቱን ለማየት ከወጡት ቃላት አንዱን ተጫን ወይም ጽፈህ ስትጨርስ ቀጥል የሚለውን ቁልፍ ተጫን።

የጻፍከው ከአንድ ቃል በላይ ከሆነ ልክ እንደተጻፈው አውጣ የሚለውን ስትመርጥ ከጻፍከው ሐረግ ጋር አንድ ዓይነት የሆኑትን ውጤቶች ብቻ ያሳይሃል።

 ርዕሰ ጉዳዮችን መፈለግ

ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል የሚለውን መጽሐፍ ካወረድክ በዚህ መጽሐፍ ላይ የሚገኝን ርዕሰ ጉዳይ መፈለግም ትችላለህ። አፕሊኬሽኑን ተጠቅመህ መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ ጽሑፎችን ስታነብብ ይህን ገጽታ መጠቀም ትችላለህ።

ፈልግ የሚለውን ቁልፍ ተጫን፤ ከዚያም የምትፈልገውን ቃል ጻፍ። መጻፍ ስትጀምር ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ላይ ያሉ ተዛማጅ ርዕሶችም ይወጡልሃል። መክፈት የምትፈልገውን ርዕስ ተጫን።

ይህ ገጽታ የወጣው ጥቅምት 2014 ሲሆን እትሙ JW Library 1.3.4 ነው፤ ይህ እትም iOS 6.0 ወይም ከዚያ በኋላ ያለ ሶፍትዌር በተጫነላቸው መሣሪያዎች ላይ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Library መጠቀም ጀምር—iOS” በሚለው ርዕስ ውስጥ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።