በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

የሕትመት ውጤቶችን ማውረድና መጠቀም—iOS

የሕትመት ውጤቶችን ማውረድና መጠቀም—iOS

JW Library ላይ ኢንተርኔት ባይኖርም ልታነባቸውና ልታያቸው የምትችል በመቶዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍት፣ ብሮሹሮች፣ ትራክቶችና ቪዲዮዎች አሉ።

የሕትመት ውጤቶችን ለማውረድና ለመጠቀም ከታች ያሉትን መመሪያዎች ተከተል፦

 የሕትመት ውጤቶችን ማውረድ

ኢንተርኔት በማይኖርበት ጊዜ ልትጠቀምባቸው የምትችል የተለያዩ ጽሑፎችን ማውረድ ትችላለህ።

  • የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ስትጫን የጽሑፎቹን ዝርዝር ታገኛለህ።

  • ቋንቋዎች የሚለውን ስትጫን ጽሑፎች የሚገኙባቸውን የተለያዩ ቋንቋዎች ዝርዝር ታገኛለህ። የምትፈልገውን ቋንቋ ምረጥ። ብዙ ጊዜ የተጠቀምክባቸው ቋንቋዎች ከላይ ይሆናሉ። የምትፈልገውን ቋንቋ ስም በመጻፍም ቋንቋውን መፈለግ ትችላለህ።

JW Library ላይ ጽሑፎችን ማግኘት የምትችልባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ።

በዓይነት የሚለው ክፍል በመረጥከው ቋንቋ የሚገኙትን የሕትመት ውጤቶች በየዓይነታቸው ይኸውም መጻሕፍት፣ ትራክት ወይም ቪዲዮዎች በማለት ከፋፍሎ ያስቀምጥልሃል። አንዳንዶቹን ምድቦች ስትጫን በሥራቸው ያሉ ዝርዝሮች ይታዩሃል። ለምሳሌ መጠበቂያ ግንብ በዓመት፣ ቪዲዮዎች ደግሞ በርዕሰ ጉዳይ ተከፋፍለው ይታያሉ። ሁሉንም ዝርዝሮች ለማየት ዋናው ዝርዝር የሚለውን ተጫን።

አዲስ ነገር በሚለው ሥር በመረጥከው ቋንቋ አዲስ የወጡ የሕትመት ውጤቶችን ታገኛለህ።

የደመና ምልክት ያለባቸው፣ ገና ያላወረድካቸው የሕትመት ውጤቶች ናቸው። የሕትመት ውጤቱን ለማውረድ ጽሑፉን ተጫን። ጽሑፉን ስታወርድ የደመናው ምልክት ይጠፋል። ለማንበብ ስትፈልግ ያወረድከውን ጽሑፍ ተጫን።

ያወረድኳቸው በሚለው ሥር በየትኛውም ቋንቋዎች ያወረድካቸውን ጽሑፎች በሙሉ መመልከት ትችላለህ። እነዚህን ጽሑፎች ብዙ ጊዜ የተከፈቱ፣ ብዙ ጊዜ ያልተከፈቱ፣ ወይም ትልቅ መጠን በሚል ቅደም ተከተላቸውን ማስተካከል ትችላለህ።

አንድን ጽሑፍ ማጥፋት

 አንድን ጽሑፍ ካልፈለግከው ወይም ተጨማሪ ማስቀመጫ ቦታ ማግኘት ከፈለግክ ልታጠፋው ትችላለህ።

የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ተጫን፤ ከዚያም ጽሑፎቹን በዝርዝር ለማየት የምትፈልገውን ምድብ (ለምሳሌ መጻሕፍት የሚለውን) ምረጥ። ምረጥ የሚለውን ተጫን፤ ከዚያም ማጥፋት የምትፈልጋቸውን ጽሑፎች አንድ በአንድ ምረጥ። አንድን ጽሑፍ ተጭነህ በመያዝም መምረጥ ትችላለህ። አጥፋ የሚለውን ተጫን፤ ከዚያም በእርግጥ ጽሑፉን ማጥፋት እንደምትፈልግ አረጋግጥ።

ተጨማሪ ማስቀመጫ ቦታ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ያልከፈትካቸውን ወይም ትልቅ መጠን ያላቸውን የሕትመት ውጤቶች ማጥፋት ትችላለህ። የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ከተጫንክ በኋላ ያወረድኳቸው የሚለው ውስጥ በመግባት ብዙ ጊዜ ያልተከፈቱ ወይም ትልቅ መጠን በማለት መለየት ትችላለህ። ከዚያም የማትፈልጋቸውን ጽሑፎች አጥፋ።

ጽሑፎችን ማደስ

 አንዳንድ ጊዜ ያወረድካቸው ጽሑፎች መታደስ ያስፈልጋቸው ይሆናል።

መታደስ በሚያስፈልጋቸው ጽሑፎች ላይ አነቃቃ የሚል ምልክት ይታያል። ጽሑፉን ስትጫን ጽሑፉ መታደስ እንደሚያስፈልገው የሚጠቁም መልእክት ይታያል። ጽሑፉን ለማደስ አውርድ የሚለውን ተጫን፤ ያልታደሰውን ጽሑፍ ማንበብ ከፈልግክ ግን በኋላ የሚለውን ተጫን።

ያወረድካቸው ጽሑፎች መታደስ ያስፈልጋቸው እንደሆነ ለማየት የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ተጫን። መታደስ የሚያስፈልገው ነገር ካለ ለመታደስ የተዘጋጁ የሚል ክፍል ይታያል። ለመታደስ ዝግጁ የሆኑ ጽሑፎችን ዝርዝር በሙሉ ለማየት ይህን ቁልፍ ተጫን። አንድን ጽሑፍ ብቻ ማደስ ከፈለግክ ጽሑፉን ተጫን፤ ሁሉንም ማደስ ከፈለግክ ደግሞ ሁሉንም አድስ የሚለውን ተጫን።

ይህ ገጽታ የወጣው የካቲት 2015 ሲሆን እትሙ JW Library 1.4 ነው፤ ይህ እትም በiOS 6.0 ወይም ከዚያ በኋላ ያለ ሶፍትዌር በተጫነላቸው መሣሪያዎች ላይ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Library መጠቀም ጀምር—iOS” በሚለው ርዕስ ውስጥ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።