የኋላ ሽፋን
የኋላ ሽፋን
የትኛው መጽሐፍ ነው?
• በጣም ታላላቅ ናቸው በሚባሉት የሥነ ጥበብ፣ የሥነ ጽሑፍና የሙዚቃ ሥራዎች እንዲሁም በሕግ አቀራረጽ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ያሳደረ?
• በሰው እጅ በተደጋጋሚ ሲገለበጥ ኖሮ ሳይለወጥ በመጀመሪያ በተጻፈበት መልኩ እስከ ዘመናችን የደረሰ?
• ሰዎች መጽሐፉን ለመተርጎም ሲሉ ራሳቸውን ለመከራና ለሞት እስከማጋለጥ ድረስ ራሳቸውን መሥዋዕት እንዲያደርጉ ያነሳሳ?
• ከ2,100 በሚበልጡ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ከ90 በመቶ በላይ ለሚሆነው የሰው ዘር የተዳረሰ?
• ከብዙ መቶ ዘመናት በኋላ የታወቁ ሳይንሳዊ ሐቆችን የሚጠቅስ?
• ከማንኛውም ዘር፣ ጎሳና ብሔር የመጡ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ የሚረዷቸው ዘመናት የማይሽሯቸው መሠረታዊ ሥርዓቶች የሚገኙበት?
• በትክክል መፈጸማቸው በታሪክ የተረጋገጠላቸው ግልጽ የሆኑ ትንቢቶች የሚገኙበት?
እንዲህ ያለውን መጽሐፍ መመርመር ተገቢ አይሆንምን?