ለውይይት የሚሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች
ለውይይት የሚሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች
1. ሃይማኖት
አንድ ተስፋ፣ አንድ እምነት፣ አንድ ጥምቀት። ኤፌ 4:5, 13
ደቀ መዛሙርት የማድረግ ተልእኮ ተሰጥቶታል። ማቴ 28:19፤ ሥራ 8:12፤ 14:21
በፍሬው ይታወቃል። ማቴ 7:19, 20፤ ሉቃስ 6:43, 44፤ ዮሐ 15:8
በአባሎቹ መካከል ፍቅርና ስምምነት ይኖራል። ዮሐ 13:35፤ 1ቆሮ 1:10፤ 1ዮሐ 4:20
ኢየሱስ የሐሰት ትምህርትን አውግዟል። ማቴ 23:15, 23, 24፤ 15:4-9
እንደዚያ ያደረገው ለታወሩት ጥበቃ ሲል ነው። ማቴ 15:14
እውነት ነፃ አውጥቶ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸዋል። ዮሐ 8:31, 32
ሐ. ሃይማኖታችን ስህተት መሆኑ ከተረጋገጠ የግድ መለወጥ ያስፈልገናል
እውነት ነፃ ያወጣል፤ ብዙዎች እንደተሳሳቱ ያሳያል። ዮሐ 8:31, 32
እስራኤላውያንና ሌሎች ፊተኛውን አምልኳቸውን ትተዋል። ኢያሱ 24:15፤ 2ነገ 5:17
የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የቀድሞ አስተሳሰባቸውን ለውጠዋል። ገላ 1:13, 14፤ ሥራ 3:17, 19
ጳውሎስ ሃይማኖቱን ለውጧል። ሥራ 26:4-6
መላው ዓለም ተታሏል፤ አስተሳሰባችንን መለወጥ ያስፈልገናል። ራእይ 12:9፤ ሮም 12:2
መ. “ሁሉም ሃይማኖቶች ጥሩ ነገር” ያላቸው ቢመስሉም አምላክ እንደሚቀበላቸው ማረጋገጫ አይሆንም
አምልኮን በተመለከተ መሥፈርት የሚያወጣው አምላክ ነው። ዮሐ 4:23, 24፤ ያዕ 1:27
ከአምላክ ፈቃድ ጋር የማይስማማ ከሆነ ተቀባይነት የለውም። ሮም 10:2, 3
ሰዎች “መልካም ሥራዎች” የሚሏቸውን ነገሮች አምላክ ላይቀበላቸው ይችላል። ማቴ 7:21-23
የሚታወቀው በፍሬው ነው። ማቴ 7:20
2. ሃይማኖትን መቀላቀል
ሀ. ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ኅብረት መፍጠር በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት የለውም
መንገዱ ጠባብና አንድ ብቻ ነው፤ የሚያገኙት ጥቂቶች ናቸው። ኤፌ 4:4-6፤ ማቴ 7:13, 14
የሐሰት ትምህርት እንደሚበክል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። ማቴ 16:6, 12፤ ገላ 5:9
ከሐሰት ሃይማኖት እንድንለይ ታዘናል። 2ጢሞ 3:5፤ 2ቆሮ 6:14-17፤ ራእይ 18:4
ለ. “ሁሉም ሃይማኖቶች ጥሩ ነገር አላቸው” የሚባለው እውነት አይደለም
አንዳንዶች ቅንዓት አላቸው፤ ሆኖም ከአምላክ ፈቃድ ጋር የሚስማማ አይደለም። ሮም 10:2, 3
መጥፎ ነገር ሌላውን መልካም ነገር ሁሉ ያበላሻል። 1ቆሮ 5:6፤ ማቴ 7:15-17
የሐሰት አስተማሪዎች ጥፋት ያመጣሉ። 2ጴጥ 2:1፤ ማቴ 12:30፤ 15:14
ንጹሕ አምልኮ ለይሖዋ ብቻ የተወሰነ አምልኮ ማቅረብን ይጠይቃል። ዘዳ 6:5, 14, 15
3. ለማርያም የሚቀርብ አምልኮ
ሀ. ማርያም የኢየሱስ እናት እንጂ “የአምላክ እናት” አልነበረችም
አምላክ መጀመሪያ የለውም። መዝ 90:2፤ 1ጢሞ 1:17
የአምላክ ልጅ በምድር ሳለ ማርያም እናቱ ነበረች። ሉቃስ 1:35
ለ. ማርያም “ለሁልጊዜው ድንግል” ሆና አልኖረችም
ዮሴፍን አግብታለች። ማቴ 1:19, 20, 24, 25
ከኢየሱስ በተጨማሪ ሌሎች ልጆች ወልዳለች። ማቴ 13:55, 56፤ ሉቃስ 8:19-21
እነሱ በወቅቱ “መንፈሳዊ ወንድሞቹ” አልነበሩም። ዮሐ 7:3, 5
4. ሐሰተኛ ነቢያት
ሀ. ሐሰተኛ ነቢያት እንደሚመጡ አስቀድሞ ተነግሯል፤ በሐዋርያት ዘመን ነበሩ
ሐሰተኛ ነቢያትን መለየት የሚቻልበት መንገድ። ዘዳ 18:20-22፤ ሉቃስ 6:26
እንደሚመጡ አስቀድሞ ተነግሯል፤ በፍሬያቸው ይታወቃሉ። ማቴ 24:23-26፤ 7:15-23
5. ሕይወት
ሀ. ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች የዘላለም ሕይወት እንደሚያገኙ ማረጋገጫ ተሰጥቷቸዋል
ሊዋሽ የማይችለው አምላክ የዘላለም ሕይወት ተስፋ ሰጥቷል። ቲቶ 1:2፤ ዮሐ 10:27, 28
እምነታቸውን በተግባር የሚያሳዩ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸዋል። ዮሐ 11:25, 26
ሞት ይጠፋል። 1ቆሮ 15:26፤ ራእይ 21:4፤ 20:14፤ ኢሳ 25:8
ለ. በሰማይ ሕይወት የሚያገኙት የክርስቶስ አካል የሆኑት ብቻ ናቸው
አምላክ እሱ በፈለገው መንገድ አባሎቹን ይመርጣል። ማቴ 20:23፤ 1ቆሮ 12:18
ከምድር የሚወሰዱት 144,000 ብቻ ናቸው። ራእይ 14:1, 4፤ 7:2-4፤ 5:9, 10
አጥማቂው ዮሐንስ እንኳ የሰማያዊው መንግሥት አባል አይሆንም። ማቴ 11:11
ሐ. ቁጥራቸው ያልተወሰነ “ሌሎች በጎች” ምድራዊ ሕይወት እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸዋል
በሰማይ ከኢየሱስ ጋር የሚሆኑት ቁጥራቸው የተወሰነ ነው። ራእይ 14:1, 4፤ 7:2-4
“ሌሎች በጎች” የክርስቶስ ወንድሞች አይደሉም። ዮሐ 10:16፤ ማቴ 25:32, 40
አሁን ብዙ ሰዎች ከጥፋት ተርፈው ምድር ላይ ለመኖር እየተሰበሰቡ ነው። ራእይ 7:9, 15-17
ሌሎች ደግሞ በምድር ላይ ለመኖር ትንሣኤ ያገኛሉ። ራእይ 20:12፤ 21:4
6. መመሥከር
ሀ. ሁሉም ክርስቲያኖች መመሥከር፣ ምሥራቹን መናገር አለባቸው
ተቀባይነት ለማግኘት ስለ ኢየሱስ በሰው ፊት መመሥከር አለብን። ማቴ 10:32
ቃሉን በተግባር በማዋል እምነታችንን በሥራ ማሳየት አለብን። ያዕ 1:22-24፤ 2:24
አዲሶችም አስተማሪዎች መሆን አለባቸው። ማቴ 28:19, 20
ለሕዝብ መመሥከር መዳን ያስገኛል። ሮም 10:10
ለ. ደጋግሞ ወደ ሰዎች መሄድ፣ በምሥክርነቱ ሥራ መቀጠል ያስፈልጋል
ፍጻሜው እንደሚመጣ ማስጠንቀቂያ መሰጠት ይኖርበታል። ማቴ 24:14
ኤርምያስ ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ ለብዙ ዓመታት አስታውቋል። ኤር 25:3
እንደ ጥንቶቹ ክርስቲያኖች ሁሉ እኛም መመሥከራችንን ልናቆም አንችልም። ሥራ 4:18-20፤ 5:28, 29
እየቀረበ ስለመጣው ፍጻሜ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለብን። ሕዝ 33:7፤ ማቴ 24:14
ይህን አለማድረግ በደም ዕዳ ተጠያቂ ያደርጋል። ሕዝ 33:8, 9፤ 3:18, 19
ጳውሎስ ከደም ዕዳ ነፃ ሆኗል፤ እውነትን በተሟላ ሁኔታ ሰብኳል። ሥራ 20:26, 27፤ 1ቆሮ 9:16
የምሥክርነቱ ሥራ የሚመሠክረውንም ሆነ የሚሰማውን ያድናል። 1ጢሞ 4:16፤ 1ቆሮ 9:22
7. መስቀል
ሀ. ኢየሱስ እንዲዋረድ ሲባል ወንጀለኞች በሚሰቀሉበት እንጨት ላይ እንዲሰቀል ተደርጓል
ኢየሱስ ወንጀለኞች በሚሰቀሉበት እንጨት ወይም ግንድ ላይ ተሰቅሏል። ሥራ 5:30፤ 10:39፤ ገላ 3:13
ክርስቲያኖች የመከራውን እንጨት መሸከማቸው የሚደርስባቸውን ነቀፋ ለመቀበል ፈቃደኛ መሆናቸውን ያሳያል። ማቴ 10:38፤ ሉቃስ 9:23
ኢየሱስ የተሰቀለበትን እንጨት እንደ ጌጥ መጠቀም እሱን እንደማዋረድ ይቆጠራል። ዕብ 6:6፤ ማቴ 27:41, 42
መስቀልን ለአምልኮ መጠቀም ጣዖት አምልኮ ነው። ዘፀ 20:4, 5፤ ኤር 10:3-5
አሁን ኢየሱስ መንፈስ ነው፤ ገና እንደተሰቀለ አይደለም። 1ጢሞ 3:16፤ 1ጴጥ 3:18
8. መታሰቢያ በዓል፣ ቁርባን
በፋሲካ ዕለት በዓመት አንድ ጊዜ ይከበራል። ሉቃስ 22:1, 17-20፤ ዘፀ 12:14
የክርስቶስ መሥዋዕታዊ ሞት መታሰቢያ ነው። 1ቆሮ 11:26፤ ማቴ 26:28
ሰማያዊ ተስፋ ያላቸው ይካፈላሉ። ሉቃስ 22:29, 30፤ 12:32, 37
አንድ ሰው ይህ ተስፋ እንዳለው የሚያውቀው እንዴት ነው? ሮም 8:15-17
የኃጢአት ይቅርታ ለማግኘት ደም መፍሰስ አለበት። ዕብ 9:22
ክርስቶስ ብቸኛው የአዲሱ ቃል ኪዳን መካከለኛ ነው። 1ጢሞ 2:5, 6፤ ዮሐ 14:6
ክርስቶስ ያለው በሰማይ ነው፤ ቄስ ወደ ምድር እንዲወርድ ሊያደርገው አይችልም። ሥራ 3:20, 21
የክርስቶስ መሥዋዕት በድጋሚ መቅረብ አያስፈልገውም። ዕብ 9:24-26፤ 10:11-14
9. መንግሥት
ሀ. የአምላክ መንግሥት ለሰው ልጆች ምን ያመጣል?
የአምላክን ፈቃድ ያስፈጽማል። ማቴ 6:9, 10፤ መዝ 45:6፤ ራእይ 4:11
ንጉሥና ሕግ ያለው መስተዳድር ነው። ኢሳ 9:6, 7፤ 2:3፤ መዝ 72:1, 8
ክፋትን አስወግዶ ጠቅላላውን ምድር ይገዛል። ዳን 2:44፤ መዝ 72:8
በ1,000 ዓመት የግዛት ዘመን የሰው ልጆችን መጀመሪያ ላይ ወደነበረው ሁኔታ ይመልሳል፤ ገነትን ያመጣል። ራእይ 21:2-4፤ 20:6
ለ. መግዛት የሚጀምረው የክርስቶስ ጠላቶች ገና እያሉ ነው
ክርስቶስ ከተነሳ በኋላ ረጅም ዘመን መጠበቅ ነበረበት። መዝ 110:1፤ ዕብ 10:12, 13
ሥልጣንን እንደሚይዝና ሰይጣንን እንደሚዋጋ ተገልጿል። መዝ 110:2፤ ራእይ 12:7-9፤ ሉቃስ 10:18
መንግሥቱ ከተቋቋመ በኋላ በምድር ላይ ወዮታ ይከሰታል። ራእይ 12:10, 12
በአሁኑ ጊዜ ያለው መከራ መንግሥቱን ደግፎ ለመቆም ጊዜው አሁን መሆኑን ያሳያል። ራእይ 11:15-18
ሐ. በሰው ‘ልብ ውስጥ’ ያለም ሆነ በሰዎች ጥረት የሚመጣ አይደለም
መንግሥቱ በሰማይ እንጂ በምድር አይደለም። 2ጢሞ 4:18፤ 1ቆሮ 15:50፤ መዝ 11:4
በሰው ‘ልብ ውስጥ’ ያለ አይደለም፤ ኢየሱስ እየተናገረ የነበረው ለፈሪሳውያን ነው። ሉቃስ 17:20, 21
የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም። ዮሐ 18:36፤ ሉቃስ 4:5-8፤ ዳን 2:44
መንግሥታትና የዓለም መሥፈርቶች በሌላ ይተካሉ። ዳን 2:44
10. መንፈስ፣ መናፍስታዊ ድርጊቶች
ከአምላክ የሚወጣ ኃይል እንጂ ራሱን የቻለ አካል አይደለም። ሥራ 2:2, 3, 33፤ ዮሐ 14:17
አምላክ ለመፍጠር፣ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጽፉ ለማነሳሳት ወዘተ ተጠቅሞበታል። ዘፍ 1:2፤ ሕዝ 11:5
የክርስቶስ አካል አባላት በመንፈስ የተወለዱና የተቀቡ ናቸው። ዮሐ 3:5-8፤ 2ቆሮ 1:21, 22
በዛሬው ጊዜ የአምላክን ሕዝቦች ያበረታቸዋል እንዲሁም ይመራቸዋል። ገላ 5:16, 18
ለ. ሕይወትን የሚያንቀሳቅሰው ኃይል መንፈስ ተብሏል
የሕይወት ኃይል ቀጣይ የሚሆነው በመተንፈስ ነው። ያዕ 2:26፤ ኢዮብ 27:3
ሕይወትን የሚያንቀሳቅሰው ኃይል በአምላክ እጅ ነው። ዘካ 12:1፤ መክ 8:8
የሰዎችና የእንስሳት የሕይወት ኃይል ባለቤት አምላክ ነው። መክ 3:19-21
ሰው ትንሣኤን ተስፋ በማድረግ መንፈሱን ለአምላክ ይሰጣል። ሉቃስ 23:46
ሐ. መናፍስታዊ ድርጊቶች የአጋንንት ሥራ ስለሆኑ ልንርቃቸው ይገባል
የአምላክ ቃል ከመናፍስታዊ ድርጊቶች እንድንርቅ ያዛል። ኢሳ 8:19, 20፤ ዘሌ 19:31፤ 20:6, 27
ጥንቆላ የአጋንንት ሥራ ነው፤ ተወግዟል። ሥራ 16:16-18
ለጥፋት ይዳርጋል። ገላ 5:19-21፤ ራእይ 21:8፤ 22:15
ኮከብ ቆጠራ የተወገዘ ነው። ዘዳ 18:10-12፤ ኤር 10:2
11. መዳን
ሀ. መዳን የሚገኘው ከአምላክ ሲሆን ይህም የሚሆነው በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ነው
ሕይወት አምላክ በልጁ በኩል የሚሰጠን ስጦታ ነው። 1ዮሐ 4:9, 14፤ ሮም 6:23
መዳን የሚቻለው በኢየሱስ መሥዋዕት በኩል ብቻ ነው። ሥራ 4:12
“በሞት ጣር ላይ እያሉ ንስሐ በመግባት” ለመዳን የሚያበቃ ሥራ መሥራት አይቻልም። ያዕ 2:14, 26
ለመዳን ብርቱ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። ሉቃስ 13:23, 24፤ 1ጢሞ 4:10
ለ. “አንዴ የዳነ ለሁልጊዜው ድኗል” የሚለው አባባል ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረት የለውም
የመንፈስ ቅዱስ ተካፋይ የሆኑት ሊወድቁ ይችላሉ። ዕብ 6:4, 6፤ 1ቆሮ 9:27
ብዙ እስራኤላውያን ከግብፅ ቢድኑም በኋላ ጠፍተዋል። ይሁዳ 5
መዳን ወዲያው የሚገኝ ነገር አይደለም። ፊልጵ 2:12፤ 3:12-14፤ ማቴ 10:22
ወደኋላ የሚመለሱት ከበፊቱ የከፋ ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ። 2ጴጥ 2:20, 21
ሐ. “ሁሉም ሰው ይድናል” የሚለው አባባል ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረት የለውም
ለአንዳንዶች ንስሐ መግባት የማይቻል ነገር ነው። ዕብ 6:4-6
አምላክ በክፉዎች ሞት አይደሰትም። ሕዝ 33:11፤ 18:32
ይሁን እንጂ ፍቅር ዓመፅን ቸል ብሎ አያልፍም። ዕብ 1:9
ክፉዎች ይጠፋሉ። ዕብ 10:26-29፤ ራእይ 20:7-15
12. መጽሐፍ ቅዱስ
ሀ. የአምላክ ቃል በመንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው
ሰዎች እንዲጽፉ ያነሳሳቸው የአምላክ መንፈስ ነው። 2ጴጥ 1:20, 21
ትንቢቶችን ይዟል:- ዳን 8:5, 6, 20-22፤ ሉቃስ 21:5, 6, 20-22፤ ኢሳ 45:1-4
ጠቅላላው መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ መሪነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው። 2ጢሞ 3:16, 17፤ ሮም 15:4
የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ችላ ማለት ለሞት ይዳርጋል። ሮም 1:28-32
የሰው ጥበብ ሊተካው አይችልም። 1ቆሮ 1:21, 25፤ 1ጢሞ 6:20
ብርቱ የሆነን ጠላት ለመመከት ያስችላል። ኤፌ 6:11, 12, 17
ሰውን በትክክለኛው አቅጣጫ ይመራል። መዝ 119:105፤ 2ጴጥ 1:19፤ ምሳሌ 3:5, 6
መጽሐፍ ቅዱስን መጻፍ የተጀመረው በመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ነው። ዘፀ 17:14፤ 24:12, 16፤ 34:27
አምላክ ያስጻፈው ለአውሮፓውያን ብቻ አይደለም። ሮም 10:11-13፤ ገላ 3:28
አምላክ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ይቀበላል። ሥራ 10:34, 35፤ ሮም 5:18፤ ራእይ 7:9, 10
13. ምስሎች
ሀ. ምስሎችንና ቅርጻ ቅርጾችን ለአምልኮ መጠቀም አምላክን እንደማዋረድ ይቆጠራል
የአምላክን ምስል መሥራት የማይቻል ነገር ነው። 1ዮሐ 4:12፤ ኢሳ 40:18፤ 46:5፤ ሥራ 17:29
ክርስቲያኖች ከምስሎች እንዲርቁ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። 1ቆሮ 10:14፤ 1ዮሐ 5:21
አምላክ በመንፈስና በእውነት መመለክ አለበት። ዮሐ 4:24
ለ. የምስል አምልኮ የእስራኤልን ሕዝብ ለጥፋት ዳርጎታል
አይሁዶች ምስሎችን እንዳያመልኩ ተከልክለው ነበር። ዘፀ 20:4, 5
ሊሰሙና ሊናገሩ አይችሉም፤ የሚሠሯቸው እንደነሱ ይሆናሉ። መዝ 115:4-8
ወጥመድና ጥፋት አምጥተዋል። መዝ 106:36, 40-42፤ ኤር 22:8, 9
ሐ. በተወሰነ መጠንም ቢሆን አምልኮን ለሌላ መስጠት አልተፈቀደም
አምላክ በተወሰነ መጠንም ቢሆን አምልኮ ለሌሎች እንዲቀርብ አይፈልግም። ኢሳ 42:8
‘ጸሎትን የሚሰማው’ አምላክ ብቻ ነው። መዝ 65:1, 2
14. ምድር
በምድር ላይ ፍጹማን ሰዎች የሚኖሩበት ገነት ተዘጋጅቶ ነበር። ዘፍ 1:28፤ 2:8-15
የአምላክ ዓላማ በእርግጥ ይፈጸማል። ኢሳ 55:11፤ 46:10, 11
ምድር ሰላማውያንና ፍጹማን በሆኑ ሰዎች ትሞላለች። መዝ 72:7፤ ኢሳ 45:18፤ 9:6, 7
በአምላክ መንግሥት አማካኝነት ገነት ተመልሶ ይቋቋማል። ማቴ 6:9, 10፤ ራእይ 21:3-5
ግዑዟ ምድር ለሁልጊዜ ጸንታ ትኖራለች። መክ 1:4፤ መዝ 104:5
በኖኅ ጊዜ የጠፉት የሰው ልጆች እንጂ ምድር አልነበረችም። 2ጴጥ 3:5-7፤ ዘፍ 7:23
በዚያን ጊዜ የተፈጸመው ነገር በዘመናችንም ከጥፋት መትረፍ እንደሚቻል ይጠቁማል። ማቴ 24:37-39
ክፉዎች ይጠፋሉ፤ “እጅግ ብዙ ሕዝብ” ይተርፋል። 2ተሰ 1:6-9፤ ራእይ 7:9, 14
15. ሞት
የሰው ልጅ ሕይወት ጅምር ፍጹም ነበር፤ ፍጻሜ የሌለው ሕይወት ከፊቱ ተዘርግቶለት ነበር። ዘፍ 1:28, 31
አለመታዘዝ የሞት ፍርድ አመጣ። ዘፍ 2:16, 17፤ 3:17, 19
ኃጢአትና ሞት ወደ አዳም ልጆች ሁሉ ተላልፈዋል። ሮም 5:12
አዳም ራሱ ነፍስ ነበር እንጂ ነፍስ አልተሰጠውም። ዘፍ 2:7፤ 1ቆሮ 15:45
የሚሞተው ነፍስ የሆነው ሰውየው ራሱ ነው። ሕዝ 18:4፤ ኢሳ 53:12፤ ኢዮብ 11:20
ሙታን አይሰሙም፤ ምንም አያውቁም። መክ 9:5, 10፤ መዝ 146:3, 4
ሙታን አንቀላፍተዋል፤ ትንሣኤ ይጠብቃሉ። ዮሐ 11:11-14, 23-26፤ ሥራ 7:60
ሙታን መናፍስት ሆነው ከአምላክ ጋር እየኖሩ አይደለም። መዝ 115:17፤ ኢሳ 38:18
ከሙታን ጋር ለመነጋገር እንዳንሞክር ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል። ኢሳ 8:19፤ ዘሌ 19:31
መናፍስት ጠሪዎችና ጠንቋዮች የተወገዙ ናቸው። ዘዳ 18:10-12፤ ገላ 5:19-21
16. ሥላሴ
ሀ. አባት የሆነው አምላክ አንድ ነው፤ በጽንፈ ዓለም ውስጥ ከሁሉ የሚበልጠው እሱ ነው
አምላክ የሦስት አካላት ጥምረት አይደለም። ዘዳ 6:4፤ ሚል 2:10፤ ማር 10:18፤ ሮም 3:29, 30
ወልድ ፍጡር ነው፤ ከዚያ በፊት አምላክ ብቻውን ነበር። ራእይ 3:14፤ ቆላ 1:15፤ ኢሳ 44:6
አምላክ ምንጊዜም የጽንፈ ዓለም ገዥ ነው።አምላክ ከሁሉም በላይ ከፍ መደረግ ይኖርበታል። ፊልጵ 2:10, 11
ለ. ወልድ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ ከአባቱ ያንሳል
ወልድ በሰማይ ሳለ ታዛዥ ነበር፤ ወደ ምድር የመጣው አባቱ ልኮት ነው። ዮሐ 8:42፤ 12:49
ምድር ላይ ሳለ ታዛዥ ነበር፤ አባቱ ይበልጠዋል። ዮሐ 14:28፤ 5:19፤ ዕብ 5:8
በሰማይ ከፍ ከፍ ተደርጓል፤ ያም ሆኖ ለአባቱ ይገዛል። ፊልጵ 2:9፤ 1ቆሮ 15:28፤ ማቴ 20:23
ይሖዋ የክርስቶስ ራስና አምላክ ነው። 1ቆሮ 11:3፤ ዮሐ 20:17፤ ራእይ 1:6
ምንጊዜም ፍጹም ስምምነት አላቸው። ዮሐ 8:28, 29፤ 14:10
አንድነታቸው በባልና በሚስት መካከል እንዳለው አንድነት ነው። ዮሐ 10:30፤ ማቴ 19:4-6
አማኞች በሙሉ ይኸው አንድነት ሊኖራቸው ይገባል። ዮሐ 17:20-22፤ 1ቆሮ 1:10
በክርስቶስ በኩል ይሖዋ ብቻ ለዘላለም ይመለካል። ዮሐ 4:23, 24
ኃይል እንጂ ራሱን የቻለ አካል አይደለም። ማቴ 3:16፤ ዮሐ 20:22፤ ሥራ 2:4, 17, 33
በሰማይ ከአምላክና ከክርስቶስ ጋር የሚኖር ራሱን የቻለ አካል አይደለም። ሥራ 7:55, 56፤ ራእይ 7:10
አምላክ ዓላማዎቹን ለመፈጸም በፈለገው መንገድ ይጠቀምበታል። መዝ 104:30፤ 1ቆሮ 12:4-11
አምላክን የሚያገለግሉ መንፈሱን ይቀበላሉ፤ እንዲሁም በመንፈሱ ይመራሉ። 1ቆሮ 2:12, 13፤ ገላ 5:16
17. ሰማይ
ሀ. ወደ ሰማይ የሚሄዱት 144,000 ብቻ ናቸው
ቁጥራቸው የተወሰነ ነው፤ ከክርስቶስ ጋር ነገሥታት ይሆናሉ። ራእይ 5:9, 10፤ 20:4
የመጀመሪያው ኢየሱስ ነው፤ ከዚያ በኋላ ሌሎች ተመርጠዋል። ቆላ 1:18፤ 1ጴጥ 2:21
ሌሎች ብዙ ሰዎች ምድር ላይ ይኖራሉ። መዝ 72:8፤ ራእይ 21:3, 4
144,000ዎቹ ሌሎች ያላገኙትን ልዩ ቦታ ያገኛሉ። ራእይ 14:1, 3፤ 7:4, 9
18. ሰንበት
ሀ. ክርስቲያኖች የሰንበትን ቀን እንዲያከብሩ አይገደዱም
የኢየሱስ ሞት ሕጉን አስወግዶታል። ኤፌ 2:15
ክርስቲያኖች ሰንበትን የማክበር ግዴታ የለባቸውም። ቆላ 2:16, 17፤ ሮም 14:5, 10
ሰንበትንና የመሳሰሉትን በማክበራቸው ተወቅሰዋል። ገላ 4:9-11፤ ሮም 10:2-4
ወደ አምላክ እረፍት የምንገባው በእምነትና በታዛዥነት ነው። ዕብ 4:9-11
ለ. ሰንበትን እንዲያከብሩ የታዘዙት የጥንት እስራኤላውያን ብቻ ናቸው
ሰንበት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው ከግብፅ ከወጡ በኋላ ነው። ዘፀ 16:26, 27, 29, 30
ለሥጋዊ እስራኤላውያን ብቻ ምልክት ሆኖ የሚያገለግል ነበር። ዘፀ 31:16, 17፤ መዝ 147:19, 20
ሕጉ ዓመታዊ ሰንበትንም ይጨምር ነበር። ዘፀ 23:10, 11፤ ዘሌ 25:3, 4
ሰንበት ለክርስቲያኖች አስፈላጊ ነገር አይደለም። ሮም 14:5, 10፤ ገላ 4:9-11
ሐ. የአምላክ የሰንበት እረፍት (የፍጥረት “ሳምንት” 7ኛ ቀን)
ይህ ሰንበት የጀመረው ምድራዊ የፍጥረት ሥራ ሲያበቃ ነው። ዘፍ 2:2, 3፤ ዕብ 4:3-5
እረፍቱ ኢየሱስ ምድር ላይ ሳለና ከዚያ በኋላም ቀጥሏል። ዕብ 4:6-8፤ መዝ 95:7-9, 11
ክርስቲያኖች የግል ጥቅምን ለማስቀደም ከሚሠሩ ሥራዎች ያርፋሉ። ዕብ 4:9, 10
የአምላክ መንግሥት ከምድር ጋር በተያያዘ የሚያከናውነውን ሥራ ሲያጠናቅቅ የሰንበት እረፍት ያበቃል። 1ቆሮ 15:24, 28
19. ሲኦል (ሔዲስ)
በሥቃይ ላይ የነበረው ኢዮብ እዚያ ለመሄድ ጸልዮአል። ኢዮብ 14:13
ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ የማይካሄድበት ቦታ ነው። መዝ 6:5፤ መክ 9:10፤ ኢሳ 38:18, 19
ኢየሱስ ከመቃብር ወይም ከሲኦል ተነስቷል።ሲኦል ሌሎቹን ሙታን ከሰጠ በኋላ ይጠፋል። ራእይ 20:13, 14
በሞት መጥፋት በእሳት ተመስሏል። ማቴ 25:41, 46፤ 13:30
ንስሐ የማይገቡ ክፉዎች ልክ በእሳት እንደጠፉ ያህል ለዘላለም ይጠፋሉ። ዕብ 10:26, 27
ሰይጣን በእሳት ‘እንደሚሠቃይ’ ተደርጎ መገለጹ ዘላለማዊ ሞትን ያመለክታል። ራእይ 20:10, 14, 15
ሐ. የሀብታሙ ሰውና የአልዓዛር ታሪክ ዘላለማዊ ሥቃይ ለመኖሩ ማስረጃ አይደለም
የአብርሃም እቅፍ ምሳሌያዊ እንደሆነ ሁሉ እሳቱም ምሳሌያዊ ነው። ሉቃስ 16:22-24
በተጨማሪም የአብርሃምን ሞገስ ማግኘት ከጨለማ ጋር ተነጻጽሮ ተገልጿል። ማቴ 8:11, 12
በባቢሎን ላይ የሚደርሰው ጥፋት በእሳት እንደመሠቃየት ተደርጎ ተገልጿል። ራእይ 18:8-10, 21
20. በዓላት፣ የልደት ቀን
ሀ. የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ልደትንና ገናን አያከብሩም ነበር
የእውነተኛ አምልኮ ተከታይ ያልሆኑ ሰዎች ልደትን አክብረዋል። ዘፍ 40:20፤ ማቴ 14:6
መከበር ያለበት ኢየሱስ የሞተበት ቀን ነው። ሉቃስ 22:19, 20፤ 1ቆሮ 11:25, 26
በበዓላት ቀን የሚታየው ፈንጠዝያ ተገቢ አይደለም። ሮም 13:13፤ ገላ 5:21፤ 1ጴጥ 4:3
21. ቤተ ክርስቲያን
ሀ. ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትርጉም አለው፣ የተገነባውም በክርስቶስ ላይ ነው
አምላክ ሰው በሠራው ቤተ መቅደስ አይኖርም። ሥራ 17:24, 25፤ 7:48
እውነተኛው ቤተ ክርስቲያን በሕያዋን ድንጋዮች የታነጸ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ነው። 1ጴጥ 2:5, 6
ክርስቶስ የማዕዘን ድንጋይ ሲሆን ሐዋርያት ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ መሠረት ናቸው። ኤፌ 2:20
አምላክ መመለክ ያለበት በመንፈስና በእውነት ነው። ዮሐ 4:24
ለ. ቤተ ክርስቲያን የተገነባው በጴጥሮስ ላይ አይደለም
ኢየሱስ፣ ቤተ ክርስቲያን በጴጥሮስ ላይ ይገነባል አላለም። ማቴ 16:18
ኢየሱስ “ዐለት” ተብሎ ተገልጿል። 1ቆሮ 10:4
ጴጥሮስ፣ ኢየሱስ መሠረት እንደሆነ ገልጿል። 1ጴጥ 2:4, 6-8፤ ሥራ 4:8-12
22. ቤዛ
ሀ. የኢየሱስ ሰብዓዊ ሕይወት “ለሁሉም ቤዛ” ሆኖ ተከፍሏል
ኢየሱስ ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል። ማቴ 20:28
የፈሰሰው ደም የኃጢአት ስርየት ያስገኛል። ዕብ 9:14, 22
አንዴ የተከፈለው መሥዋዕት ለሁልጊዜ በቂ ነው። ሮም 6:10፤ ዕብ 9:26
ጥቅሞቹ ወዲያው የሚመጡ አይደሉም፤ አምኖ መቀበል ያስፈልጋል። ዮሐ 3:16
አዳም ፍጹም ሆኖ ተፈጥሮ ነበር። ዘዳ 32:4፤ መክ 7:29፤ ዘፍ 1:31
ኃጢአት በመሥራቱ ራሱም ሆነ ልጆቹ ፍጽምናን አጡ። ሮም 5:12, 18
ልጆቹ ራሳቸውን ማዳን አልቻሉም፤ ከአዳም ጋር የሚመጣጠን አስፈለገ። መዝ 49:7፤ ዘዳ 19:21
የኢየሱስ ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወት ቤዛ ሆነ። 1ጢሞ 2:5, 6፤ 1ጴጥ 1:18, 19
23. ተቃውሞ፣ ስደት
ሀ. በክርስቲያኖች ላይ ተቃውሞ የሚደርስበት ምክንያት
ኢየሱስ ተጠልቷል፤ ተቃውሞ እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል። ዮሐ 15:18-20፤ ማቴ 10:22
ትክክለኛ መሠረታዊ ሥርዓቶችን በጥብቅ መከተል ዓለምን ይኰንናል። 1ጴጥ 4:1, 4, 12, 13
የዚህ ሥርዓት አምላክ የሆነው ሰይጣን የአምላክን መንግሥት ይቃወማል። 2ቆሮ 4:4፤ 1ጴጥ 5:8
ክርስቲያን አይፈራም፤ አምላክ ይደግፈዋል። ሮም 8:38, 39፤ ያዕ 4:8
ለ. ሚስት ባሏ ከአምላክ እንዲለያት መፍቀድ የለባትም
አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፤ ሌሎች ያልሆነ ወሬ ሊነግሩት ይችላሉ። ማቴ 10:34-38፤ ሥራ 28:22
ከአምላክና ከክርስቶስ ጋር ያላትን ዝምድና አጥብቃ መያዝ አለባት። ዮሐ 6:68፤ 17:3
በታማኝነቷ እሱንም ማዳን ትችል ይሆናል። 1ቆሮ 7:16፤ 1ጴጥ 3:1-6
ባል ራስ ነው፤ ሆኖም የእሱን አምልኮ እንድትከተል ማስገደድ አይችልም። 1ቆሮ 11:3፤ ሥራ 5:29
ሐ. ባል ሚስቱ አምላክን ማገልገሉን እንድታስተወው መፍቀድ የለበትም
ሚስቱንና ቤተሰቡን መውደድ አለበት፤ ሕይወት እንዲያገኙ ይፈልጋል። 1ቆሮ 7:16
ውሳኔ የማድረግና ለቤተሰቡ የሚያስፈልጉትን ነገሮች የማቅረብ ኃላፊነት አለበት። 1ቆሮ 11:3፤ 1ጢሞ 5:8
አምላክ ለእውነት የሚቆምን ሰው ይወዳል። ያዕ 1:12፤ 5:10, 11
ለሰላም ብሎ አቋምን ማላላት የአምላክን ሞገስ ያሳጣል። ዕብ 10:38
ቤተሰብህ በአዲሱ ዓለም ውስጥ የሚገኘው ደስታ ተካፋይ እንዲሆን እርዳ። ራእይ 21:3, 4
24. ትንሣኤ
በመቃብር ያሉት ሁሉ ይነሳሉ። ዮሐ 5:28, 29
የኢየሱስ ትንሣኤ ለዚህ ዋስትና ነው። 1ቆሮ 15:20-22፤ ሥራ 17:31
በመንፈስ ቅዱስ ላይ ኃጢአት የሠሩ አይነሱም። ማቴ 12:31, 32
እምነት የሚያሳዩ ትንሣኤ እንደሚያገኙ ዋስትና አላቸው። ዮሐ 11:25
ሁሉም በአዳም ይሞታሉ፤ በኢየሱስ ሕይወት ያገኛሉ። 1ቆሮ 15:20-22፤ ሮም 5:19
የሚነሱት ሰዎች አካላዊ ሁኔታ ይለያያል። 1ቆሮ 15:40, 42, 44
ከኢየሱስ ጋር የሚሆኑት ልክ እንደ እሱ ይሆናሉ። 1ቆሮ 15:49፤ ፊልጵ 3:20, 21
ገዥ የማይሆኑት በምድር ላይ ይኖራሉ። ራእይ 20:4ለ, 5, 13፤ 21:3, 4
25. ኃጢአት
የአምላክን ሕግ፣ እሱ ያወጣውን ፍጹም መሥፈርት መጣስ ማለት ነው። 1ዮሐ 3:4፤ 5:17
ሰው የአምላክ ፍጡር እንደመሆኑ በእሱ ዘንድ ተጠያቂ ነው። ሮም 14:12፤ 2:12-15
ሕጉ ኃጢአት ምን እንደሆነ ገለጸ፤ ሰዎች ኃጢአተኝነታቸው እንዲታወቃቸው አደረገ። ገላ 3:19፤ ሮም 3:20
ሁሉም ኃጢአት አለባቸው፤ የአምላክን ፍጹም መሥፈርት አያሟሉም። ሮም 3:23፤ መዝ 51:5
ለ. ሁሉም በአዳም ኃጢአት አበሳ ያዩት ለምንድን ነው?
አዳም ለሁሉም አለፍጽምናንና ሞትን አስተላለፈ። ሮም 5:12, 18
አምላክ የሰው ልጆችን በመታገሥ መሐሪነቱን አሳይቷል። መዝ 103:8, 10, 14, 17
የኢየሱስ መሥዋዕት ኃጢአትን ያስተሰርያል። 1ዮሐ 2:2
ኃጢአትና ሌሎቹ የዲያብሎስ ሥራዎች በሙሉ ይወገዳሉ። 1ዮሐ 3:8
ሐ. የተከለከለው ፍሬ ካለመታዘዝ ጋር እንጂ ከወሲብ ጋር ግንኙነት የለውም
ከዛፉ መብላት የተከለከለው ሔዋን ከመፈጠሯ በፊት ነው። ዘፍ 2:17, 18
አዳምና ሔዋን ልጆች እንዲወልዱ ተነግሯቸዋል። ዘፍ 1:28
ልጆች የአምላክ በረከት እንጂ የኃጢአት ውጤት አይደሉም። መዝ 127:3-5
ሔዋን ኃጢአት የሠራችው ባሏ በሌለበት ነው፤ ከእሱ ቀድማ ሄደች። ዘፍ 3:6፤ 1ጢሞ 2:11-14
ራሷ የነበረው አዳም በአምላክ ሕግ ላይ ዓመፀ። ሮም 5:12, 19
መ. በመንፈስ ቅዱስ ላይ ኃጢአት መሥራት ሲባል ምን ማለት ነው? (ማቴ 12:32፤ ማር 3:28, 29)
ከአዳም የተወረሰው ኃጢአት ከዚህ የተለየ ነው። ሮም 5:8, 12, 18፤ 1ዮሐ 5:17
አንድ ሰው መንፈስን ሊያሳዝን ሆኖም ተስተካክሎ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ሊመለስ ይችላል። ኤፌ 4:30፤ ያዕ 5:19, 20
ሆነ ብሎ ኃጢአት መሥራትን ልማድ ማድረግ ወደ ሞት ይመራል። 1ዮሐ 3:6-9
አምላክ እንደነዚህ ያሉትን ይፈርድባቸዋል፣ መንፈሱንም ይወስድባቸዋል።እንደነዚህ ላሉት ንስሐ የማይገቡ ሰዎች መጸለይ አይገባንም። 1ዮሐ 5:16, 17
26. ነፍስ
ሰው ነፍስ ነው። ዘፍ 2:7፤ 1ቆሮ 15:45፤ ኢያሱ 11:11 የ1954 ትርጉም፤ ሥራ 27:37
እንስሳትም ነፍሳት ተብለው ተጠርተዋል። ዘኁ 31:28 የ1879 ትርጉም፤ ራእይ 16:3፤ ዘሌ 24:18 የ1879 ትርጉም
ነፍስ ደም አለው፣ ምግብ ይበላል፣ ሊሞት ይችላል። ኤር 2:34 የ1879 ትርጉም፤ መዝ 107:5, 9፤ ሕዝ 18:4
ሰው ሕይወት ስላለው ነፍስ አለው ሊባል ይችላል። ማር 8:36፤ ዮሐ 10:15
ሕይወት ያለው ሰው ወይም ፍጡር ነፍስ ነው። ዮሐ 10:15፤ ዘሌ 17:11 የ1879 ትርጉም
ነፍሳትን የሚያንቀሳቅስ የሕይወት ኃይል “መንፈስ” ይባላል። መዝ 146:4፤ 104:29 NW
ሰው ሲሞት የሕይወት ኃይሉ እንደገና በአምላክ ቁጥጥር ሥር ይሆናል። መክ 12:7
የሕይወት ኃይልን መልሶ ሊሰጥ የሚችለው አምላክ ብቻ ነው። ሕዝ 37:12-14
27. አርማጌዶን
ሀ. ክፋትን ለማስወገድ አምላክ የሚያደርገው ውጊያ
ብሔራት ወደ አርማጌዶን ይሰበሰባሉ። ራእይ 16:14, 16
አምላክ በልጁና በመላእክቱ አማካኝነት ይዋጋል። 2ተሰ 1:6-9፤ ራእይ 19:11-16
ከጥፋቱ መትረፍ የምንችለው እንዴት ነው? ሶፎ 2:2, 3፤ ራእይ 7:14
ዓለም እጅግ ተበላሽቷል። 2ጢሞ 3:1-5
አምላክ ታጋሽ ነው፤ ቢሆንም ፍትሕ እርምጃ እንዲወሰድ ያስገድዳል። 2ጴጥ 3:9, 15፤ ሉቃስ 18:7, 8
ጻድቃን በጥሩ ሁኔታ መኖር እንዲችሉ ክፉዎች መጥፋት አለባቸው። ምሳሌ 21:18፤ ራእይ 11:18
28. አገልጋይ
ሀ. ሁሉም ክርስቲያኖች አገልጋይ መሆን አለባቸው
ኢየሱስ የአምላክ አገልጋይ ነበር። ሮም 15:8, 9፤ ማቴ 20:28
ክርስቲያኖች የእሱን ምሳሌ ይከተላሉ። 1ጴጥ 2:21፤ 1ቆሮ 11:1
አገልግሎታቸውን ለማከናወን መስበክ ይኖርባቸዋል። 2ጢሞ 4:2, 5፤ 1ቆሮ 9:16
የአምላክ መንፈስና የቃሉ እውቀት። 2ጢሞ 2:15፤ ኢሳ 61:1-3
ክርስቶስ በስብከቱ ሥራ የተወውን ምሳሌ ተከተሉ። 1ጴጥ 2:21፤ 2ጢሞ 4:2, 5
አምላክ በመንፈሱና በድርጅቱ በኩል ሥልጠና ይሰጣል። ዮሐ 14:26፤ 2ቆሮ 3:1-3
29. ኢየሱስ
የአምላክ የበኩር ልጅ ነው፤ ሁሉም ነገር የተፈጠረው በእሱ በኩል ነው። ራእይ 3:14፤ ቆላ 1:15-17
ከሴት የተወለደ፣ ከመላእክት ዝቅ ያለ ሰው ሆነ። ገላ 4:4፤ ዕብ 2:9
በአምላክ መንፈስ ተወለደ፤ የወደፊት ዕጣው ወደ ሰማይ መሄድ ነበር። ማቴ 3:16, 17
ሰው ከመሆኑ በፊት ከነበረው የበለጠ ክብር ተሰጠው። ፊልጵ 2:9, 10
ለ. ለመዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን የግድ አስፈላጊ ነው
ክርስቶስ፣ እንደሚመጣ አስቀድሞ የተነገረለት የአብርሃም ዘር ነው። ዘፍ 22:18፤ ገላ 3:16
ብቸኛው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ነው፣ ቤዛ ሆኗል። 1ዮሐ 2:1, 2፤ ዕብ 7:25, 26፤ ማቴ 20:28
አምላክንና ክርስቶስን በማወቅና በመታዘዝ ሕይወት ይገኛል። ዮሐ 17:3፤ ሥራ 4:12
እምነት በሥራ የተደገፈ መሆን አለበት። ያዕ 2:17-26፤ 1:22-25
ትእዛዛቱን ማክበርና እሱ የሠራውን ሥራ መሥራት አለብን። ዮሐ 14:12, 15፤ 1ዮሐ 2:3
ጌታ ብለው የሚጠሩት ሁሉ ወደ መንግሥቱ ይገባሉ ማለት አይደለም። ማቴ 7:21-23
30. ክፋት፣ በዓለም ላይ ያለው መከራ
ሀ. በዓለም ላይ ላለው መከራ ተጠያቂው ማን ነው?
ዛሬ ላለው ክፉ ዘመን መንስኤው መጥፎ አገዛዝ ነው። ምሳሌ 29:2፤ 28:28
የዓለም ገዥ የአምላክ ጠላት ነው። 2ቆሮ 4:4፤ 1ዮሐ 5:19፤ ዮሐ 12:31
መከራ የመጣው በዲያብሎስ ነው፤ የቀረው ጊዜ አጭር ነው። ራእይ 12:9, 12
ዲያብሎስ ይታሰራል፤ ከዚያም ታላቅ ሰላም ይሰፍናል። ራእይ 20:1-3፤ 21:3, 4
ዲያብሎስ የአምላክ ፍጡሮች ከእሱ ጐን በታማኝነት አይቆሙም የሚል ክርክር አንስቷል። ኢዮብ 1:11, 12
ታማኝ ፍጡሮች ታማኝነታቸውን እንዲያስመሠክሩ አጋጣሚ ተሰጥቷቸዋል። ሮም 9:17፤ ምሳሌ 27:11
የዲያብሎስ ሐሰተኝነት ተረጋግጧል፤ የተነሳው ጥያቄ ሙሉ በሙሉ እልባት ያገኛል። ዮሐ 12:31
ታማኞቹ የዘላለም ሕይወት ሽልማት ያገኛሉ። ሮም 2:6, 7፤ ራእይ 21:3-5
ሐ. የፍጻሜው ዘመን መርዘሙ የምሕረት ዝግጅት ነው
እንደ ኖኅ ዘመን ሁሉ ዛሬም ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ጊዜ ያስፈልጋል። ማቴ 24:14, 37-39
አምላክ መሐሪ ነው እንጂ እርምጃ ለመውሰድ አይዘገይም። 2ጴጥ 3:9፤ ኢሳ 30:18
መጽሐፍ ቅዱስ ሳናስበው በወጥመድ ከመያዝ እንድንጠበቅ ይረዳናል። ሉቃስ 21:36፤ 1ተሰ 5:4
ጥበቃ ለማግኘት አሁኑኑ አምላክ ባዘጋጀው ዝግጅት ተጠቀሙ። ኢሳ 2:2-4፤ ሶፎ 2:3
መ. በዓለም ላይ ላለው መከራ ሰው መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም
ሰዎች በፍርሃት ተውጠዋል፣ ግራ ተጋብተዋል። ሉቃስ 21:10, 11፤ 2ጢሞ 3:1-5
የሚሳካለት የአምላክ መንግሥት እንጂ የሰዎች መንግሥት አይደለም። ዳን 2:44፤ ማቴ 6:10
በሕይወት ለመኖር ከንጉሡ ጋር አሁኑኑ ሰላም መሥርቱ። መዝ 2:9, 11, 12
31. ዕድል ተወስኗል?
የአምላክ ዓላማ መፈጸሙ የተረጋገጠ ነው። ኢሳ 55:11፤ ዘፍ 1:28
ግለሰቦች አምላክን ለማገልገል ምርጫ ተሰጥቷቸዋል። ዮሐ 3:16፤ ፊልጵ 2:12
32. የመጨረሻዎቹ ቀኖች
የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ማለት ነው። ማቴ 24:3፤ 2ጴጥ 3:5-7፤ ማር 13:14
የክፉ ሥርዓት እንጂ የምድር ፍጻሜ አይደለም። 1ዮሐ 2:17
ከጥፋቱ በፊት የፍጻሜ ዘመን መምጣት አለበት። ማቴ 24:14
ጻድቃን ይድናሉ፤ አዲስ ሥርዓት ይከተላል። 2ጴጥ 2:9፤ ራእይ 7:14-17
ለ. የመጨረሻውን ቀን ምልክቶች ነቅቶ መከታተል ያስፈልጋል
አምላክ ጊዜውን ለይተን እንድናውቅ ምልክቶች ሰጥቶናል። 2ጢሞ 3:1-5፤ 1ተሰ 5:1-4
ዓለም የጉዳዩን አሳሳቢነት መገንዘብ ተስኖታል። 2ጴጥ 3:3, 4, 7፤ ማቴ 24:39
አምላክ እርምጃ ለመውሰድ አይዘገይም፤ ነገር ግን ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። 2ጴጥ 3:9
ሁኔታውን በንቃትና በትኩረት መከታተል ወሮታ ያስገኛል። ሉቃስ 21:34-36
33. የቀድሞ አባቶችን ማምለክ
የቀድሞ አባቶች ሙት ናቸው፣ ምንም አያውቁም። መክ 9:5, 10
የመጀመሪያዎቹ ወላጆች መመለክ የሚገባቸው አይደሉም። ሮም 5:12, 14፤ 1ጢሞ 2:14
አምላክ ይህን ዓይነቱን አምልኮ ይከለክላል። ዘፀ 34:14፤ ማቴ 4:10
ለ. ሰዎች ሊከበሩ ይችላሉ፤ መመለክ የሚገባው ግን አምላክ ብቻ ነው
ወጣቶች ትልልቅ ሰዎችን ማክበር አለባቸው። 1ጢሞ 5:1, 2, 17፤ ኤፌ 6:1-3
መመለክ የሚገባው ግን አምላክ ብቻ ነው። ሥራ 10:25, 26፤ ራእይ 22:8, 9
34. የክርስቶስ መመለስ
ወደፊት ዓለም እንደማያየው ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል። ዮሐ 14:19
ማረጉን የተመለከቱት ደቀ መዛሙርቱ ብቻ ናቸው፤ የሚመለሰውም በተመሳሳይ ሁኔታ ነው። ሥራ 1:6, 10, 11
የማይታይ መንፈስ ሆኖ በሰማይ ይኖራል። 1ጢሞ 6:14-16፤ ዕብ 1:3
የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ ይመለሳል። ዳን 7:13, 14
ደቀ መዛሙርቱ የመገኘቱን ምልክት እንዲነግራቸው ጠይቀውት ነበር። ማቴ 24:3
ክርስቲያኖች መገኘቱን “የሚያዩት” በማስተዋል ዓይናቸው ነው። ኤፌ 1:18
የመገኘቱ ማስረጃ የሆኑ ብዙ ክንውኖች አሉ። ሉቃስ 21:10, 11
ጠላቶች ጥፋት ሲመጣባቸው “ያዩታል።” ራእይ 1:7
35. የዘመናት ስሌት
ሀ. የአሕዛብ ዘመን በ1914 (ከክ. ል. በኋላ) ተፈጸመ
የነገሥታቱ ሥርወ መንግሥት በ607 ከክ. ል. በፊት ተቋረጠ። ሕዝ 21:25-27
አገዛዙ ዳግም እስኪቋቋም ድረስ “ሰባት ዓመት” ማለፍ ነበረበት። ዳን 4:32, 16, 17
ሰባት = 2 × 3 1/2 ዓመት፤ ወይም 2 × 1,260 ቀናት። ራእይ 12:6, 14፤ 11:2, 3
አንድ ቀን እንደ አንድ ዓመት ተደርጎ ይወሰዳል። [2,520 ዓመታት ይሆናሉ።] ሕዝ 4:6፤ ዘኁ 14:34
ይህ የአሕዛብ ዘመን መንግሥቱ እስኪቋቋም ድረስ የሚቀጥል ነበር። ሉቃስ 21:24፤ ዳን 7:13, 14
36. የይሖዋ ምሥክሮች
ይሖዋ የራሱን ምሥክሮች ማንነት ገልጿል። ኢሳ 43:10-12፤ ኤር 15:16
ከአቤል አንስቶ ብዙ ታማኝ ምሥክሮች አሉት። ዕብ 11:4, 39፤ 12:1
ኢየሱስ የታመነና እውነተኛ ምሥክር ነው። ዮሐ 18:37፤ ራእይ 1:5፤ 3:14
37. ይሖዋ፣ አምላክ
“አምላክ” የሚለው ቃል የወል ስም ነው፣ ጌታችን የግል ስም አለው። 1ቆሮ 8:5, 6
ስሙ እንዲቀደስ እንጸልያለን። ማቴ 6:9, 10
የአምላክ ስም ይሖዋ ነው። መዝ 83:18 NW፤ ዘፀ 6:2, 3 የ1879 ትርጉም፤ 3:15 NW፤ ኢሳ 42:8 NW
በኪንግ ጄምስ ትርጉም ስሙ ዘፀ 6:3 ላይ ይገኛል (ዲዋይ የግርጌ ማስታወሻ)። መዝ 83:18 NW፤ ኢሳ 12:2 NW፤ 26:4 NW
ኢየሱስ ይህን ስም ለሰዎች አሳውቋል። ዮሐ 17:6, 26፤ 5:43፤ 12:12, 13, 28
አምላክን አይቶ መኖር አይቻልም። ዘፀ 33:20፤ ዮሐ 1:18፤ 1ዮሐ 4:12
ለማመን አምላክን ማየት አያስፈልግም። ዕብ 11:1፤ ሮም 8:24, 25፤ 10:17
አምላክ በሚታዩ ሥራዎቹ ይታወቃል። ሮም 1:20፤ መዝ 19:1, 2
የትንቢቶች መፈጸም የአምላክን መኖር ያረጋግጣል። ኢሳ 46:8-11
አምላክ ፍቅር ነው። 1ዮሐ 4:8, 16፤ ዘፀ 34:6፤ 2ቆሮ 13:11፤ ሚክ 7:18 [NW]
በጥበብ የላቀ ነው። ኢዮብ 12:13፤ ሮም 11:33፤ 1ቆሮ 2:7
ፍትሐዊ ነው፤ ፍትሕ እንዲሰፍን ያደርጋል። ዘዳ 32:4፤ መዝ 37:28
ሁሉን ቻይ ነው፤ ኃይሉ ገደብ የለውም። ኢዮብ 37:23፤ ራእይ 7:12፤ 4:11
መ. ሁሉም ሰው የሚያመልከው አንዱን አምላክ አይደለም
ጥሩ የሚመስል መንገድ ሁሉ ትክክለኛ ነው ማለት አይደለም። ምሳሌ 16:25፤ ማቴ 7:21
ሁለት መንገዶች አሉ፤ ወደ ሕይወት የሚመራው አንዱ ብቻ ነው። ማቴ 7:13, 14፤ ዘዳ 30:19
ብዙ አማልክት አሉ፤ እውነተኛው አምላክ ግን አንድ ነው። 1ቆሮ 8:5, 6፤ መዝ 82:1
እውነተኛውን አምላክ ማወቅ ሕይወት ለማግኘት የግድ አስፈላጊ ነው። ዮሐ 17:3፤ 1ዮሐ 5:20
38. ደም
ሀ. ደም መውሰድ ወይም መስጠት ከደም ቅድስና ጋር ይቃረናል
ኖኅ ደም ቅዱስ እንደሆነና ሕይወት እንደሆነ ተነግሮት ነበር። ዘፍ 9:4, 16
የሕጉ ቃል ኪዳን ደም መብላትን ይከለክል ነበር። ዘሌ 17:14፤ 7:26, 27
ክርስቲያኖችም ከደም እንዲርቁ ታዘዋል። ሥራ 15:28, 29፤ 21:25
ለ. ሕይወትን ለማዳን ነው የሚለው ሰበብ የአምላክን ሕግ ለማፍረስ ምክንያት ሊሆን አይችልም
መታዘዝ ከመሥዋዕት ይበልጣል። 1ሳሙ 15:22፤ ማር 12:33
የራስን ሕይወት ከአምላክ ሕግ ማስቀደም ለሞት ይዳርጋል። ማር 8:35, 36
39. ዲያብሎስ፣ አጋንንት
በሰው ውስጥ ያለ ክፋት ሳይሆን መንፈሳዊ አካል ነው። 2ጢሞ 2:26
ዲያብሎስ ልክ እንደ መላእክት ራሱን የቻለ አንድ አካል ነው። ማቴ 4:1, 11፤ ኢዮብ 1:6
በውስጡ መጥፎ ምኞቶችን በማሳደር ራሱን ዲያብሎስ አደረገ። ያዕ 1:13-15
ለ. ዲያብሎስ በዓይን የማይታይ የዓለም ገዥ ነው
እንደ አምላክ ሆኖ ዓለምን ይቆጣጠራል። 2ቆሮ 4:4፤ 1ዮሐ 5:19፤ ራእይ 12:9
ክርክሩ መልስ እስኪያገኝ ድረስ እንዲቆይ ተፈቀደለት። ዘፀ 9:16፤ ዮሐ 12:31
በጥልቅ ውስጥ ይታሰራል፤ ከዚያም ይደመሰሳል። ራእይ 20:2, 3, 10
ከጥፋት ውኃ በፊት ከሰይጣን ጎን ተሰለፉ። ዘፍ 6:1, 2፤ 1ጴጥ 3:19, 20
እንዲዋረዱ ተደርገዋል፤ ማንኛውም የእውቀት ብርሃን ተቋርጦባቸዋል። 2ጴጥ 2:4፤ ይሁዳ 6
አምላክን ይጻረራሉ፤ ሰውን ይጨቁናሉ። ሉቃስ 8:27-29፤ ራእይ 16:13, 14
ከሰይጣን ጋር ይደመሰሳሉ። ማቴ 25:41፤ ሉቃስ 8:31፤ ራእይ 20:2, 3, 10
40. ጋብቻ
ከክርስቶስና ከሙሽራው ጋር ተመሳስሏል። ኤፌ 5:22, 23
የጋብቻ መኝታ መርከስ የለበትም። ዕብ 13:4
ባልና ሚስት ተለያይተው እንዳይኖሩ ተመክረዋል።ለፍቺ የሚያበቃው ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረት ፖርኒያ ብቻ ነው። ማቴ 19:9
ለ. ክርስቲያኖች የራስነትን መሠረታዊ ሥርዓት ማክበር አለባቸው
ባል ራስ እንደመሆኑ መጠን ቤተሰቡን መውደድና መንከባከብ አለበት። ኤፌ 5:23-31
ሚስት ለባሏ መገዛት፣ እሱን ማፍቀርና መታዘዝ አለባት። 1ጴጥ 3:1-7፤ ኤፌ 5:22
ልጆች ታዛዥ መሆን አለባቸው። ኤፌ 6:1-3፤ ቆላ 3:20
ሐ. ክርስቲያን ወላጆች ልጆቻቸውን በተመለከተ ያለባቸው ኃላፊነት
ጊዜያቸውንና ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ፍቅር ማሳየት አለባቸው። ቲቶ 2:4
አታበሳጯቸው። ቆላ 3:21
መንፈሳዊ ነገሮችን ጨምሮ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች አሟሉላቸው። 2ቆሮ 12:14፤ 1ጢሞ 5:8
ሕይወታቸውን እንዴት መምራት እንዳለባቸው አሠልጥኗቸው። ኤፌ 6:4፤ ምሳሌ 22:6, 15፤ 23:13, 14
መ. ክርስቲያኖች ማግባት ያለባቸው ክርስቲያኖችን ብቻ ነው
ማግባት ያለባችሁ “በጌታ ብቻ” ነው። 1ቆሮ 7:39፤ ዘዳ 7:3, 4፤ ነህ 13:26
ሠ. ከአንድ በላይ ማግባት ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ የለውም
በመጀመሪያ የነበረው ዝግጅት አንድ ሰው አንዲት ሚስት ብቻ እንድትኖረው ነበር። ዘፍ 2:18, 22-25
ኢየሱስ ክርስቲያኖች ይህንኑ መሥፈርት እንዲከተሉ አስተምሯል። ማቴ 19:3-9
የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ከአንድ በላይ አያገቡም ነበር። 1ቆሮ 7:2, 12-16፤ ኤፌ 5:28-31
41. ጥምቀት
ኢየሱስ ምሳሌ ትቶልናል። ማቴ 3:13-15፤ ዕብ 10:7
ራሳችንን መካዳችንን ወይም ለአምላክ መወሰናችንን የሚያሳይ ምልክት ነው። ማቴ 16:24፤ 1ጴጥ 3:21
መማር የሚችሉበት ዕድሜ ላይ የደረሱ ብቻ ይጠመቃሉ። ማቴ 28:19, 20፤ ሥራ 2:41
ትክክለኛው መንገድ ውኃ ውስጥ ማጥለቅ ነው። ሥራ 8:38, 39፤ ዮሐ 3:23
ኢየሱስ የተጠመቀው ከኃጢአት ታጥቦ ለመንጻት አልነበረም። 1ጴጥ 2:22፤ 3:18
ኃጢአትን የሚያጥበው የኢየሱስ ደም ነው። 1ዮሐ 1:7
42. ጸሎት
አምላክ የሰዎችን ጸሎት ይሰማል። መዝ 145:18፤ 1ጴጥ 3:12
ዓመፀኞች አካሄዳቸውን ካልለወጡ ተሰሚነት አያገኙም። ኢሳ 1:15-17
በኢየሱስ ስም መጸለይ ያስፈልጋል። ዮሐ 14:13, 14፤ 2ቆሮ 1:20
ከአምላክ ፈቃድ ጋር የሚስማማ ጸሎት ማቅረብ አለብን። 1ዮሐ 5:14, 15
እምነት አስፈላጊ ነው። ያዕ 1:6-8
ለ. በከንቱ መደጋገም፣ ለማርያም ወይም “ለቅዱሳን” መጸለይ ዋጋ የለውም
በኢየሱስ ስም ወደ አምላክ መጸለይ አለብን። ዮሐ 14:6, 14፤ 16:23, 24
እንዲሁ ቃላትን መደጋገም ተሰሚነት አያስገኝም። ማቴ 6:7
43. ፈውስ፣ ልሳን
መንፈሳዊ ሕመም ለጥፋት ይዳርጋል። ኢሳ 1:4-6፤ 6:10፤ ሆሴዕ 4:6
ዋነኛው ተልእኮ መንፈሳዊ ፈውስ ነው። ዮሐ 6:63፤ ሉቃስ 4:18
ኃጢአትን ያስወግዳል፤ ደስታና ሕይወት ይሰጣል። ያዕ 5:19, 20፤ ራእይ 7:14-17
ለ. የአምላክ መንግሥት ዘላቂ አካላዊ ፈውስ ያመጣል
ኢየሱስ የተለያዩ በሽታዎችን ፈውሷል፤ መንግሥቱ ስለሚያመጣቸው በረከቶችም ሰብኳል። ማቴ 4:23
መንግሥቱ ዘላቂ ፈውስ እንደሚያስገኝ ተስፋ ተሰጥቷል። ማቴ 6:10፤ ኢሳ 9:7
ሞትም እንኳ ይጠፋል። 1ቆሮ 15:25, 26፤ ራእይ 21:4፤ 20:14
ሐ. በዘመናችን ተአምራዊ ፈውስ መለኮታዊ ድጋፍ ያለው ለመሆኑ ማስረጃ የለም
ደቀ መዛሙርት ራሳቸውን በተአምር አይፈውሱም ነበር። 2ቆሮ 12:7-9፤ 1ጢሞ 5:23
ተአምር የማድረግ ስጦታዎች ከሐዋርያት ዘመን በኋላ አቁመዋል። 1ቆሮ 13:8-11
መፈወስ የአምላክ ድጋፍ ለመኖሩ አስተማማኝ ማስረጃ አይደለም። ማቴ 7:22, 23፤ 2ተሰ 2:9-11
መ. በልሳን መናገር ለጊዜው ብቻ የተሰጠ ስጦታ ነበር
ምልክት ብቻ ነበር፤ ክርስቲያኖች ከዚያ የሚበልጡትን ስጦታዎች መፈለግ ነበረባቸው። 1ቆሮ 14:22፤ 12:30, 31
የመንፈስ ተአምራዊ ስጦታዎች እንደሚቀሩ አስቀድሞ ተነግሮ ነበር። 1ቆሮ 13:8-10
የተለያዩ ድንቅ ነገሮችን መፈጸም የአምላክ ድጋፍ መኖሩን የሚያሳይ አስተማማኝ ማስረጃ አይደለም። ማቴ 7:22, 23፤ 24:24
44. ፍጥረት
ሀ. በትክክለኛ ማስረጃ ከተደገፈ ሳይንስ ጋር ይስማማል፤ የዝግመተ ለውጥን ጽንሰ ሐሳብ ውድቅ ያደርጋል
ሳይንስ ከፍጥረት ሥራ ቅደም ተከተል ጋር ይስማማል። ዘፍ 1:11, 12, 21, 24, 25
አምላክ ሁሉም ‘እንደየወገኑ’ እንዲባዛ ያወጣው ሕግ እውነት ሆኖ ተገኝቷል። ዘፍ 1:11, 12፤ ያዕ 3:12
ለ. የፍጥረት ቀናት የ24 ሰዓት ርዝመት ያላቸው ቀናት አይደሉም
“ቀን” አንድን የተወሰነ ጊዜ ሊያመለክት ይችላል። ዘፍ 2:4 የ1954 ትርጉም
በአምላክ ዘንድ ቀን ረጅም ዘመንን ሊያመለክት ይችላል። መዝ 90:4፤ 2ጴጥ 3:8