በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 36

በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን

በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን

ሁላችንም ጓደኞቻችን ሐቀኛ እንዲሆኑ እንፈልጋለን። ይሖዋም ወዳጆቹ ሐቀኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል። ሆኖም ሐቀኛ ያልሆኑ ሰዎች በሞሉበት ዓለም ውስጥ ይህን ባሕርይ ማሳየት ቀላል አይደለም። በሁሉም ነገር ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅሞች አሉት?

1. ሐቀኛ እንድንሆን የሚያነሳሳን ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው?

ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ሐቀኛ መሆናችን ለይሖዋ ያለንን ፍቅርና አክብሮት ያሳያል። ይሖዋ የምናስበውንና የምናደርገውን ነገር ሁሉ እንደሚያውቅ አስታውስ። (ዕብራውያን 4:13) ሐቀኛ ለመሆን የምናደርገውን ጥረት የሚመለከት ከመሆኑም ሌላ ጥረታችንን ያደንቃል። ቃሉ እንዲህ ይላል፦ “ይሖዋ ተንኮለኛን ሰው ይጸየፋልና፤ ከቅኖች ጋር ግን የጠበቀ ወዳጅነት አለው።”ምሳሌ 3:32

2. በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ሐቀኛ መሆናችንን የምናሳይባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ይሖዋ ‘እርስ በርሳችን እውነትን እንድንነጋገር’ ይፈልጋል። (ዘካርያስ 8:16, 17) ይህ ምን ነገሮችን ያካትታል? ለቤተሰባችን አባላት፣ ለሥራ ባልደረቦቻችን፣ ለክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም ለመንግሥት ባለሥልጣናት አንዋሽም ወይም የተዛባ መረጃ አንሰጥም። ሐቀኛ የሆኑ ሰዎች አይሰርቁም ወይም አያጭበረብሩም። (ምሳሌ 24:28⁠ን እና ኤፌሶን 4:28⁠ን አንብብ።) በተጨማሪም የሚጠበቅባቸውን ቀረጥ ይከፍላሉ። (ሮም 13:5-7) እነዚህንም ሆነ እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎች ነገሮችን በማድረግ “በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር” ጥረት እናደርጋለን።—ዕብራውያን 13:18

3. ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅሞች አሉት?

ሐቀኛ በመሆን ረገድ ጥሩ ስም ስናተርፍ ሌሎች እምነት ይጥሉብናል። በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሁሉ ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ እርስ በርስ እንዲተማመኑና የደህንነት ስሜት እንዲሰማቸው አስተዋጽኦ እናደርጋለን። ንጹሕ ሕሊና ይኖረናል። በተጨማሪም ሐቀኛ መሆናችን “አዳኛችን የሆነው አምላክ ትምህርት . . . ውበት እንዲጎናጸፍ” እንዲሁም ሌሎች ወደ እውነተኛው አምልኮ እንዲሳቡ ያደርጋል።—ቲቶ 2:10

ጠለቅ ያለ ጥናት

ሐቀኛ መሆንህ ከይሖዋ ጋር ያለህን ግንኙነት የሚነካው እንዴት እንደሆነ እንዲሁም በተለያዩ የሕይወትህ ክፍሎች ሐቀኛ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

4. ሐቀኝነት ይሖዋን ያስደስታል

መዝሙር 44:21ን እና ሚልክያስ 3:16ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • እውነቱን መደበቅ እንደምንችል ማሰብ ሞኝነት የሆነው ለምንድን ነው?

  • ከባድ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ እውነቱን ለመናገር ስንመርጥ ይሖዋ ምን የሚሰማው ይመስልሃል?

ልጆች እውነቱን ሲናገሩ ወላጆች ይደሰታሉ። እኛም እውነቱን ስንናገር ይሖዋ ይደሰታል

5. ምንጊዜም ሐቀኛ ሁን

ብዙ ሰዎች እውነቱን መናገር የማያዋጣበት ጊዜ እንዳለ ይሰማቸዋል። ሆኖም ሁልጊዜ ሐቀኛ መሆን ያለብን ለምንድን ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ

ዕብራውያን 13:18ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ሁኔታዎች ሥር ሐቀኛ መሆን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩ፦

  • በቤተሰብ ውስጥ

  • በሥራ ወይም በትምህርት ቤት

  • በሌሎች ሁኔታዎች

6. ሐቀኛ መሆናችን ይጠቅመናል

ሐቀኛ መሆናችን አንዳንድ ችግሮች ሊያስከትልብን ይችል ይሆናል። ውሎ አድሮ ከሚያስገኘው ጥቅም አንጻር ግን ሐቀኝነት ሁሌም የተሻለ አማራጭ ነው። መዝሙር 34:12-16ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ሐቀኛ መሆንህ የተሻለ ሕይወት እንድትመራ የሚረዳህ እንዴት ነው?

  1. ሀ. ሐቀኛ ባልና ሚስት ጠንካራ ትዳር ይኖራቸዋል

  2. ለ. ሐቀኛ ሠራተኞች የአሠሪዎቻቸውን አመኔታ ያተርፋሉ

  3. ሐ. ሐቀኛ ዜጎች በመንግሥት ባለሥልጣናት ዘንድ ጥሩ ስም ይኖራቸዋል

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “አንዳንድ ትናንሽ ውሸቶችን መዋሸት ምንም ችግር የለውም።”

  • ይሖዋ ሁሉንም ዓይነት ውሸት ይጠላል ብለህ እንድታምን የሚያደርግህ ምንድን ነው?

ማጠቃለያ

ይሖዋ ወዳጆቹ፣ በሚናገሩትም ሆነ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ ሐቀኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል።

ክለሳ

  • ሐቀኛ መሆናችንን የምናሳይባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

  • እውነቱን መደበቅ እችላለሁ ብሎ ማሰብ ሞኝነት የሆነው ለምንድን ነው?

  • ምንጊዜም ሐቀኛ መሆን የምትፈልገው ለምንድን ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

ወላጆች ልጆቻቸውን ሐቀኛ እንዲሆኑ ማስተማር የሚችሉት እንዴት ነው?

እውነቱን ተናገር (1:44)

የገባነውን ቃል መጠበቅ ምን ጥቅም አለው?

ቃላችሁን ጠብቁ፤ ትባረካላችሁ (9:09)

በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ላይውል ቢችልም እንኳ ቀረጥ መክፈል ያለብን ለምንድን ነው?

“ቀረጥ መክፈል ይኖርብሃል?” (መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1, 2011)

የማጭበርበር ድርጊት ይፈጽም የነበረ አንድ ሰው ሕይወቱን እንዲለውጥና በሐቀኝነት እንዲሠራ ያነሳሳው ምንድን ነው?

“ይሖዋ መሐሪና ይቅር ባይ እንደሆነ ተማርኩ” (መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1, 2015)