‘የመጨረሻ ቀኖች’ እና መንግሥቲቱ
ምዕራፍ 12
‘የመጨረሻ ቀኖች’ እና መንግሥቲቱ
1. (ሀ) አሁን ምን በጣም አስፈላጊ የሆኑ ጥያቄዎች ይነሣሉ? (ለ) ቅዱሳን ጽሑፎች ምድርንና እርሷን የሚያበላሿትን በተመለከተ፣ ስለ መጨረሻ ቀኖች ምን ይላሉ?
እኛ በአሁኑ ጊዜ የምንኖረው ‘በመጨረሻዎቹ ቀናት’ ውስጥ ነውን? ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ምን ትርጉም አላቸው? ምድር ራስዋ “የመጨረሻ ቀን” የላትም፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “ለዘላለም እንዳትናወጥ ምድርን በመሠረትዋ ላይ መሠረታት” በማለት ያረጋግጥልናል። ይህ የሚያስደስት ነው። በመጀመሪያው የይሖዋ ዓላማ መሠረት ሰውና እንስሳት እዚችው ምድር ላይ ለዘላለለም ይኖራሉ። (መዝሙር 104:5–24፤ 119:89, 90፤ ዘፍጥረት 1:27, 28፤ 8:21, 22) ነገር ግን የአምላክ ንብረት የሆነችውን ምድር የሚያበላሹት ክፉ ሕዝቦችና ግለሰቦች “የመጨረሻ ቀን” ይኖራቸዋል። እነዚህን አጥፊዎች የሚያጠፋቸው የመንግሥቲቱ ‘መምጣት’ ነው። — 2 ጴጥሮስ 3:3–7፤ ያዕቆብ 5:1–4፤ ራእይ 11:15–18
2. ጳውሎስ ‘በአስጨናቂው ዘመናችን’ ምን ምን ነገር ይሆናል ብሎ ተነበየ?
2 በአሁኑ ጊዜ የምንኖረው በእነዚህ “የመጨረሻ ቀኖች” ውስጥ ይሆን እንዴ? የትኛውንም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም አንሥተህ ሐዋርያው ጳውሎስ በሁለተኛ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ 3 ቁጥር ከ1 እስከ 5 ላይ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት ስለ “መጨረሻ ቀኖች” የተናገረውን ትንቢት አንብብ። ከዚያም በዛሬው ጊዜ ያለው የሰው ልጆች ዓለም መልክ እንደዚህ ሆኗልን? ብለህ ራስህን ጠይቅ። እዚህ ላይ ሐዋርያው “የሚያስጨንቅ ዘመን” እንደሚመጣ ከተናገረ በኋላ እንዲህ አለ:-
“ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብን የሚወዱ፣ ትዕቢተኞች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ይቅር የማይሉ፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ተንኮለኞች፣ ችኩሎች፣ አታላዮች፣ አምላክን ከመውደድ ይልቅ ተድላን የሚወዱ፣ የአምልኮት መልክ ያላቸው ግን ኃይሉን የካዱ ይሆናሉ። ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አይኑርህ።” — ኒው ኢንተርናሽናል ቨርሽን።
3. ጳውሎስ “የመጨረሻ ቀን” ብሎ የጠቀሰው የአይሁድ ሥርዓት መጨረሻ ቀኖችን ሳይሆን ሌላ ይበልጥ ከፍተኛ የሆነን ጊዜ ማመልከት የሚኖርበት ለምንድን ነው?
3 ሐዋርያው ከላይ ያለውን የጻፈው የአይሁዳውያንን የነገሮች ሥርዓት “የመጨረሻ ቀኖች” በተመለከተ አልነበረም። ጳውሎስ እነዚህን ቃላት የጻፈው በ65 እዘአ አካባቢ ስለ ነበር እንደዚያ ሊሆን አይችልም። በዚያን ጊዜ የአይሁድ “የመጨረሻ ቀኖች” ከጀመሩ ከ30 ዓመታት በላይ አልፏቸው ነበር። ኢየሩሳሌም ለመጥፋት የቀራት ጊዜ አምስት ዓመታት ብቻ ነበር። በጊዜው በነበሩት ክርስቲያን ነን በሚሉት ሰዎች ዘንድ ይህ የክህደት ሁኔታ ገና አልተፈጠረም ነበር። እነዚያ የአይሁድ ሥርዓት “የመጨረሻ ቀኖች” አስከፊ ነበሩ፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ መንግሥቱን ለማቋቋም እንደገና ሲመጣ በመላው የሰይጣን ዓለም “የመጨረሻ ቀኖች” ውስጥ ከሚፈጸሙት ነገሮች ጋር ሲወዳደሩ ከቁጥር የሚገቡ አይደሉም።
ሁለት ጊዜ የሚፈጸም
4. ደቀ መዛሙርቱ በማቴዎስ 24:3 ላይ ያለውን ጥያቄ ለመጠየቅ ያነሣሣቸው ምንድን ነው?
4 ኢየሱስ በምሳሌው ላይ ስለ “ነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ ዘመን” ተናግሮ ነበር። (ማቴዎስ 13:39, 40, 49 አዓት) ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ጉዳይ ለማወቅ ፍላጎታቸው ተነሣስቶ ነበር፤ ምክንያቱም በዚያን ጊዜ በተለይ ተራው ሕዝብ በአስጨናቂው የሮም የአገዛዝ ቀንበርና በአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች ጭቆና ይማቅቅ ነበር። የአምላክ መንግሥት ከዚህ ሁሉ እንደምትገላግላቸው ተስፋ አድርገው ነበር። በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ከመሞቱ ከሦስት ቀን በፊት በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ አራት ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው ኢየሩሳሌምን ቁልቁል እየተመለከቱ እንዲህ ብለው ጠየቁት:- “ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የመገኘትህና የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ ዘመን ምልክት ምን ይሆናል?” — ማቴዎስ 24:3 አዓት፤ ማርቆስ 13:3, 4
5. ኢየሱስ ለጥያቄው መልስ ሲሰጥ የተናገራቸው ቃላት የሚፈጸሙት እንዴት ነው?
5 ምንም እንኳን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የታያቸው ከፊት ለፊታቸው የነበረው ጊዜ ቢሆንም በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ሁለት ጊዜ የሚፈጸም ትንቢት ሰጥቷል። ይህም በመጀመሪያ በአይሁድ ሥርዓት “የመጨረሻ ቀኖች” ውስጥ የሚፈጸም ሲሆን ከዚያም ብዙ ዘመናት ቆይቶ መላዋን ምድር በሚያካትተው የሰይጣን ዓለማዊ ሥርዓት “የመጨረሻ ቀኖች” ላይ ይፈጸማል።
6, 7. (ሀ) በማቴዎስ 24:7–22 ላይ የሚገኙት የኢየሱስ ቃላት በትንሹ የተፈጸሙት እንዴት ነው? (ለ) ዛሬ ለዚህ ነገር ምን መታሰቢያ አለ?
6 በማቴዎስ ምዕራፍ 24 ቁጥር 7–22 ላይ ተመዝግበው የሚገኙት ኢየሱስ ለእነዚያ ደቀ መዛሙርቱ የገለጸላቸው ነገሮች እስከ 70 እዘአ በነበሩት 37 ዓመታት ውስጥ በትንሹ የሚፈጸሙ ሁኔታዎች ናቸው። በኢየሱስ ዘመን ለነበሩት አይሁዶች ጊዜው ጦርነት፣ የምግብ እጥረትና የመሬት መንቀጥቀጥ የሚታይበት፤ እንዲሁም ክርስቲያኖች የሚጠሉበትና ሐሰተኛ ክርስቶሶች የሚመጡበት የሁከት ጊዜ ይሆንባቸዋል። ሆኖም “ይህ የመንግሥት ምሥራች” ለምሥክርነት ለሁሉም ፍጥረት መሰበክ ነበረበት። በመጨረሻም ያ “የጥፋት ርኩሰት” ማለትም አረመኔያዊው የሮም ጦር ሠራዊት “የተቀደሰችውን ሥፍራ” የኢየሩሳሌምን ቤተ መቅደስ ወረረ። ሮማውያን ወደኋላ ተመልሰው ለአጭር ጊዜ ፋታ ሲሰጡ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ትንቢታዊ ትእዛዙን በመከተል ለመዳን ወደ ተራሮች ሸሹ። ሮማውያኑ በጄኔራል ቲቶ እየተመሩ ኢየሩሳሌምንና ልጆችዋን ፈጠፈጡ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይተዉ ቤተ መቅደሷን አፈራረሱ። — በተጨማሪም ሉቃስ 19:43, 44፤ ቆላስይስ 1:23 ተመልከት።
7 ኢየሱስ ለተናገረው “ምልክት” ፍጻሜ በመሆን እነዚህ ድርብርብ ችግሮች በአይሁዶች ላይ ብዙ ሥቃይ አደረሱባቸው። በ70 እዘአ ኢየሩሳሌም በእሳት ተቃጥላ ስትጠፋም ተደመደሙ። ከአንድ ሚልዮን በላይ የሚሆኑ አይሁዶች ከከተማቸው ጋር አብረው ተደመሰሱ። በሕይወት የተረፉትም ምርኮኛ ተደርገው ተወሰዱ። ለኢየሱስ ትንቢት መፈጸም አሰቃቂ ማስታወሻ የሆነው የቲቶ የድል ሐውልት እስከ ዛሬ ድረስ በሮም ከተማ ውስጥ ቆሞ ይገኛል። ይሁን እንጂ በጽሑፍ ተመዝግቦና ተጠብቆ የሚገኘው ኢየሱስ የሰጠው “ምልክት” ማስጠንቀቂያ የሚሆነው በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለነበሩት ሰዎች ብቻ ነውን? በዛሬው ጊዜ ‘ያለቀለት፣ የሞተ ታሪክ’ ነውን? መልሱ አይደለም የሚል መሆን ይኖርበታል።
በምድር ዙሪያ የሚኖረው ተፈጻሚነት
8. (ሀ) የኢየሱስ ቃላት በትንሹ መፈጸማቸው ዛሬ እኛን እንዴት ሊነካን ይገባል? (ለ) ይህስ ገና ሊመጡ ላሉ ለምን ነገሮች ምሳሌ ይሆናል?
8 ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት በአይሁድ የነገሮች ሥርዓት “የመጨረሻ ቀኖች” ውስጥ በትንሹ መፈጸማቸው መለኮታዊ ትንቢት የቱን ያህል ኃይል እንዳለው የበለጠ እምነት ሊያሳድርብን ይገባል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን የተፈጸሙት ነገሮች ምድር አቀፍ በሆነው የሰይጣን የነገሮች ሥርዓት ላይ በስፋት ለሚፈጸሙት ነገሮች ጉልህ ትንቢታዊ ምሳሌ ይሆናሉ። በማቴዎስ 24:21, 22 ላይ የሚገኙት የኢየሱስ ቃላት ሙሉ በሙሉ የሚፈጸሙበትን ጊዜ ይጠብቃሉ:-
“በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና። እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።”
9. የኢየሱስ ቃላት ዓለም አቀፋዊ ወደሆነ የፍርድ ቀን እንደሚያመለክቱ እንዴት እናውቃለን?
9 በማቴዎስ 24:23 እስከ 25:46 ላይ የሚገኙት የሚቀጥሉት የኢየሱስ ትንቢት ቃላት “የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ” ዓለም አቀፋዊ ስፋት እንደሚኖረው ያመለክታሉ። ያ የጭንቀት ዘመን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ “የሰው ልጅ” በአምላክ የተሾመ ንጉሥ በመሆን በሰይጣን ዓለም ላይ ፍርዱን ይፈጽማል። “በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ።” ይህም የኢየሱስን ንግሥና የማይቀበሉትን ሁሉ የሚያጠቃልል ይሆናል። ይህ አንድን ሕዝብና ከተማውን ብቻ የሚመለከት ፍርድ ሳይሆን ዓለም አቀፍ የሆነ የፍርድ ቀን ነው። — ማቴዎስ 24:30
10. (ሀ) በኢየሱስ ትንቢት ላይ በምሳሌ እንደተገለጸው ‘የራሳቸውን የግል ጉዳይ የሚያከናውኑት’ ሰዎች መጨረሻ ‘አስቀድመው የአምላክን መንግሥት ከሚፈልጉት’ ሰዎች መጨረሻ የሚለየው እንዴት ነው? (ለ) ይህስ በዓለም አቀፍ ደረጃ መከናወን የሚኖርበት ለምንድን ነው?
10 የአምላክ ፍርድ በመላው ዓለም ላይ የሚፈጸም መሆኑን በድጋሚ ሲያመለክት የኢየሱስ ትንቢት “የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ” ከኖኅ ዘመን የጥፋት ውኃ ቀደም ብሎ ከነበረው ጊዜ ጋር አወዳድሮታል። እንዲህ ይላል:-
“በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፣ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፣ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደነበሩ፣ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፣ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናልና።”
በኖኅ ዘመን የመጣው የጥፋት ውኃ ጠቅላላውን አምላክ የለሽ ዓለም ጠራርጎ እንዳጠፋው ሁሉ የመሲሑ መገኘት የመጨረሻ ደረጃ የሆነው እንደ እሳት የሚለበልበው መከራም መንግሥቲቱን ወደ ጐን በመተው የግል ጉዳያቸውን የሚያሳድዱትን ሁሉ ከምድራችን ያስወግዳል። ደስ የሚለው ግን ‘አስቀድመው መንግሥቱንና ጽድቁን የሚፈልጉ’ ሁሉ በገነቲቱ ምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ለመውረስ ከታላቁ መከራ ይተርፋሉ። ከእነርሱ አንዱ ትሆናለህን? — ማቴዎስ 6:33፤ 24:37–39፤ 25:31–46
11. ይህ ሁሉንም ብሔራት እንደሚጨምርና ከጥፋት የሚተርፉ ሰዎች እንደሚኖሩ የትኞቹ ሌሎች ትንቢቶች ያሳያሉ?
11 በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች መጪው “ታላቅ መዝሙር 2:2–9፤ ኢሳይያስ 34:1, 2፤ ኤርምያስ 25:31–33፤ ሕዝቅኤል 38:23፤ ኢዩኤል 3:12–16፤ ሚክያስ 5:15፤ ዕንባቆም 3:1, 12, 13) ይሁን እንጂ ከጥፋቱ የሚተርፉ ሰዎችም ይኖራሉ። — ኢሳይያስ 26:20, 21፤ ዳንኤል 12:1፤ ኢዩኤል 2:31, 32
መከራ” በምድር ላይ የሚገኙትን “ሁሉንም ሕዝቦች” እንደሚነካ ያሳያሉ። (የንጉሡ በሰማያዊ ክብር መገኘት
12. (ሀ) የኢየሱስን መገኘት የሚያሳውቅ “ምልክት” ለምን አስፈለገ? (ለ) እርሱስ እንደገና ሥጋዊ አካል ለብሶ መገለጥ የማያስፈልገው ለምንድን ነው?
12 ኢየሱስ መገኘቱን ስለሚያረጋግጠው “ምልክት” በተናገረበት ታላቅ ትንቢት ላይ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፣ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል” ሲል ይነግረናል። (ማቴዎስ 25:31) የዚያ ክብር ነጸብራቅ ደካማውን የሰው ዓይን ሊጎዳ ስለሚችል ንጉሡ ከእይታ መሰወር አለበት። (ከዘጸአት 33:17–20፤ ከዕብራውያን 12:2 ጋር አወዳድር።) ‘የመገኘቱ ምልክት’ አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው። መሲሑ ሁለተኛ በሚመጣበት ጊዜ ‘ስለ ኃጢአት መሥዋዕት’ የሚሆን አካል ለብሶ ወደ ምድር ለመምጣት ሲል በሰማይ ያለውን መንፈሳዊ ሕይወት መተው አያስፈልገውም። ሰብአዊ መስዋእቱን ‘ለአንዴና ለሁልጊዜው’ ስላቀረበ ሁለተኛ ጊዜ የሚመጣው ከኃጢአት ነፃ የሆነ የማይታይ ሰማያዊ ንጉሥ በመሆን ነው። — ዕብራውያን 7:26, 27፤ 9:27, 28፤ 10:8–10፤ 1 ጴጥሮስ 3:18
13. ሉቃስ 19:11–27 ኢየሱስ ስለሚመለስበት ሁኔታና አሕዛብ ስለሚያደርጉለት አቀባበል ምን ነገር ይገልጻል?
13 ኢየሱስ የቅርብ ወዳጆቹ ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ባሳለፈው የመጨረሻዋ ምሽት “ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፣ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ” ብሎ ነግሯቸው ነበር። (ዮሐንስ 14:2, 3) ከዚህ ጋር በመስማማት ኢየሱስ በሉቃስ 19:11–27 በሚገኘው ምሳሌው ላይ ‘ለራሱ መንግሥትን ይዞ ሊመለስ ወደ ሩቅ አገር እንደሄደ አንድ መኮንን’ አድርጎ ራሱን ገልጿል። ይህም ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ ነው። ይሁን እንጂ “የአገሩ ሰዎች ይጠሉት ነበርና:- ይህ በላያችን ሊነግሥ አንወድም ብለው በኋላው መልእክተኞችን ላኩ።” ዛሬም ቢሆን ክርስቲያን ነን የሚሉ ነገር ግን የራሳቸውን ፍጽምና የጐደለው ሰብአዊ አገዛዝ ይዘው ለመኖር ስለሚመርጡ “የነገሥታት ንጉሥ” የሆነውን የማይቀበሉ አንዳንድ ሰዎች አሉ። (ራእይ 19:16) በኢየሱስ ምሳሌ ላይ እንደተጠቀሱት “የአገሩ ሰዎች” እነዚህም ከባድ ቅጣት ይደርስባቸዋል።
“የምጥ ጣር መጀመሪያ”
14. ምንም እንኳ ሰዎች ሐሳቡን ቢቃወሙትም 1914 እዘአ ክርስቶስ የተመለሰበት ጊዜ መሆኑን የሚደግፍ ምን ነገር አለ?
14 ይህ ብሔራት ያልፈለጉት ኃያል ንጉሥ በምድር ላይ መግዛት የሚጀምረው መቼ ነው? ማስረጃዎቹ በሙሉ ወደ 1914 እዘአ ያመለክታሉ። ነገር ግን አንድ ሰው ‘ያ ዓመት ሰላማዊ የሆነውን የክርስቶስ ግዛት ከማምጣት ይልቅ በሰው ዘር ላይ የመከራ ዘመን የጀመረበት ዓመት ነው’ በማለት ተቃውሞ ያቀርብ ይሆናል። ዋናው ነጥብም ይህ ነው! ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት መሠረት ‘የዓለም መንግሥት የይሖዋና የክርስቶስ’ በሚሆንበት ጊዜ የምድር ብሔራት ‘ይቆጣሉ።’ (ራእይ 11:15, 18) በተጨማሪም ይህ ጊዜ ይሖዋ የእርሱ ተባባሪ ንጉሥ የሆነውን “በጠላቶችህ መካከል ግዛ” በማለት የሚልክበት ጊዜም ነው። (መዝሙር 110:1, 2) ይሁን እንጂ እነዚህ ጠላቶች ወዲያውኑ አይደመሰሱም።
15. ራእይ ምዕራፍ 12 የመንግሥቱን መወለድ በትክክል የሚገልጸው እንዴት ነው?
15 ራእይ ምዕራፍ 12 ሐዋርያው ዮሐንስ የአምላክ መሲሐዊ መንግሥት ሲወለድ የተመለከተበትን ምሳሌያዊ ሁኔታ እጅግ አስደናቂ የሆነ ራእይ ይገልጻል። ልክ እንደ ወንድ ልጅ በመሆን ይህ መንግሥት ከአምላክ “ሴት” ማለትም መላእክታዊ ፍጥረታት ከሚገኙበት ከሰማያዊ ድርጅቱ ተወለደ። እርሱም “ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።” ይህም የሆነበት ምክንያት መንግሥቱ ሥራውን የሚያካሄደው በይሖዋና በሉዓላዊነቱ ላይ በመደገፍ ነው። — ራእይ 12:1–5
16, 17. (ሀ) ከ1914 ወዲህ ወዮ የሚያሰኙ መከራዎች ለመምጣታቸው ምክንያት የሆነው ምንድን ነው? (ለ) በማቴዎስና በሉቃስ የሚገኙት የኢየሱስ ቃላት የእነዚህን መከራዎች መጀመር የሚገልጹት እንዴት ነው?
ራእይ 12:7–12) በዚህ “ጥቂት ዘመን” በተባለው ጊዜ ውስጥ ንጉሡ የጽድቅ ዝንባሌ ያላቸውን ሰዎች ለመዳን ይሰበስባል፤ እንዲሁም በሰይጣን ዓለም የነገሮች ሥርዓት ላይ ስለሚመጣው ፍርድ ማስጠንቀቂያ ያሰማል። — ማቴዎስ 24:32–41፤ 25:31–33
16 ከዚህ በመቀጠል በሰማይ ላይ ጦርነት ተደረገ። የተሾመው ንጉሥና መላእክቱ ከሰይጣንና ከአጋንንት ጭፍራው ጋር ውጊያ አድርገው የይሖዋ መኖሪያ ከሆኑት ሰማያት በማባረር ወደ ምድራችን ክልል ጣሏቸው። “ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፣ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና” የተባለው በዚህ ምክንያት ነው። (17 ዛሬ እኛ በማቴዎስ ምዕራፍ 24 እና 25 በማርቆስ ምዕራፍ 13 እና በሉቃስ ምዕራፍ 21 ላይ የተመዘገበውን ኢየሱስ የገለጸውን “ምልክት” ፍጻሜ እየተመለከትን ነው። “የምጥ ጣር መጀመሪያ” የሚሆነውን ሁኔታ ኢየሱስ በሚከተሉት ቃላት ሲገልጽ እንመልከት:-
“ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፣ ታላቅም የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ቸነፈር ራብም ይሆናል፤ የሚያስፈራም ነገር ከሰማይም ታላቅ ምልክት ይሆናል።” (ማቴዎስ 24:3, 7, 8፤ ሉቃስ 21:10, 11)
እንዲህ ያለ “የምጥ ጣር” ከ1914 ጀምሮ የሰውን ዘር ሲያተራምስ ቆይቷልን?
18. ከ1914 ጀምሮ ጦርነት በጣም አስከፊ የሆነው እንዴት ነው?
18 ታላቁ ጦርነት (በኋላ አንደኛው የዓለም ጦርነት ተብሎ የተጠራው) የጀመረው በ1914 ነበር። እርሱንም ተከትሎ ቸነፈርና ራብ መጣ። ታሪክ ጸሐፊዎች ከ1914–1918 በተካሄደው ወደር የለሽ መጨፋጨፍ በየጉድጓዱ የረገፉትን የሚልዮኖች ሰቆቃና በየጦር ሜዳው ላይ የደረሰውን እልቂት ለመግለጽ ተቸግረዋል። አይ ዲፕ ኢን ሔል (የሰው ዓይን ሲኦልን ጠለቅ
ብሎ ሲመለከተው ) በተባለው መጽሐፍ ውስጥ ፖል ኔሽ ስለ አውሮፓ የጦር ሜዳዎች እንደሚከተለው በማለት እንደተናገሩ ተጠቅሷል:- “የትኛውም ብዕር ወይም ሥዕል የዚህን አገር ሁኔታ ሊገልጽ አይችልም። ቀንና ሌሊት ከወር እስከ ወር የተካሄደውን ውጊያ ለመግለጽ ያዳግታል። የዚህ ጦርነት አራማጅ ሊሆን የሚችለው ክፉ መንፈስና ጣረ ሞት ብቻ ነው፤ የአምላክ እጅ በየትኛውም ቦታ አይታይም። . . . የቦምብ ናዳው በፍጹም አያቋርጥም። . . . ሕዝብ ተደመሰሰ፣ አካለ ጎዶሎ ሆነ፣ አንዳንዱ ቀወሰ፣ ይህች አገር መቃብራቸው ሆነች — የምስኪኖች ታላቅ መቃብር። ለወሬ ይከብዳል፤ ለአምላክ ምንም ደንታ የማያሳይ ተስፋ ቢስ ጦርነት።”19. ከ1914 ወዲህ የመሬት መንቀጥቀጥ እየጨመረ ስለ መምጣቱ ስታትስቲካዊ መረጃዎች ምን ያሳያሉ?
19 ከዚህም በተጨማሪ ‘የምልክቱ’ ክፍል በመሆን ‘የመሬት መንቀጥቀጥ’ ተጨምሯል። ከ1914 ወዲህ የመሬት መንቀጥቀጥ እየጨመረ መጥቷልን? ይህ ምናልባት የሚያስገርም ሊመስል ይችላል። ሆኖም ያሉት ስታትስቲካዊ መረጃዎች ይበልጥ አስገራሚ ናቸው። ኢል ፒኮሎ በተባለው መጽሔት ላይ ጂኦ ማላጎሊ አስተያየታቸውን ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል:- “በ1,059 ዓመታት ውስጥ (ከ856 እስከ 1914) አስተማማኝ የሆኑ ምንጮች የመዘገቡት 24 ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎችን ብቻ ነው።” እርሳቸው ባቀረቡት መረጃ መሠረት በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በየዓመቱ በአማካይ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1,800 ነበር። ከ1915 ወዲህ ግን 43 ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች ደርሰው በየዓመቱ በአማካይ 25, 300 ሰዎች ተገድለዋል።
20, 21. (ሀ) ከ1914 ወዲህ ምን ነገር ታይቷል? ለምንስ? (ለ) በዛሬው ጊዜ የትኛውን የሉቃስ 21:25, 26 ተፈጻሚነት እያየን ነው? (ሐ) ‘ከሰማይ ታላላቅ ምልክቶች’ ይበልጥ እየታዩ የመጡት እንዴት ነው?
20 በአንደኛው የዓለም ጦርነት ያለማቋረጥ ይወርድ የነበረው የቦምብ ውርጅብኝ አንድ አዲስ ነገር ይኸውም አጠቃላይ ጦርነት መጀመሩን የሚያመለክት ነበር። የአየር መርከብ ተብሎ ይጠራ የነበረውና በኋላም አውሮፕላን የአየር ላይ ውጊያ የሚደረግበትን ዘመን አስጀመረ።
21 ሰው ጠፈርን ድል አድርጎ መያዝ እያለ የሚገልጸው የእድገት ደረጃ በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ያተኮረ ነው። ኃያላን መንግሥታት በሳተላይቶች በመጠቀም ወታደራዊ የጦር ሰፈሮችን ለማቋቋም እቅድ እንዳላቸው የሚያመለክቱ ሁኔታዎችም አሉ። ሆኖም አሁንም ቢሆን አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳይሎችን በመረጡት ዒላማ ላይ ከሰማይ እንደ ዝናብ ለማውረድ ችሎታው አላቸው። በአሁኑ ጊዜ ተቀናቃኝ መንግሥታት የታጠቁት የኑክሌር መሣሪያ ክምችት የሰውን ዘር ብዙ ጊዜ ደጋግሞ ለማጥፋት በቂ ነው። እንደነዚህ ያሉትን የእልቂት መሣሪያዎች የታጠቁ መንግሥታት ቁጥር በዚህ መቶ ዘመን መጨረሻ ላይ 35 እንደሚደርሱ ተገምቷል።
22. (ሀ) ከ1914 ወዲህ ቃል በቃል ባሕር አዲስ መልክ የያዘው እንዴት ነው? (ለ) አዋቂ የሆኑ ሰዎች በምድራችን ላይ ስላለው አስጊ ሁኔታ ምን በማለት ያስጠነቅቃሉ?
22 በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በተካሄደው ውጊያ ላይ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ለጦርነት በመዋሉ ባሕር አዲስ መልክ ለመያዝ በቅቷል። ይህ ሁኔታ በዚያን ጊዜ ዩናይትድ ስቴትስን ጦርነት ውስጥ የከተታት ሲሆን በዛሬው ጊዜ ይበልጥ አደገኛ ሆኗል። የኑክሌር መሣሪያ የተሸከሙ ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች በባሕሮች ላይ በተጠንቀቅ ቆመዋል። በምድር ላይ ከሚሳይል ጥቃት ሊያመልጥ የሚችል ምንም ከተማ የለም። ነሐሴ 30, 1980 የወጣው የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የአሜሪካ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር መሥሪያ ቤት ኤክስፐርት የሆኑትን ማርሻል ዲ ሹልማንን በመጥቀስ የኑክሌር ጦርነት ለመነሣት ያለው አጋጣሚ “እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ እየጨመረ የሚሄድ ይመስለኛል” ብለው እንደተናገሩ ዘግቧል። ከ600 በሚበልጡ ባለሞያ ወንዶችና ሴቶች ድጋፍ መጋቢት 2, 1980 በኒው ዮርክ ታይምስ ላይ የወጣው ሙሉ ገጽ ማስታወቂያ እንዲህ ይላል:- “በተሰወነ አካባቢ ብቻ እንኳ የኑክሌር ጦርነት ቢደረግ በሰው ኅልውና ታሪክ ውስጥ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሞት፣ የአካል ጉዳትና በሽታ ያስከትላል።” በተጨማሪም “አጠቃላይ የሆነ የኑክሌር ውጊያ ቢደረግ በአንድ ሰዓት ውስጥ ሊጠናቀቅና በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ያለውን አብዛኛውን ሕይወት ሊደመስስ
ይችላል” ብለዋል። በ1981 በሞስኮ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት “ዓለም በታሪክ ውስጥ ከምን ጊዜውም ይበልጥ በአደጋ ላይ እንደሆነች ይሰማኛል” ብለው ነበር። አሁንም ብዙ ሕዝብ በአንድ ጊዜ ሊደመስሱ የሚችሉ የጦር መሣሪያዎች ለመሥራት የሚጠፋው ገንዘብ በጣም እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው።23. መንግሥ ቲቱ ‘ትምጣ’ ብለን ከልባችን መጸለይ የሚገባንስ ለምንድን ነው?
23 የኖቤል ሽልማት አሸናፊ የሆኑት ሃሮልድ ሲ ዩሬይ ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደተነበዩት ደረጃ ላይ የተደረሰ ይመስላል። እንዲህ አሉ:- “ወደፊት ፍርሃትን እንበላለን፣ በፍርሃት እንተኛለን፣ በፍርሃት እንኖራለን በፍርሃትም እንሞታለን።”
ይሁን እንጂ ደስ የሚል ነገር አለ፤ ይህችን ምድር ለጥሩ ዓላማ የፈጠራት ሉዓላዊ ጌታ ይሖዋ በልጁ መንግሥት አማካኝነት መውጫውን መንገድ ያዘጋጃል። ነገር ግን ይህን በዝርዝር ከመመርመራችን በፊት የኢየሱስን ትንቢት በበለጠ ትኩረት እንመርምረው። እንደ “ምልክቱ” ገጽታዎች አድርጎ ስለ ዓለም ጦርነት፣ ስለ ራብና ቸነፈር የተናገራቸው ቃላት በራእይ ላይ ከሚገኘው አስደናቂ ትንቢት ጋር እንዴት በአስገራሚ ሁኔታ እንደሚመሳሰሉ እንመልከት። በመሲሑ የምትመራው የአምላክ መንግሥት ለዚህ ሁሉ መፍትሔ መሆኗን አስታውስ። “ትምጣ” ብለን ከልባችን የምንጸልይላት ይህች መንግሥት ናት!
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 115 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
ጸሐፊዎች ስለ 1914 ምን ተናግረዋል?
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላም እንኳ በዘመናችን ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው ታላቅ ዓመት 1914 እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ:-
“በዘመናችን ከሂሮሺማ ይልቅ አዲስ ምዕራፍ ከፋች የሆነው በእርግጥ የ1914 ዓመት ነው። — ሬን ኦልብሬሽት ካሪ፣ “ዘ ሳይንትፊክ መንዝሊ” ሐምሌ 1951
“ከ1914 ወዲህ በዓለም ውስጥ የነገሮችን ሂደት የሚከታተል ማንኛውም ሰው ከምን ጊዜውም ወደ ባሰ ታላቅ አደጋ አንዴ የተወሰነ ጉዞ እየተደረገ እንዳለ በሚመስለው አካሄድ በጥልቅ ተረብሿል። ነገሮችን በጥሞና የሚከታተሉ ብዙ ሰዎች ወደ ጥፋት አዘቅት የሚደረገውን ጉዞ ለመቀየር ምንም ሊደረግ እንደማይቸል ሆኖ እየተሰማቸው መጥቷል። ሰብአዊውን ዘር የሚመለከቱት በግሪክ አሳዛኝ ልብ ወለድ ታሪክ ውስጥ እንዳለ በተቆጡ አማልክት እንደሚነዳና ከዚህ በኋላ ምንም ዕድል እንደሌለው ጀግና አድርገው ነው።” — በርትራንድ ራስል፣ ኒው ዮርክ “ታይምስ መጽሔት” መስከረም 27, 1953
“አዲሱ ዘመን . . . በ1914 ተጀመረ፤ መቼ ወይም እንዴት እንደሚያበቃ ግን የሚያውቅ የለም። . . . ምናልባት ታላቅ እልቂት ካደረሰ በኋላ ያበቃ ይሆናል። — ኤዲቶሪያል፣ “ዘ ሲያትል ታይምስ” ጥር 1, 1959
“በ1914 በዚያን ጊዜ ይታወቅ የነበረውና ተቀባይነት ያገኘው ዓለም ወደ ፍጻሜው መጣ።” — ጄምስ ካሜሮን፣ “1914” በ1959 የታተመ
“አንደኛው የዓለም ጦርነት ታሪክን ከገለባበጡት ታላላቅ ነገሮች አንዱ ነው።” ባርባራ ቱክማን፣ “ዘ ገንስ ኦቭ ኦገስት” 1962
“አንዳንድ ሐሳቦችና ሥዕሎች ወደ አእምሮዬ ይመጣሉ . . . እነዚህም ሐሳቦች ከ1914 በፊት በዚህ ምድር ላይ እውነተኛ ሰላም፣ መረጋጋትና ደኅንነት የነበረበትን ጊዜ የሚያስታውሱኝ ናቸው፤ ያ ጊዜ ምንም ፍርሃትን የማናውቅበት ጊዜ ነበር። . . . ከ1914 ወዲህ አስተማማኝ ኑሮና ጸጥታ ከሰዎች ሕይወት ጠፍተዋል።” የጀርመን ፖለቲከኛ የነበሩት ኮንራድ አደናወር፣ 1965
“አንደኛው የዓለም ጦርነት መላውን ዓለም አናጋው፣ ምክንያቱን ግን እስከ አሁን አላወቅነውም። . . . የተሻለ ዓለም ሲመጣ ይታየን ነበር። ሰላምና ብልጽግና ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ሁሉም ነገር ተናጋ። ከዚያን ጊዜ ወዲህም በድን ሆነናል።” — ዶክተር ዎከር ፔርሲ፣ “አሜሪካን ሜዲካል ኒውስ” ኅዳር 21, 1977
“ዓለም ከ1914 ወዲያ እርስ በርስ ተጣብቆ መኖር ተስኖታል። . . . ይህ ጊዜ ከብሔራዊ ድንበሮች ውጭም ሆነ በብሔራት በራሳቸው ውስጥ ልዩ የብጥብጥና የዓመፅ ጊዜ ሆኗል። — “ዘ ኢኮኖሚስት” ለንደን፣ ነሐሴ 4, 1979
“በ1914 ሥልጣኔ ክፉ ምናልባትም ለሞት የሚያደርስ በሽታ ያዘው። — ፍራንክ ፒተርስ፣ ሴንት ሉዊ “ፖስት ዲስፓች” ጥር 27, 1980
“ሁሉም ነገር እየተሻሻለ ይሄድ ነበር። እኔ የተወለድኩበት ዓለም እንደዚህ ይመስል ነበር። . . . በኋላ ግን በድንገት፣ ሳይጠበቅ አንድ ቀን ጠዋት በ1914 ሁሉም ነገር አበቃለት።” — የእንግሊዙ ፖለቲከኛ ሐሮልድ ማክሚላን፣ ኒው ዮርክ፣ “ታይምስ” ኅዳር 23, 1980