በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለወላጆች የቀረበ ሐሳብ

ለወላጆች የቀረበ ሐሳብ

ለልጆቻችሁ ልትሰጡት የምትችሉት ከሁሉ የላቀ ስጦታ ምንድን ነው? ልጆቻችሁ የእናንተን ፍቅር፣ አመራርና ጥበቃ ጨምሮ ብዙ ነገሮች ያስፈልጓቸዋል። ለልጆቻችሁ ልትሰጡት የምትችሉት ከሁሉ የላቀው ውድ ስጦታ ግን ስለ ይሖዋና በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላለው እውነት ማስተማር ነው። (ዮሐንስ 17:3) እንዲህ ያለው እውቀት ልጆቻችሁ ገና በለጋ ዕድሜያቸው ይሖዋን እንዲወዱና በሙሉ ልባቸው እሱን ለማገልገል እንዲነሳሱ ያደርጋቸዋል።—ማቴዎስ 21:16

ትናንሽ ልጆች አንድን ትምህርት ባልተንዛዛ መንገድና በጨዋታ መልክ ሲማሩት የተሻለ ውጤት እንደሚገኝ በርካታ ወላጆች ተገንዝበዋል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ መማሪያዬ የተባለውን ይህን ብሮሹር ለእናንተ በማዘጋጀታችን ደስ ብሎናል። እያንዳንዱ ትምህርት የተዘጋጀው ቀለል ባለ መንገድ ነው። ሥዕሎቹና በብሮሹሩ ላይ የሰፈሩት ሐሳቦች በተለይ ሦስት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆችን ለማስተማር ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። ብሮሹሩን እንዴት መጠቀም እንደምትችሉ የሚጠቁሙ ሐሳቦችም ተካትተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ መማሪያዬ የተባለው ብሮሹር የተዘጋጀው ለልጆች መጫወቻ ተብሎ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ከልጆቻችሁ ጋር አብራችሁ እንድታነቡት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፤ ይህ ደግሞ በመካከላችሁ ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ እንዲኖር ያስችላል።

ይህ ብሮሹር ልጆቻችሁን ‘ከጨቅላነታቸው ጀምሮ’ ለማስተማር በምታደርጉት ጥረት ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኞች ነን።—2 ጢሞቴዎስ 3:14, 15

ወንድሞቻችሁ

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል