በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት 4

ትምህርት 4

ዝናብ በመዝነቡ፣ ሚጣ ተበሳጨች።

“አያባራም እንዴ?” በማለት አሰበች፤

መጫወት ስላልቻለች በጣም እያዘነች።

ድንገት ሳይታሰብ፣ ፀሐይዋ ብቅ አለች!

ዝናቡ አቆመ፣

ሚጣም ተደሰተች!

ሚጣ እየቦረቀች፣ ወደ ደጁ ወጣች፤ ከዚያም የሚያስገርም! አንድ ነገር አየች።

እየተደነቀች ሚጣ እንዲህ አለች፦ “የዝናቡ ጥቅም የገባኝ አሁን ነው፤ አበቦች እንዲያድጉ አምላክ የሚያደርገው፣ ለካስ ከሰማይ ላይ ዝናብ በማዝነብ ነው!”

ለወላጆች የተሰጠ መመሪያ

ለልጃችሁ አንብቡለት፦

የሐዋርያት ሥራ 14:17

ልጃችሁ የሚከተሉትን ነገሮች እንዲያመለክት አድርጉ፦

መስኮት ወፍ ሚጣ

ዛፍ አበቦች

ልጃችሁ የሚከተሉትን ነገሮች ፈልጎ እንዲያገኝ አድርጉ፦

ጥንዚዛ አውሮፕላን

ልጃችሁን ጠይቁት፦

ይሖዋ ዝናብ እንዲዘንብ የሚያደርገው ለምንድን ነው?