በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 1

ጥሩ መግቢያ

ጥሩ መግቢያ

የሐዋርያት ሥራ 17:22

ፍሬ ሐሳብ፦ መግቢያህ አድማጮች ጉጉት እንዲያድርባቸው የሚያደርግ፣ ርዕሰ ጉዳዩ ምን እንደሆነ የሚገልጽ እንዲሁም ለትምህርቱ ትኩረት ሊሰጡት የሚገባው ለምን እንደሆነ የሚጠቁም መሆን አለበት።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ጉጉት እንዲያድርባቸው አድርግ። የአድማጮችህን ትኩረት ሊስብ የሚችል ጥያቄ፣ እውነተኛ ታሪክ፣ የዜና ዘገባ ወይም ሌላ ነገር ጥቀስ።

  • ርዕሰ ጉዳዩ ምን እንደሆነ ጠቁም። መግቢያህ ርዕሰ ጉዳዩንና ዓላማውን ለአድማጮችህ ግልጽ የሚያደርግ መሆን አለበት።

  • ትምህርቱ እንዴት እንደሚጠቅማቸው ግለጽ። አድማጮችህን ሊጠቅሙ የሚችሉ ነገሮችን ከግምት በማስገባት መግቢያህ በዚያ ላይ ያተኮረ እንዲሆን አድርግ። አድማጮችህ የምትናገረው ነገር በግለሰብ ደረጃ እንዴት እንደሚጠቅማቸው ግልጽ ሊሆንላቸው ይገባል።