በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 10

ድምፅን መለዋወጥ

ድምፅን መለዋወጥ

ምሳሌ 8:4, 7

ፍሬ ሐሳብ፦ የድምፅህን መጠን፣ ውፍረትና ቅጥነት እንዲሁም የምትናገርበትን ፍጥነት በመለዋወጥ መልእክቱን በግልጽ ለማስተላለፍ ብሎም የአድማጮችህን ስሜት ለመቀስቀስ ጥረት አድርግ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • የድምፅን መጠን መለዋወጥ። የድምፅህን መጠን ከፍ በማድረግ ዋና ዋና ነጥቦችን ማጉላትና አድማጮችህን ለተግባር ማነሳሳት ትችላለህ። የፍርድ መልእክት የያዙ ቅዱስ ጽሑፋዊ ሐሳቦችን ስታነብም እንዲሁ አድርግ። አድማጮችህ ጉጉት እንዲያድርባቸው ለማድረግ ዝግ ባለ ድምፅ ተናገር፤ የፍርሃትና የጭንቀት ስሜት የሚንጸባረቅበት ሐሳብ በምትናገርበት ጊዜም በዚህ ዘዴ መጠቀም ትችላለህ።

  • የድምፅን ውፍረትና ቅጥነት መለዋወጥ። ሞቅ ባለ ስሜት ለመናገር አሊያም መጠንን ወይም ርቀትን ለመግለጽ ድምፅህን ቀጠን ማድረግ ትችላለህ፤ እርግጥ እንዲህ ያለውን የአነጋገር ዘዴ የምትጠቀመው በአካባቢህ የተለመደ ከሆነ ነው። የሐዘን ወይም የጭንቀት ስሜትን ለማንጸባረቅ ደግሞ ወፈር ባለ ድምፅ ተናገር።

  • የምትናገርበትን ፍጥነት መለዋወጥ። ለየት ያለ ስሜት (ደስታ፣ ድንጋጤ ወዘተ) የሚፈጥር ነገር ስትናገር ፍጥነትህን ጨመር አድርግ። አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን ስትጠቅስ ደግሞ ረጋ ብለህ ተናገር።